ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በሠላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

19ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በሠላም መጠናቀቁን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ የሩጫ ውድድሩ በሚደረግባቸው መስመሮች መንገዶች ለውድድሩ ዝግ በመሆናቸው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለታገሱ የመንገድ ተጠቃሚ እግረኞችና አሽከርካሪዎች ምስጋናውን አቅርቧል።

ከዚህ ባለፈም በዋና ዋና የፍተሻ ቦታዎች ላይ ተባባሪ ለሆኑ የከተማው ነዋሪዎችና የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡ ለፖሊስ አመራርና አባላት የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

(ኢ.ፕ.ድ)

የታላቁ ሩጫ ድባብ

የታላቁ ሩጫ ድባብ

Posted by FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) on Sunday, November 17, 2019

(ኢ.ፕ.ድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.