ወጣት አዲሱ ካሳሁን ከሃገር ወጣ!

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና ምክትል ፋይናንስ ሀላፊ የነበረው ወጣት አዲሱ ካሳሁን በስርዓቱ ጫና ምክንያት ከሃገር ለቆ መውጣቱን ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ። እውነተኛው አንድነት በህገወጥ መንገድ እንዲፈርስ ከተደረገ ወዲህ የስርዓቱ የደህንነት ኃይሎች በእውነተኛው አንድነት አመራሮች ላይ እስር፣ ወከባ እና ክትትል እየተካሄደባቸው መሆኑ ተደጋግሞ የተዘገበ ጉዳይ ነው።

ወጣት አዲሱ ካሳሁን ቀደም ሲል የአዲስ አበባ መዋቅር የአንድነት ስራ አስፈፃሚ ሆኖ የሰራ ሲሆን፤ በተጨማሪም አንድነት በአዲሰ አበባ ጠንከራ መዋቅር ከነበራቸው አከባቢዎች አንዱ የነበረው ወረዳ 24 ሰብሳቢ ሆኖ አገልግለዋል። በአንድነት ውስጥ አዲስ የአመራርና የአስተሳሰብ ለውጥ ለማመጣት ከተነሳው ኃይል ጋር በመሰለፍና የራሱን ወረዳ በማስተባበር ኢንጂነር ግዛቸው ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ እና ፓርቲው በለውጡ ኃይል እንዲመራ በማድረግ በኩል ወሳኝና ከፍተኛ ትግል ካደረጉ የአንድነት ወጣቶችና የወረዳ አመራሮች አንዱ ነበር።

11258327_826820170736252_4326557521164834528_nአንድነት በስርዓቱ ፖለቲካዊ ውሳኔና በምርጫ ቦርድ ደባ ለህገወጦቹ የስርዓቱ ተላላኪዎች እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስም፤ አዲሱ ካሳሁን በወረዳው እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የፓርቲው መዋቅር፤ በፓርቲው የፋይናንስ ዘርፍ ጊዜውን፤ ጉልበቱንና እውቀቱን ሳይሳሳ የሚቻለውን ሁሉ አድርጓል፤ ፓርቲው የተሻለና ጠንካራ እንዲሆን ታግሏል። አንድነት በዘንድሮ ምርጫ እንዳይወዳዳር የተደረገውና እንዲፈርስ የሆነው በሁሉም አከባቢዎች እንደ አዲሱ ያሉ ጠንካራ አመራሮችና አባላት የነበሩት ፓርቲ በመሆኑ ነው።

ለማነኛውም፤ ይሄ የትግል ጓዳችን በሄደበት ሁሉ ቀና ይሆንለት ዘንድ ከልብ እንመኝለታለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.