የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና ውሳኔ ምን ኣሳየን ፣በቀጣይስ ምን ይደረግ? – ኣክሊሉ ወንድአፈረው

ኣክሊሉ ወንድአፈረው ethioandenet@bell.net
ህዳር 14, 2012  (ኖቨንበር 24,2019)

የራሴ ኣስተዳደር ይገባኛል ሲል የኖረውና በዚህም የተነሳ ባለፉት 28 ኣመታት ከኣንዴም ሁለት ሶስት ጊዜ በህወሀት መራሹ መንግስት ኣጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የተፈጸመበት የሲዳማ ሀዝብ ኣነሆ ፍላጎቱን  በድምጹ ኣንዲገልጽ ሆኖ ከ98% በላይ የሆነው ድምጹን የሰጠው የክልሉ ነዋሪ ሲዳማ ራሱን የቻለ ክልል ኣንዲሆን መወሰኑ ተገልጿል፤፥

ሰለ ክልል ሲነሳ በብዙወቻችን ውስጥ የሚቀሰቅሰው ስሜት ኣጅግ ጠንካራ ነው፤፥ ይህ የሚሆንበት ራሱን የቻለ በቂ ምክንያት አለው፥፥ ታዲያ ከስሜትና ትርክት ባሻገር የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና የውሳኔ ሂደት ምን ኣሳየን? በቀጣይስ ምን መደረግ ይኖርበታል ከሚል አይታ በመነሳት የሚከተሉትን ነጥቦች ኣቀርባለሁ፤፥

  1. የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ኣጅግ ግዙፍ በሆነ የህዝብ ቁጥር (98.5%) መደገፉ በህወህትና በኣጋሮቹ የተዋቀረው ክልል ከህዝብ ፍላጎት ጋር ኣንደማይጣጣም፡ በኢትዮጰያ ማኣቀፍ ስር ትርጉም የሚስጥ አዲስ የኣስተዳደር ኣወቃቀር መኖር ኣለበት ብለው የሚታገሉ ዜጎችን ፍላጎት ተደጋጋሚ (የህውሀት ወይም ሌላ) ጭፍጨፉ ሊያንበረክከው ኣንደማይችል ኣሳይቶናል፤
  2. ኣሁን ያለው የክልል ኣወቃቀር ይቀየር ማለት ፌደራሊዝም ይፍረስ ወይም ኣሀዳዊ ስርአት ይምጣ ማለት ኣንዳልሆን በማያሻማ ሁኔታ አረጋግጧል
  3. ፌደራሊዝም ትርጉም ያለው ኣንዲሆን ከተፈለገ መንግሰትን ወደ ህዝብ ሊያቀርበው የሚያስችል ኣስተዳደራዊ ኣወቃቀርን ተግባራዊ ማድረግ ኣንደሚያስፈልግ ኣመላክቷል፤
  4. ኣሁን ያለው ህገ መንግስት ይቀየር ወይም ይሻሻል ማለት “ሀገር ያፈርሳል ህዝብ ኣንዲተላለቅ ያደርጋል ” ወዘተ የሚለው ትርክትና ማስፈራሪያ ፣ ውሀ የማይቋጥር ኣንደሆነ ኣሳይቷል፥
  5. በኢትዮጰያ ማኣቀፍ ውስጥ ራሳችንን የማስተዳደር መብታችን ይክበር ብለው የተነሱ ሁሉ ጥያቄያቸው በስላማዊና በሀጋዊ መንገድ ሊታይና ሊፈታ ኣንደሚገባና ኣንደሚቻልም ኣመላክቷል
  6. ራስን የማስተዳደር ጥያቄን ሀገር ኣፍራሽ ሀይሎች ሊጠቀሙብት ኣንደሚጥሩና በነዚህ ኣጥፊ ሀይሎች ኣንዳይጠለፉም ጥንቃቄ መውሰድ ኣጅግ ኣስፈላጊ ኣንደሆነ፤ ጠቁሞ ኣልፏል
  7. ሲዳማ ራሱን በቻለ ክልል ለመተዳደር መጠየቁ “ኢትዮጰያዊነትን ለማዳክም ሊያግዘን ይችላል” ብለው ነገር ሲያራግቡ ቅራኔን ሲያበረታቱ ለቆዩ ሁሉ የሲዳማ አመራር ከምርጫው በፊትም ሆነ በኻላ የሲዳማ ሕዝብ በኢትዮጰያዊነቱ የሚኮራ ሲዳማም በውስጥዋ የሚኖሩ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጰያውያን ሁሉ ኣንደሆነች በማያሻማ ቋንቋ ማሳወቃቸው ጽንፈኞችን ኣንገት ያስደፋ መሆኑን ኣሳይቷል
  8. ህገ መንግስቱን ለማሻሻልም ሆነ ክልሎችን በተሻለ ሁኔታ ለማዋቀርና ፌደራሊዝምን በትክክል ተግባራዊ ለማድረግ ህዝባችን ብቃቱም ጽናቱም ኣንዳለው ኣሳይቷል፤
  9. ኣሁን ያለው ክልል መቀየር ኣለበት የሚለው ጥያቄ የትላንቱን ስርኣት የሚናፍቁ ጥቂት ስዎች ጥያቄ ኣንዳልሆነ ከሚገባው በላይ ግልጽ በሆነ መልክ ኣሳይቷል፤

