መንግሥቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙት የአገር ክህደት! – አቻምየለህ ታምሩ

መንግሥቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ የኢትዮጵያ አርበኞችን በግፍ ከመረሸናቸው ባሻገር በኢትዮጵያም ላይ የአገር ክህደትም የፈጸሙ ነበሩ። እነ መንግሥቱ ንዋይን ሲያሞካሹ የኖሩ የ ያ ትውልድ ፖለቲከኞች ስለፈጸሙ የአገር ክህደት ወንጀል ሊነግሩን አይፈልጉም።

ከታች የታተመው ታሪካዊ ሰነድ መንግሥቱና ግርማሜ ንዋይ ስዒረ መንግሥት ባደረጉበት ወቅት እርዳታ እንዲያደርጉላቸው ወደ አዲስ አበባ ስለጋበዟቸው በግብጽ መከላከካ ሚኒስቴር ወታደራዊ ስለላ ምክትል ሚኒስቴር የተመራ 15 አባላት ያሉት የግብጽ ወታደራዊና የስለላ ቡድን ማምነት የሚያወሳ ነው።

ስዒረ መንግሥቱ ከከሸፈ በኋላ በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ የቆዩት እነዚህ እነ በነግርማሜ ግብዣ በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ከካይሮ የመጡት በግብጹ ወታደራዊ ስለላ ምክትል ሚኒስቴር የተመሩት የግብጽ ወታደሮችና እያበረሩ ይዘዋት የመጧት የጦር አውሮፕላን ለፈጸሙት ወንጀል ተገቢውን ወታደራዊ ቅጣት ከተቀጡ በኋላ ተዋርደው፣ ጸጉራቸውንና ጺማቸውን እንዳንጨፈረሩ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲባረሩ ተደርገዋል።

እንግዲህ! ያ ትውልድ ሲያሞካሻቸው የኖሩት እነ ግርማሜ ንዋይና መንግሥቱ ንዋይ የግብጽን መንግሥት ወታደራዊ ልዑክ አዲስ አበባ ድረስ ጋብዘው፣ ግብጽ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ተዳፍራ በኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት እንድታደርግ ያስቻሉትን በአገር ክህደት ወንጀል መከሰስ የሚገባቸውን ከሀዲዎች ነው! ያ ትውልድ ንጉሡን ባንዳዎችን ሾሙ እያለ እያወገዘ ኢትዮጵያን የከዱትን ባንዶቹንና አርበኞችን የፈጁትን እነ መንግሥቱን ንዋይን ግን ሲያጀግን የኖረ ግብዝ ትውልድ ነው።

በነገራችን ላይ እነዚህን በግብጹ ምክትል ሚኒስቴር እየተመሩ እነ ግርማሜ ንዋይን ለማገዝ ከካይሮ እየበረሩ የመጡ የግብጽ ወታደሮች ከነ አውሮፕላናቸው የማረከው የፈጥሮ ደራሽ ፖሊስ አዛዥ የነበረው ኮሎኔል [ኋላ ጀኔራል] ታደሰ ብሩ ነበር። ይህንን እውነት ጀኔራል ታደሰ ብሩ ራሱ ለጀኔራል መርዕድ መንገሻ በወቅቱ በጻፈው ሪፖርት ላይ አረጋግጧል። ጀኔራል ታደሰ ብሩ መፈንቅለ መንግሥቱን እንዴት እንዳከሸፈና እነ ግርማሜን ለመርዳት የመጡትን ግብጾቹን ከነ አውሮፕላናቸው ማርኮ ለምድር ጦር አዛዡ ለጀኔራል ከበደ ገብሬ እንዴት እንዳስረከበ በማተት የጻፈውን በእጃችን የሚገኘውን ይህንን ሪፖርት ትውልድ ይማርበት ዘንድ ወደፊት እናትመዋለን! ጀኔራል መንግሥቱ ንዋይም ራሱ ፍርድ ቤት ቀርቦ በሰጠው ቃል ላይ የግብጽ የወታደራዊና የስለላ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የመጣው መፈንቅለ መንግሥቱ እንዲሳካ የወታደራዊ፣ የስለላና ኢኮኖሚያዊ እርዳታ ሊያደርጉላቸው እንደሆነ አምኗል። ጀኔራል መንግሥት የሰጠው ቃልም እናቀርባለን!

5 thoughts on “መንግሥቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙት የአገር ክህደት! – አቻምየለህ ታምሩ

 1. The Egypt military were sent by United Nations (UN) and the Organization of African Unity (OAU) to keep the peace since the heavy handed Ethiopian security apparatus killed many civilians during this time known in history as YEGIRGIRU GIZE .

