የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለቀጣዩ ምርጫ የምርጫ ማኔፊስቶ ከማዘጋጀት ጀምሮ የክልል እና የፌደራል ፓርላማ ተመራጭ እጩዎችን በመመልመል ላይ መሆኑን አስታወቀ

ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በአገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት የፖለቲካ ስራችንን ለማከናወን የፈጠረብን ተጽእኖ ቀላል ባይሆንም ለምርጫው ግን እየተዘጋጀን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

እስካሁን በነበረው ጊዜ ፕሮግራሞቻችንን ለህዝቡ ለማስተዋወቅና ለምርጫው በሙሉ አቅማችን እንዳንዘጋጅ እነዚህ የጸጥታ ጉዳዮች ገድበውን ቆይተዋል፤ ሆኖም ከዚህ በኋላ ግን ትኩረታችንን ምርጫው ላይ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ የፓርቲው በርካታ አባላት ከሰኔ 15ቱ ኹነት ጋር በተያያዘ ለእስር መዳረጋቸው የሰው ኃይላችሁ እንዲመናመንና ፓርቲያችሁ እንዲዳከም አላደረገውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ደሳለኝ “የአባሎቻችንን መታሰር አጥብቀን የምንቃወመውና ጫና ያደረገብን ጉዳይ ቢሆንም የፓርቲያችንን መሰረት የሚያናጋ ግን አይደለም፤ አብን በርካታ አባላት አሉት ዓላማችንም ትልቅ ነው” ብለዋል፡፡ የምርጫ ማኒፌስቶ በማዘጋጀት ዝርዝር ፖሊሲዎችንና ፕሮግራሞችን ማውጣት፤ ለክልል ምክር ቤትና ለፌዴራል ፓርላማ እጩ የሚሆኑ አባላትን በማጣራት ማቅረብ ፓርቲው በቀጣይ የሙሉ ጊዜ ስራው አድርጎ የሚሰራባቸው ጉዳች መሆናቸውንም ዶ/ር ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.