ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ወይስ ዶ/ር ቴዎድሮስ? ቢቢሲ ቀጣዩ የሀገሪቱ መሪ ስለሚሆነው ሰው ከወዲሁ ይተነብያል

Current Prime Minister, Hailemariam Desalegn (L), is favourite to retain the post but faces competition from leading challengers Debretsion Gebremikael (C) and Tewodros Adhanom (R)
Current Prime Minister, Hailemariam Desalegn (L), is favourite to retain the post but faces competition from leading challengers Debretsion Gebremikael (C) and Tewodros Adhanom (R)

ቢቢሲ ስለከትናንት በስቲያው አምስተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ከዘገቡት ታላላቅ ሚዲያዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡   ቢቢሲ(BBC)

በዚሁ ዘገባው የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት በአንድ ሳምንት ውስት የሚታወቅ እንደሆነ ቢገልጽም እንኳን ገዢው ኢህአዴግ ፓርቲ በዘንድሮው ምርጫ ያን ያክል ፉክክር እንደማይገጥመውና ማሸነፉም ከወዲሁ የተተነበየ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ አባላትን፣ መራጮችንና የፖለቲካ ምሁራንን ተዟዙሮ የጠየቀው ይህ ዘገባ የኢህአዴግ ማሸነፍን የሚደግፍ አስተያየቶቻቸውን ያስነብበናል፡፡ ከዚህ ውጪ ኢህአዲግ ካሸነፈ የሀገሪቱ መሪ ማን ይሆናል የሚለውን ለማጠያየቅ የሞክረው ዘገባው የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተቀዳሚ ተመራጭ ይሆናሉ የሚለው እንዳለ ቢሆንም ሌሎችም እንደ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም እንዲሁም በምክትል ጠቅላይ ሚነስትር ማእረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪውና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በፓርቲው ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑ እጩዎችና አቶ ሀይለማሪያምን ተፎካካሪ ይሆናሉ ከሚባሉት ውስጥ ይጠቀሳሉ ሲል ነው ያተተው፡፡