ደቂቀ ዋለልኝ መኮንን በመንፈስ አባታቸው በኩል የተላለፈውን የሻዕብያ ፈጠራ ትርክት – አቻምየለህ ታምሩ

ደቂቀ ዋለልኝ መኮንን በመንፈስ አባታቸው በኩል የተላለፈውን የሻዕብያ ፈጠራ የኢትዮጵያ እውነት እንደነበር አድርገው ድርሰቱ የተጻፈበትን 50ኛ ዓመት ሲያከብሩ ሲሰነብቱ ዶክተርና ፕሮፌሰር የሚባሉት ሁሉ አንዴም እንኳ ምሑራዊ አእምሯቸው ተጣልቷቸው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የነበረውን የኢትዮጵያ ገጽታ የሚያሳየውን ከታት በታተመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጽሔት ላይ የሚታየውን አይነት የኢትዮጵያ መልክ፤ የዘመኑ መንግሥትና አየር መንገዱ ኢትዮጵያ ለአለም ያስተዋወቁበትን ታሪክ ሊያወሱት አይሹም!

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀመሮ ባለ ብዙ ቋንቋ፣ ባለ ብዙ ባሕል፣ ባለብዙ ሃይማኖት አገር ነበረች። ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚባሉትን የምትጨፈልቅና የምታጠፋ ቢሆን ኖሮ ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ በቆየው የመንግሥትነት ታሪክ ውስጥ ሁሉን ድምጥማጡን አጥፍታ ለወሬ ነጋሪ እንኳ የሚተርፍ አልነበረም። እውነታው ግን ብሔር፣ ብሔረሰብ የሚባሉትን ሰብስባ የኦሮሞ ገዢ መደብና ግራኝ ባካሄዱት ወረራና የማንነት ድምሰሳ ጨርሰው እንዳይጠፉ ያደረገችው ኢትዮጵያ ናት።

የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ መንግሥታት ጠብቀው ካቆዩዋቸው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መካከል ወደ ሰላሳ የሚጠጉት የአገራችን ቋንቋዎች የጠፉት የኦሮሞ የገዢ መደብ በገዳ ወታደራዊ ዘመቻ እየተመራ ባካሄደው ወረራ፣ ማፈናቀ፣ ማፍለስ፣ማንነትና ሃይማኖትን በግድ ማስለወጥ፣ መዋጥና የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ ነው።

ኢትዮጵያ «የብሔር ብሔረሰቦች እስር ቤት» የነበረችው የኦሮሞ ገዢ መደብ በገዳ እየተመራ በተከተለው የባህል ድምሰሳ፣ ከርስት ማፍለስና ቋንቋን የመጨፍለቅ ፖሊሲ ነበር። የኦሮሞ የገዢ መደብ ከባሌ በታች ተነስቶ ሲስፋፋ የተከተለው የመስፋፋትና የወረራ ፖሊሲው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ነበር። «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚለው የኦሮሞ የገዢ መደብ ሲወር ይከተለው የነበረው ፖሊሲ ትርጉም «ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ”» እንደ ማለት ነው።

ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚባሉት እስር ቤት የነበሩት «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ፖለሲ የሚያራምድ የኦሮሞ የገዢ መደብ ከርስታቸው ሲያፈልሳቸው፣ ማንነታቸውን በሞጋሳ ቀይሮ ሌላ ሰው ሲያደርጋቸውና ቋንቋቸውን ጨፍልቆ ገርባ ሲያደርጋቸው ነው።

ባጭሩ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች የሚባሉት እስር ቤት የነበረችው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል የገዳ ፖሊሲ ሲታወጅባት ነው። ዳግማዊ ምኒልክ ደርሰው ብሔር ብሔረሰቦች የሚባሉትን የኦሮሞ የገዢ መደብ ይከተለው ከነበረው ከዚህ ጨፍላቂ ወረራና የቋንቋና ባህል ድምሰሳ ፕሮግራም ባይታደጓቸው ኖሮ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የብዙ ነገዶች አገር ሳትሆን «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚለውን የኦሮሞ ገዢ መደብን የድምሰሳ ፕሮግራም መቋቋም የቻሉ የጥቂት ነገዶች አገር ብቻ ትሆን ነበር!

ከታች የታተመው ሰነድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 25ኛ አመቱን ባከበረበት ወቅት ያወጣው የአየር መንገዱ ሰላምታ መጽሔት ሽፋን ነው። በዚህ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በታተመው የአየር መንገዱ መጽሔት ላይ የወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ የብዙ ባሕሎች፣ ቋንቋዎች፣ ሃይማኖቶችንና ማንነቶች አገር፣ አቃፊና አካታች መሆኗን የሚያሳይ ነው።