ኣሁን ከፊት ለፊት የተደቀነው ፈተና ኣስካሁን የተመለከትነው  በጎ ነገር ኣንዲቀጥል ይሆናል ወይንስ በየቦታው ወደ ተመለከትናቸው ኣግላይና ኣፍራሽ ኣዝማሚያ ያጋድላል፣ ሲዳማ ለሁሉም የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ስላምና፣ ብልጽግናን ያጎናጽፋል፣ ኣድልኦን ያስውግዳል ወይስ የጥቂት ልሂቃንና የተወስነ የህብረተሰብ ክፍል  ብቻ መጠቀሚያ ይሆናል? የሁሉም ዜጎች ሙሉ መብትስ ይከበራል ወይስ ኣዲስ ኣምባገነንና ተጨማሪ ኣድጋ ብቅ ይላል የሚሉትና ሌሎችም ናችው፤፥

በዚህ ኣንጻር  ሲዳማ የሁሉም ነዋሪዎችዋ ኣንደሆነች  ሁሉን ኣቃፊነትን፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን፣ በተግባር፣ በማሳየት ፊደራላዊ ኣወቃቀርን ወደህዝብ የቀረበና የህዝብን ፍላጎት የሚያረካ በማድረግ ወዘተ  ሲዳማ ህዝብን ያስመረረው  “የኣኛና የኣነርሱ ” ቀጣይ የንትርክ ሜዳ ሳይሆን ኣስካሁን ካየነው የተሻለ የኣዲስ ገንቢ ጉዞ ጅምር ምሳሌ ለማድረግ ለክልሉ ኣመራር ለፌደራል መንግስቱና ለነዋሪዎች ሁሉ  ኣዲስ ኣድል ተፈጥሮላቸዋል፤፥

በኣሁኑ ስኣት የሲዳማ ነዋሪዎችም ሆኑ የመላ ሀገራችን ዜጎች ኣንዱ ትልቅ ስጋት በተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችና ኣምነት ተከታዮች መህል ያለውን ኣንድነት ማዳበር ግጭቶችን ማስወገድ የጽንፈኞችን ተጠናክሮ ሊመጣ የሚችል ተጻኣኖ መቋቋምና ማክሽፍ የመቻልና ያለመቻል ጉዳይ ነው፤

ይህን ታላቅ ስጋት ማስወገድና ተስፋን ማረጋገጥ ለመንግስት ብቻ የሚተው ተግባር ሳይሆን ከኣዲሱ ክልል ነዋሪዎች የተውጣጣ ህዝብን መኣክል ያደረገ “የኣብሮነትና የሰላም” ኮሚቴወችን በኣስቸኻይ በመመስረት በዜጎች ተሳትፎ ኣንድነትን ለማጠናክር፣ የኣካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ኣፍራሽ ተግባሮቸን ለመከላከልና ለማስውገድ በኣቅድና በቀጣይነት መስራት ኣስፈላጊ ነው፤፥  ይህንን ተግባር ፈር ለማስያዝ ደግሞ የክልሉ መንግስት ግልጽ የሆነ ህግ ቢደነግግ  ለጉዳዩ ተጨማሪ ጥንካሬን ሊሰጠው ይችላል፤፥ ዜጎችም በግልም በቡድንም  ሙሉ ትሳትፎን በማሳየት የተሻለ ነገር ማድረግ ኣንደሚቻል በተግባር ማሳየት የሚጠበቅባቸው ሃላፊነት ነው፥፤

የህገራችን ብሂል ኣንደሚያስተምረን ካያያዝ ይቀደዳል፤ ካነጋገር ይፈረዳል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.