በዛጉዬ ዘመን የላሊበላ አይነት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የተፈለፈሉባቸው ጥንታዊ የኢትዮጵያ አውራጃዎች! – አቻምየለህ ታምሩ

ባሌ፣ ኢሉባቦር፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ ወዘተ የኦሮሞ ገዢ መደብ በ1514 ዓ.ም. ከባሌ በታች ተነስቶ ነባሮቹን ባለርስቶች አጥፍቶና ማንነታቸው ቀይሮ የባሕል ጄኖሳይድ በማካሄድ አውራጃዎቹን በወረራ ከመያዙ በፊት የአባቶቻችን ባድማ ነበሩ የምንለው ዝም ብለን አይደለም።

ከታች የታተመው ታሪካዊ ካርታ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስትና በፕሮፌሰር ጆፍሬይ ላስት በ1961 ዓ.ም. «A History of Ethiopia in Pictures» በሚል ካታተሙት መጽሐፍ ገጽ 16 የተወሰደ ነው። ካርታው የላሊበላ አይነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በላሊበላ ዘመን የተፈለፈሉባቸውን የኢትዮጵያ አውራጃዎች በካርታ ላይ የት እንደሚገኙ የሚያሳይ ነው።

በካርታው ላይ እንደሚታየው ግራኝ አሕመድ «የባሌ አበሾች ሰይጣኖች ናቸው» ሲል የመከሰረላቸው የባሌ ነጋሹ የአማራ ተወላጅነት ያላቸው የራስ ተክለ ሃይማኖት ምድር የሆነው ባሌ፤ ከግራኝ አሕመድ ጋር ሲዋጉ ለአገራቸውና ለሃይማኖታቸው የወደቁት የባሌ ተወላጆች የነ ራስ ነብያትና የነ አዛዥ ፋኑኤል ርስት የሆነው የባሌ ምድር ጎባ አቅራቢያ በላቢበላ ዘመን የተፈለፈለ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የሚገኝበትና ከኦሮሞ በፊት የኢትዮጵያውያን አጽመ ርስት ነበር።

ከባሌ በተጨማሪ ከፋ፣ ወሊሶ፣ አገረ ሕይዎት [የአሁኑ አምቦ]፣ አዲስ አበባና ዙሪያው የኦሮሞ ገዢ መደብ ከባሌ በታች ተነስቶ ነባሮቹን ባለርስቶች እያፈለሰ፣ የአካባቢዎችን ስም እየቀየረና የባሕል ድምሰሳ እያካሄደ እንደ ዋርካ ከመንሰራፋቱ በፊት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን የተፈለፈሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የሚገኝበት የኢትዮጵያውያን ርስት ነበሩ።

አቻምየለህ ታምሩ

2 COMMENTS

 1. What can we say about this meticulous citizen? as he said it, he is at the forefront to correct the distorted history and differentiate fact from tales. When Achamyelh writes something he doesn’t say someone told me unless the person is alive, on the other hand, his rivals the so-called Oromo elites prefer to say ” somebody told me” to defend their argument. Hezqeal Gabisa is known for this style of argument.
  I advise citizens to open a file under ACHAMYELH and store his articles these days he is the source of knowledge.
  Long live Achamyelh, you are great, your parents were right when they give you the name that equates your ability.

 2. Comment:ንጉሥ ንጉሥ ነኝ! አይልም ዘሩ ይናገራል::
  ኦሮሞ ንጉሥ ነኝ! አይልም ሀገር ይናገራል::
  አላጣም አንጋሹን ሶማሊ ዘመዱ አለ ከጎኑ::
  ትግሬ አፋር መሳይ ያውቃል የቀንድ ሐረጉ::
  ንጉሥ ነኝ አማራ ይገለጥ የስር መሰረቱ::
  አጋውን አላወቁም የአማራ ማንነቱ::
  ጎጃም ወሎ ጎንደር የሉም ከመስራቱ::
  ንጉሥ ነኝ ላሊበላ ሰማን ከዎለዬ ጎጃም ነው አባቱ የረገመውምክንያቱ ዛሬም አያውቁም ምን አባ!ማን አባቱ
  ቄስ ከመቼነው ንጉሥ የሚሆነው ከሰር መሰረቱ::

  ጎባና ሐዳሞ እና የሸዋ ቤተሰብ ይታወቃል::
  ሃይማኖት ብሔር አይሆነም::
  ቤተ ክርስቲያን የአማራ አይደለም::ክርስትያን ኦርቶዶክስ አይደለም::ኦርቶዶክስ ነው ክርስትያን:: ኦርቶዶክስ እውቅና የለውም ::
  ግራኝ አህመድ ወደ ሰሜን ነው:: የዘመተው አንጂ ሚእራብ አይደለም:: የተዋጋው ከ ቴድሮስ አንጂ ከ ተክለ ሃይማኖት አይደለም::የገዛው ለ 27ዓመት አትዮጵያን አማራ የት ነበረ?መተማ ላይ አልቅሰው ዓለም የረዳቸው::ሁለተኛ በ 1977 በ ኦጋዴን war አልቅሰው ነው::በሶፌትህብረት ሊቢያ,ምስራቅ ጀርመን,እስራኤል, ኩባ እና ሰሜን ኮርያ እርዳታ ነው የተረፋጁ

  ሰለዚህ ውሸታም!ነህ

  መደምደሚያ;- አኢትዮጵያ ከኛ የምትፈልገው?ኦሮሞ ሶማሊ አማራ አፋር ትግሬ ሙስሊም ክርስትያን የሁድ ሁሉም በእኩል አይን ልዩነታችንን አስወግደን ከጠላት እንጠብቅ:: ሰዎች ጥላቻ መልመድ አለባቸው:: መውደድ እንዲቺሉ::ለሰዎች መዋደድ ነው ጥሩ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.