2 COMMENTS

  1. አዎ አቻሜ አዎ አማራ ማንንም አልጎዳም::ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ( ተፈሪ መኮንን ጉዲሳ) ከሳቸውም በሗላ ኮሎኔል መንግስቱ ወልዴ አያና ዘራቸው ከሸዋ ኦሮሞ ሸኖ አካባቢ ነው:: አማራ ኦሮሞን ጨፍልቆ አያውቅም:: የአማራ መንግስት ትርክት አማራን አንገት አስደፍቶ ለመግዛት የተሸረበ ፖለቲካ ነው:: እዳሜ በአእምሮ ልዕልና መብለጥ ሲያቅትው የፈጠሩት ቅጥፈት ነው

  2. በሃገራችን ሰፊ ታሪክ ውስጥ አማራ በማንም ላይ በደል አድርሶ አያውቅም። ግን ልክ እንደ ወያኔና ሻቢያ የአማራን ህዝብ ስም ተገን ያደረጉ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በሰዎች ላይ በደል ፈጽመው ይሆናል። እነዚያ ሰዎች ፈጸሙት የሚባለው በደል ግን ሻቢያና ወያኔ በምድሪቱ ላይ ካዘነቡት መከራ ጋር ጭራሽ ማወዳደር አይቻልም። ለዘመናት ሃበሳውን የሚቆጥረው ሰፊው የአማራ ህዝብ ግን ሰው አቃፊ እንጂ በዳይ አይደለም። ለዚህም ሥራቸው ይመሰክራል። የ 1960 ዎቹ የፓለቲካ ትራፊዎችን የፈጠሩት የዘር ፓለቲካ ሻቢያን በአስመራ ወያኔን በአዲስ አበባ አለቃ አርጎ ከሾመብን ወዲህና እና ገና በበረሃ እያሉም ግፍ በአማራው ህዝብ ላይ እንደማያቋርጥ ጅረት ዝንተ ዓለም ያወርዱበት እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ሻቢያና ወያኔ በቅንጅት ጊዜ የጣለውን ደርግ አሽቀንጥረው ሲጥሉት ደርግ ገድሎ የቀበራቸውን እያስቆፈሩ በማውጣት የዋህ ህዝባችንን በሃዘን ደረት እያስመቱ በጎን ለጋ ልጆቻቸውን ሲገድሉና ሲያስሩ ሃብታቸውን ሲያጋብሱ ለዘመናት ኖረዋል። ዛሬ ከማሃል ሃገር ተሰርቆ በመቀሌና ዙሪያዋ የተከመረው ጥሬ ሃብት ማራገፊያ ገቢያ አጥቶ ቁጭ ብሎአል። በቅርቡ የተከፈተው የኤርትራው ግንኙነትም እንዲዘጋ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች ዋንኛው የወያኔ ተንኮልና ኤርትራን የተሰረቀና የተዘረፈ የእቃ ማራገፊያ ለማድረግ ወያኔዎች መከጀላቸው ነው። ሌባ ለሌባ ይተዋወቃልና ነቁባቸው። አንባቢ እንዲያስተውል የሚገባው አንድ ነገር አለ። ወደ ኋላ መለስ በማለት የሻቢያንና የወያኔን ማኒፌስቶዎች ለመረመረ ለህዝባቸው ለዘመናት ሲያስተምሩት የኖሩት “አማራ የመከራህ ሁሉ ምንጭ ነው” የንጉሱ ወይም የደርግ ወታደር ማለት አማራ ነው እያሉ ነው። በዚህ ክፋት የተቃመሰው የተማረም ሆነ ያልተማረ የሻቢያና የወያኔ የፓለቲካ አለቅላቂዎች ሃገር ለቀው በስደት ሲኖሩም ” አማርኛ ቋንቋ” አናውቅም። የጨቋኝ ቋንቋ ነው የሚሉት ለዛ ነበር ነውም። ፕ/ኢሳያስ ከአማርኛ ይልቅ በአረብኛ መናገር የሚመርጠው ሃበሻ መሆኑ ጠፍቶት አይደለም። ጥላቻው አጥንትን ዘልቆ በእርጅናውም ቀፍዶ ስለያዘው እንጂ! የኢትዮጵያ ገበሬ ግብር ከፍሎ ያስተማራቸው ኤርትርዊያንና የትግራይ ተወላጆች ሃገርን የማፍረስ ተንኮላቸውን የደገፉላቸውና መጠለያ የሰጦአቸው ሱዳን፤ ግብጽ፤ የዓረቡ ባህረ ሰላጤ ሃገሮች፤ ኢራን፤ ኢራቅ፤ ፓኪስታን የመንና ሌሎችም ናቸው። ለምን ቢባል ክርስቲያን የሆነ የአማራ መንግሥት ጋር ነው ጦርነት የገጠምነው በማለት ስለሚነግሯቸው ነው። የሊቢያው ጋዳፊ ቁጥራቸው የበዛ ዘመናዊ አጥቂ ፈጣን ጀልባዎችን ለሻቢያ ገዝቶ የለገሰው በዚሁ የፓለቲካ አሻጥር መሰረት ነው። እስልምናንን ለማስፋፋት ክርስቲያኖችን ማጥፋት! ዛሬ ግን እሱም ሃገሪቱም የለችም!
