ሰበር ዜና … በሳምንቱ ሌላ የአጥፍቶ አጥፊ ጥቃት በሳውዲ ደማም – ነቢዩ ሲራክ

* ጥቃቱ በአኑድ መስጊድ ለአርቡ እኩለ ቀን ጸሎት የተሰበሰቡትን ለማጥቃት የታለመ ነበር ተብሏል
* ፍንዳታው ከመስጊዱ መኪና ማቆሚያ በመፈንዳቱ አደጋው ሊቀንስ ችሏል
* በጥቃቱ አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካታዎች ቆስለዋል ፣ ንብረት ወድሟል
* አጥፍቶ አጥፊው የሴት አበያ ለብሶ ተደብቆ ማለፉ ተጠቁሟል

ባሳለፍነው ሳምን ከደማም የቅርብ ርቀት በምትገኘው በቃጢፍ ውስጥ ባንድ መስጊድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የ 21 ሰዎች መገደላቸውና ከመቶ በላይ መቁሰላቸው አይዘነጋም ! ለጥቃቱ አይ ኤስ ወይም ደአሽ ተብሎ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን ኋላፊነት የወሰደ ሲሆን የሳውዲ መንግስ የአሸባሪ ቡድኑን መረብ ለመበጣጠስ መዛቱ ይጠቀሳል ። ያም ሆኑ የአልቃኢዳን ተደጋጋሚ ጥቃቶች በመመከት የሚታወቁት የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች የደአሽን ጥቃት ሲደጋገም መስተዋሉ ብዙዎቻችን ያስገረመ ሆኗል ! በተለይም ባሳለፍነው ሳንንት የ21 ሰዎች ህይወት የተቀጠፈበት የቃጢፉ ጥቃት የሳውዲን መንግስትና ህዝብ አስቆጥቶ ለበቀል በተዛተበት ባለበት ወቅት ይህ መሰሉ ጥቃት መፈጸሙ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል !

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓም