የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ በሠላም ተጠናቀቀ

የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ገለጹ።

አቶ ርስቱ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ የሕዝበ ውሳኔው ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ ዛሬ ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ምርጫ በተቀመጠለት ሠዓት ተጠናቋል።

ምርጫው ውጤታማ እንዲሆን የክልሉ መንግሥት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከዞኑ አስተዳርና የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን አንስተዋል።

“ሂደቱ በሠላማዊ ሁኔታ ተጠናቋል” ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ የክልሉና የፌዴራል ፀጥታ መዋቅር ከሰራው ስራ ባሻገር የሲዳማ ብሄር የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ወጣቶች ለተጫወቱት ሚና ምስጋና አቅርበዋል።

የሕዝበ ውሳኔ ውጤቱ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚገልጸው መሰረት ቀጣይ ስራዎች እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

ቀጣይ ተግባራትን ሕዝቡ ተረጋግቶ በተለይም የሕዝቦችን አብሮናትና ወንድማማችነት በሚያጠናክር፣ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያጎለብት መንገድ ሠላማዊ እንዲሆንና ይኸው ቅንጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ክልሉን እየመራ ያለው ድርጅት ደኢህዴን የሕዝቡ ጥያቄ በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲመለስና ምርጫ እንዲካሄድ አቋም ወስዶ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው በቅደመ ዝግጅትም የክልሉ መንግሥት ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ምርጫው ዴሞክራዊያዊ እንዲሆን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ገለጻ ሲደረግ ነበር ያሉት አቶ ርስቱ፤ ይህም ውጤታማ እንዲሆን አድርጓል ነው ያሉት።

ኢዜአ

1 COMMENT

  1. We would like to congratulate the Sidama people for their achievements. We would also like to take this opportunity to plead with the Sidama people to give us (the ethnic Gedeo Ethiopians) a small piece of the Sidama State’s land so we ethnic Gedeos can establish an independent Gedeo State.

    As you know currently we the ethnic Gedeo people are displaced remaining not to.be able to return to our former lands since ethnic Guji people took our homeland from us by force rendering us to be stateless with nowhere to establish.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.