የኢህአዴግ ውህደት በሦስቱ አባል ድርጅቶች ድጋፍና በህወሓት ተቃውሞ ፀድቋል

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በአብላጭ ድምፅ ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ::

ኮሚቴው በውህደቱ ማዕቀፍ ውሰጥ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን በስፋት እንስቶ መወያየየቱንም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ ተናግረዋል::

በዚህም ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ተጠናክሮ በሚቀጥልበትና የራስ አስተዳደር በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ኮሚቴው በዛሬው ስብሰባው ትኩረት ሰጥቶ በዝርዝር መወያየቱንም ገልፀዋል::

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በዛሬው እለት የተጀመረው ስብሰባ ላይ፡፡

Posted by Seyoum Teshome on Saturday, November 16, 2019

የቋንቋ ብዝሃነት ፣ የብሔር እና ሀገራዊ ማንነትን ሚዛኑን በጠበቀ መልክ እንዲጠናከር የሚሉት ጉዳዮችም በመድረኩ ላይ ምክክር ተደርጎባቸዋል ብለዋል አቶ ፍቃዱ::

በመሆኑም ሁሉንም ብሄር ብሔረሰቦች ያማከለ ፍትሃዊ ውክልና በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ውጥስ እንድኖር በዝርዝር ተመክሮበታልም ብለዋል፡ ፡

በመጨረሻም የውህደቱን ጥናት ኮሚቴው በ6 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል::

በነገው ዕለትም ለወደ ፊቱ ውህድ ፓርቲ በተቀረፀው ረቂቅ ፕሮግራም ላይ እንደሚወያይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ መናገራቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

(ኢ.ፕ.ድ)

————————————

ይህ አስገራሚና አስቂኝ የሆነ ቅንብር መታየት ያለበት

ይህ አስገራሚና አስቂኝ የሆነ ቅንብር መታየት አለበት🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Posted by Seyoum Teshome on Saturday, November 16, 2019

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.