የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት በዋሽንግተን ዲሲ ስኬታማ የውይይት መድረክ አደረገ

ባለአደራው በሀገር ቤት ለሚያደርገው ሰላማዊ ትግል በዉጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ከፍተኛ ድጋፍ እና አጋርነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል፡፡ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ወደ ፖለቲካ ፓርቲ እንዲያድግም ከተሰብሳቢው ጥያቄ ተነስቷል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የህዝብ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄ ምክር ቤቱ ተነጋግሮ እንደሚወስን አቅጣጫ ጠቁሟል፡፡ በጃዋር የሚመራው ራሱን ቄሮ በማለት የሚጠራው አክራሪ ቡድን ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ የማይወክል ጨፍጫፊ ሃይል በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ በአቋም መግለጫ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ ቀርቧል፡፡ በቀጣይ አገራዊ ምርጫ ባለአደራዉ አዲስ አበባና ዙሪያው ሙሉ ለሙሉ እንዲቆጣጠር ኢትዮጵያን የማዳን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ በእልህ ዲያስፖራው ከጎኑ እንደሚቆም ቃል ገብቷል፡፡

በወይይቱ የገቢ ማሰባሰቢያ የተደረገ ሲሆን
የእምዬ ሚኒሊክንና የኢትዮጵያዉያኖች እናት የጣይቱን ምስል የያዘዉ ስእል 90.000 ዶላር በኢትዮጵያ ወደ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶሺ በጨረታ ተሽጧል። ታሪክ ስትሰራ ለሀገርህ በጎ ነገርን ሰርተህ ስታልፍ ትዉልድ ይዘክራል፡፡ ስምህ ሁልጊዜም ከመቃብር በላይ እንደ ኮከብ ይደምቃል፡፡

ባለአደራው
ድል ለዲሞክራሲ
አዲስ አበባ

ባላደራ – ባልደራስ – አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያውያን ላብ፣ ጉልበት፣ እውቀት የፈሰሰባት ለአንድ ብሄር ተላልፋ የማትሰጥ የሁላችንም ከተማ ናት!
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እንብርት ናት!!

Posted by Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ on Sunday, November 24, 2019

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.