ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሊወያዩ ነው!

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንባሩን በማዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በስድስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ከስምምነት ላይ መድረሱን ይታወቃል። በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት የግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል የቀረበውን ሃሳብ ተቃውመው ድምጽ የሰጡት የህወሓት አባላት ሲሆኑ ከቀድሞው የደህንነት ተቋም ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ በስተቀር የህወሓት አባላት መሳተፋቸውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ውሳኔው በተሰጠበት ጊዜ ስድስት ብቻ መቃወማቸው ድምጽ በሚሰጥበት ወቅት ከተሳታፊዎች መካከል “መውጣትና መግባት” ስለነበረ በአጋጣሚ የተፈጠረ መሆኑን አቶ አስመላሽ ገልጸው በውይይቱ ሁሉም እንደተሳተፉና “በፓርቲያቸው አቋም ጸንተው መውጣታቸውን” ገልጸዋል። በዚህ ወሳኝ ድምጽ በሚሰጥበት ጊዜ ሁለቱ አባላት ያለመገኘታቸው አጠያያቂ ቢሆንም አቶ ስመላሽ በጉዳየ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የድርጅቱ ውህደትን በሚመለከቱ ቀጣይ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ዛሬም ስብሰባውን የቀጠለ ሲሆን ውህደትን በተመለከተ የቀረበውን ሃሳብ የተቃወሙት የህወሓት አባላት ግን በዛሬው ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ አቶ አስመላሽ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለጻቸው ከእርሳቸው ጋር እንደሚነጋገሩ አቶ አስመላሽ ጠቁመዋል።

(ምንጭ- ቢቢሲ)

1 COMMENT

  1. ህውሀት ግራየገባው ድርጅት ነው

    1. ከተገነጠሉ የትግራይ ሬፐብሊክ የአመት ታክስ ገቢ 5 ቢሊዮን ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 45 ቢሊዮን ነው:: መገንጠል ማስፈራሪያነቱ የተበላ እቁብ ይሆናል::

    2. የአዲሱ ፓርቲ አባል ለመሆን ጫማ ስመው ቢመለሱ ልክ እንደ ሶማሌ ክልል የድምፃቸው ውክልና 6% ብቻ ይሆናል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.