 2. ከላይ አቶ ብርሃኔ ያለው መረጃ የለሽ ነው። በታህሳሱ ግርግር የዛሬ 60 ዓመት ገደማ በመንግሥቱ ንዋይና በተባባሪዎቹ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ደርግ 61 የቁርጥ ቀን ልጆችን በእንበለ ፍርድ ከጨፈጨፈበት ጋር ይነጻጸራል። እተጌ ታማለች እና ኑ በማለት ለስብሰባ ጠርቶ ሃሳቡን አንጋራም ያሉትን አዛውንቶች ጨፍጭፎ መግደሉ ሃገር ወዳድ አያስብለውም። ያው ዛሬም ከ 60 ዓመት በህዋላ ልዪነታችን እየሰፋ በጎሳና በጎጥ እየተከፋፈልን አልፈነዋል ያልነው የእንስሳት ባህሪ በምድሪቱ እየታየ ይገኛል። አሁን በተለይም በትግራይና ክልል ባሰከራቸው ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚታየው ሽኩቻ በመሳፍንት ዘመን ከነበረው ጋር ይመሳሰላል። ሁሉም የማእድ ቤት ጀግና። ሁሉም አሳማ ይመስል ለእኔ ብቻ የሚልባት የወልጋዶች ሃገር ሆናለች።
  እውቁና ሃገር ወዳዱ አክሊሉ ሃ/ወልድ በቁጥር 30 የሆኑንት የግብጽ ወታደሮችና የስለላ መዋቅር ሰራተኞች እንዲመለሱ ያደረገው አቶ ብርሃኔ እንዳለው ለሰላም አስከባሪነት ተልከው አልነበረም። ሃገር ለማናጋት እንጂ። እንደምናውቀው አሁንም አላረፉም። በመሰረቱ የተባበሩት መንግስታትም ድርጅት በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል በአባይ ወንዝ ጉዳይ ያለውን እሰጣ ገባ ስለሚረዳ የግብጽን ሰላም አስከባሪነት አይፈልገውም። ለነገሩ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የተቋቋመው 25 May 1963 በነጮች የዘመን መስፈሪያ በ 32 ሃገራት አባልነት ነው። ጊዜው አይገጣጠምም። እስቲ ማን ይሙት የግብጽ ወታደር የጥቁር ሰው ደም እንዳይፈስ ዝብ ሊቆም። የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ይሉሃል ይሄ ነው። የእኛ መገዳደል የእነርሱ ጮቤ መርገጫ ከሆነ ዘመናት አልፈዋል። ዛሬም ቢሆን የአረቦቹ ሴራ አልተገታም። የታህሳስ ግርግር የተባለው መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የሚለውን ቃል ላለማስገባት ሆን ተብሎ የተሸረበ ፈሊጥ ነው። በብራዚል ጉብኝት ላይ የነበሩት ንጉሱ ያው በአስመራ በኩል ሲመለሱ ሁሉም ለመኖር አደገደገ። ኮ/ሌ መንግሥቱም ከፈረሰችው የድሮዋ ምስራቅ ጀርመን በአስመራ በኩል ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አብረው የሴራው ተካፋይ የነበሩት ናቸው የሃይል ሚዛን አይተው ጓደኞቻቸውን እንደ ጄ/ፋንታ በላይ ያሉትን በራሳቸው እጅ አጥፍተው ራሱን ገደለ እያሉ ከመንግስቱ ጎን የቆሙት። ጄ/መንግሥቱ ንዋይ የረሸናቸው ወገኖች በጣሊያን ጦርነት ጊዜ በረሃ ለበረሃ የተንከራተቱ፤ በውጭ ሃገር በስደት ላይ ሆነው ሃገራችን ወክለው የተፋለሙና ጥቂት አውደልዳዪችንም ያካተተ ነበር።
  Richard Greenfield – Ethiopia: a new political history በተሰኘው መጽሃፉ ላይ የጄ/መንግሥቱ ንዋይን የመጨረሻ ቀን እንዲህ ሲል ይገልጻታል። አዲስ አበባ ጭጋጋማ ቀን ነበር አልፎ አልፎም ዝናብ ያካፋል። የሚሰቀልበት ስፍራና የመስቀያው ዝግጅት ከፊት ለፊት ይታያል። ታጅቦ በመምጣት ያለምንም ማመንታት የተዘጋጀለት ቦታ ወጣ ገመድ ከአንገቱ ገባ የቆመበት ተገፈተረ ከጥቂት ደቂቃዎች በህዋላ በድኑ በሰው ተከበበ። ዝናቡም ማካፋቱን አላቆመም ይለናል። ስንገል ስንገዳደል፤ ስናቃጥል፤ ስናፈርስ ኖረን አሁን ደግሞ ባሰ እንጂ የሚሻል ነገር የለም። ከ 60 አመታት በህዋላ ዛሬም የምንፋጀው ያኔ የፓለቲካ ተግዳሮት በነበሩ ችግሮች ላይ ነው። በአለህበት ሂድ ይሉሃል ይሄ ነው። የሁለቱ መንግስቶች (መንግስቱ ንዋይና መንግሥቱ ሃይለማሪያም) በሃገሪቱ ለውጥ ለማምጣት መሻታቸው ወያኔና ሻቢያን ወልዶ አሁን ያለንበት ላይ ደርሰናል። መሰንበት መልካም ነው። ሌላም እናያለን። ቀሪው ሁሉ ፍሪሬ ፈርሲኪ – ፉርሽ ነው!

 3. Mengistu and Girmame Neway were executed by hanging for the said “treason”. Does Achamyeleh want to sentence and kill them once again?? You can not bring back the Atse imperial system even that way!! You can not resurrect the dead!

 4. ሰውየው! ከዚያ ትውልድ ጀርባ አልወርድ ያልኸው ለምንድን ነው? ስንት የሚጻፍበት ወቅታዊ ሁኔታ እያለ ሮጠህ ሄደህ ከዚያ ትውልድ ጀርባ ላይ ፊጢጥ ትላለህ። ኧረ ይደብራል

 5. ኣባ ቃላ እና ኣማሮ
  ምነው ታሪክ አይነገር አላችሁ አቻም እውነቱን እየፈለፈለ እያውጣው ነው፡፡ ብውሽት ትንገርት የተወናበደ ትውልድ ሃገር ማፍረሱን ተያይዞታል ስለዚህ ቢመርም እውነታውን ዋጡት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.