በኦሮሚያ ክልል ትናንት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በትናንትናው እለት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ።

የትራፊክ አደጋዎቹ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ፣ ከመቱ ወደ አዲስ አበባ እና ከቢሾፍቱ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሱ ናቸው።

  በዚህም ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ 20 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ሀይሩፍ በመባል የሚጠራ ተሽከርካሪ በኤጄሬና ሆለታ ከተሞች መካከል ከሲኖ ትራክ ጋር ተጋጭቶ አደጋ ደርሷል።

በትራፊክ አደጋው የ18 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፥ በሌሎች 2 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱን የአምቦ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ በትናንትናው እለት ከመቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ኦዳ ባስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋም የሰዎች ህይወት አልፏል።

አውቶብሱ ምስራቅ ወለጋ ዞን ሌቃ ዱለቻ ወረዳ ገተማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተገለበጠ ሲሆን፥ በአደጋው የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ21 ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጣን ያለው ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም ትናንት ምሽት ከቢሾፍቱ ከተማ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ፥ 14 ሰዎች ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በአርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በአዋሾ ቀበሌ ሰዎችን አሳፍሮ ሲዷዝ የነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋም የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳም አንድ አይሱዙ ተሽከርካሪ ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪን በመግጨት ባደረሰው ጉዳትም በባጃጁ ውስጥ የነበሩ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል።

በተመሳሳይ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደኣ ወረዳ ኡዴ ደንካካ ቀበሌ ትናንት ሌሊት በደረሰው የትራፊክ አደጋ በአንድ ሰው ላይ የሞት በ18 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በአርሲ ዞን ዲገሉ እና ጢጆ ወረዳ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እግረኛን ገጭቶ በፈረሱ ላይ የነበረው ሰው እና የፈረሱ ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

በትራፊክ አደጋዎቹ በንብረት ላይም እስከ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ጉዳት መድረሱ ነው የተነገረው።

ኤፍ.ቢ.ሲ

1 COMMENT

  1. This is the result of giving away (selling) drivers licenses in Oromo region. One can literally buy drivers license without even touching a car!!

    Most of the car accidents in Addis are caused buy Oromo plated cars!!

    This is the prize for corruption in Oromo region!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.