ሬዳዋ ‼እንደገና ሌላ ሀዘን‼

ገንደ ገራዳ የ 4 ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ  አማሩ ደረጀ ትላንትና በመንጋው በደረሰባቸው ድብደባ በወቅቱ ወደ ድልጮራ ሆስፒታል ተወስደው በህክምና ሲረዱ ቢቆዩም ከደረሰባቸው ከባድ ድብደባ የተነሳ ዛሬ ማለዳ አርፈዋል።

ወ/ሮ አማሩ በብሔራቸው #ጉራጌ በሐይማኖታቸው #ፕሮቴስታንት ቢሆንም እሳቸው ግን ከነልጆቻቸው አንድም የዘረኝነት አመለካከት የሌለባቸው በድሬዳዋዊ ስነልቦና የኖሩና ልጆቻቸውንም በዚሁ ያሳደጉ ደግ ምርጥ ኢትዮጵያዊት እናት ነበሩ።

ሀዘኑን የበለጠ ከባድ የሚያደርገው ወ/ሮ አማሩ ደረጀ ትንሿ ልጃቸው ከቀናት በፊት #ከሉሲ_ኮሌጅ ስትመለስ በመንጋው በደረሰባት ድብደባ ለከፍተኛ የህክምና እርዳታ ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስዳ በህክምና እየተራዳች ሲሆን እናቷም ወ/ሮ አማሩ ልጃቸውን ከድሬዳዋ አዲስ አበባ ድረስ እየተመላለሱ በደሀ ጉልበታቸው በእናት አቅማቸው እያስታመሟት የልጃቸውን መዳን እንደናፈቁ ልጃቸውን ለአልጋ ቁራኛ የዳረገው የመንጋ ፍርድ እሳቸውምን የሞት ሰለባ አድርጓቸዋል። በእውነት በሁሉም የሀገራችን ክፍል በሁሉም ብሔር ዘርን/ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመረዳት አይደለም ለመስማት እንኳን ከአቅም በላይ ሆኗል ነብስ ይማር!!

ገላዬ በዛብህ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.