    የሻቢያና የወያኔ ተቀጥላዎች የኦሮሞ ብሄርተኞች ደግሞ ይባስ ብለው የሰው አንገት እየቀሉ፤ ቤ/ክርስቲያን እያቃጠሉ ይገኛሉ። የእኛ ብቻ ሃገር የሚለው ጠባቡ የኦሮሞ ስብስብ ጭራሽ ፓለቲካና የዓለም ታሪክ የማይገባው በቆንጨራው ብቻ የሚያምን እንደ እንቁራሪት መንጋ አንድ ድምጽ ሲያሰማ አብሮ የሚጮህ ፍጡር ነው። በየትኛውም የአለም ክፍል ግፍ ያልተሰራበት ቦታ የለም። ሰው የሁለተኛውን የዓለም ጦርነትና የሂትለርን የአይሁድ ፍጅት አድምቆ ያወራል እንጂ ከዚያ የከፋ በደል የደረሰባቸው አሉ። ለምሳሌ አርሜኒያን እንውሰድ። ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰባት ምድር። ስዎች ሃገራችው በቱርክ ተወሮ አዲስ አበባ ድረስ ጥገኝነት የጠየቁና የኖሩ፤ እንግሊዞች ህንድንና ፓኪስታንን ሲከፋፍሉ የሞተው የሰው ቁጥር ሰማይ ጠቀስ ነው። ዛሬ ነጻው ዓለም እየተባለ የሚጠራው አሜሪካ በነባር ህንዶች ላይ የፈጸመው በደል ተሰፍሮ አያልቅም። ረሃብ እንዲገላቸው እንስሶቻቸው፤ ጋልበው ከጥቃት የሚያመልጡበት ፈረሶቻቸው፤ ያበቀሉትና የከመሩት እህል ሁሉ እያወደሙ ነው መሬት ነጥቀው ነው ዛሬ አንድ ገበሬ አንዲት ሃገር የሚያክል ማሳ ይዞ የሚኖረው። ግን በኦሮሞ መስፈርት ያ ሰው መጤ ነው። የአሜሪካ ህንዶች ቋንቋቸው፤ ባህላቸው፤ መሬታቸው ነው የተቀሙት። የዘር ማጥፋት በደል በነጭ መጤዎች እንደ ተፈጸመ እንደ ኦሮሞው የአፍ ታሪክ ሳይሆን በመረጃ የተደገፈ ለመሆኑ የአሜሪካ ዝክረ መዛግብት ያሳያሉ። ግን ህንዶቹ የሰው አንገት እንቁረጥ ውጡልን አላሉም አይሉም። ቢሉም ትርፍ የለውም። እንደ በቀለ ገርባ ያለው የፓለቲካ ለፍዳዳ ግን ዘመኑን ሙሉ መከፋፈልና መገዳደልን እንደሰበከ ይሞታል። ያው አንገት አሳራጅን ጃዋርን ተክቷልና እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን የኦሮሞ ጠባቦችን! ለልጆቻቹህ የምታወርሱት የጥላቻ ዘር ሰው አብሮ እንዳይኖር የሚያረግ “ለእኔ ብቻ” የሚል የአውሬ ባህሪ ነው። የእነ ዋለልኝ መኮንን የፓለቲካ እይታ ተካፋዪችና ከሞት ተራፊዎች ዛሬ ኢትዪጵያ የምትባለው ሃገር ያለችበትን ሁኔታ ቢያዪ እንደ ሰጎን አንገታቸውን አሽዋ ውስጥ ይቀብሩ ነበር። ለዚያውም የሃበሻው የመጠላለፍ ፓለቲካ ቀድሞ ካልቀበራቸው! ጎበዝ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ፍዳ ገና አላለቀም። የአረብ ራቢጣ በቅርቡ ባወጣው መረጃ ” በአባይ ግድብ ዙሪያ ግብጽን እንደግፋለን” ይሉናል። ይህ አያስደንቀንም። ችግሩ ግን በዘርም ሆነ በሌላ አካኪ ዘራፍ በማለት ጫካ የሚገቡትን ሁሉ እያስታጠቁና እያሰለጠኑ የህዝባችንን መከራ የማያቋርጥ ያረጉታል። ገና በዙ ሃበሳ ይታየኛል። ባህታዊ አይደለሁም። በሃገራችን ነቢያትም አላምንም። ዝም ብሎ መዘላበድ ስለሆነ። እኔም ዘሬም ነብይነት የለብንም። ግን በመሬት ላይ ያለው እውነታ የሚያሳየው የጨለማ ጊዜ እንደሚሆን ነው። ቀን እያለ አንድ ነገር እናርግ። ጾም ጸሎት ምህላው ይቁም። የሰዎች አንገት እንዳይቆረጥ ለመከላከል ራሳችንን እናዘጋጅ። እየጸለዪ ከመሞት ሮጦ ማምለጥ ይመረጣልና! በቃኝ!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.