ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ብዙዎቹን የትግራይ ተወላጆችን 1 ለ 5 በሚል አደራጀ

ምንጮቻችን እንደገለጹልን ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ብዙዎቹን የትግራይ ተወላጆችን 1 ለ 5 በሚል አደራጅቷል:: ይህም በአሻንጉሊቶቹ የተከበበት ኢህአዲግ ካለው መሰል አደረጃጀት ጎን ለጎን ነው:: እነኝሁ 1 ለ 5 የተደራጁት የወያኔ አባላትም ወደዱም ጠሉም ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ለሚመደብላቸው ሰው ስለሚኖሩበት፣ ስለሚሰሩበት በአጠቃላይ ስላዩት፣ ስለሰሙት፣ ስለሰለሉት ዘገባ (ሪፖርት) ያደርጋሉ::

ባለፈው እሁድ ከተካሄደውና ወያኔ እራሱ ተወዳዳሪ፣ እራሱ ዳኛ ሆኖ ካሸነፈበት የቀልድ ምርጫ ጋር በተያያዘም 20 ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሲቪሎች መሳሪያ ታጥቀዋል አዲስ አበባ ውስጥ:: እነኝሁ አባላትም የሚያወቋቸውን ሰዎች ሁሉ “ካርድ ወስደሃል? መርጠሃል ወይ?” ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅና በወግ መልክ በመሰለልና በመከታተል፣ ለተመደበላቸው የወያኔ አገናኛቸውም ዘገባ በማቅረብ ተጠምደው ሰንብተዋል::

ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃዋሚ የሚባሉትን ለማዳከም በተለይ ትግራይን ሙሉ በሙሉ የተቃዋሚነት አዝማሚያ ካላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ተጽዕኖ ነፃ ለማድረግ ያለምንም ምህረት (ዜሮ ቶሎራንስ) እየሠራ ነው:: ከዚህም ጋር በተያያዘ ገብሩ አሥራትን ለጥቃት እያዘጋጁት ነው:: በመጽሀፉ የትግራይን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል፣ የትግራይን ህዝብ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል አቋም እያራመደ ነው፣ ይህም ከመጽሀፉ በተጨማሪ ውጭ ሄዶ መግለጫ ሲሰጥ ተንጸባርቋል፣ ወዘተ የሚሉትን ክሶች በሰፊው በወሬ ደረጃ በማናፈስ ላይ ይገኛሉ:: ወያኔ የጥቃቱ ጭዳ ሊያደርጋቸው ያሰባቸው ሰለባዎቹ ላይም ይህን መሰል ወደ ጥቃት የመረማማጃ ወሬ በሰፊው ማናፈስ ከደደቢት ጀምሮ የሚሠራበት የተለመደ ስልት ነው::

በትግራይና ከዚያም ውጭ የሚኖሩት አባላቱን፣ በአጠቃላይ የክፍለሃገሩን ተወላጆች “ኤርትራ ጠላት እያዘጋጀብን ነው፣ ሰርጎ ገቦች ሊልክብን ነው፣ ወዘተ” የሚሉትን ወሬዎች በሰፊው በማስወራት በፍርሃት ሸብቦ ለመያዝ እየጣረ መሆኑም ታውቋል::

በመጨረሻም በምርጫው የአሯሯጭነት ሚና የተጫዎቱት ተቃዋሚዎች ስለውጤቱ ካወጧቸው መግለጫዎች ጋር በተያያዘ የወያኔ ካድሬዎች መቀሌ ውስጥ በየመዝናኛ ሥፍራዎች በአደባባይ “ዱሮስ ማን ዴሞክራሲ አለ አላቸው! ዱሮስ በደም የተገኘን ድል በብጣሽ ወረቀት ማን መውሰድ ይቻላል አላቸው! ወዘተ” በማለት በድል አድራጊነት ሲቀልዱ ምንጮቻችን ታዝበዋል:: በታሪክ ሃያላን የተባሉት ሁሉ ወቅታቸውን ጠበቀው መውደቃቸውን ለነኝህ ባለጊዜዎች ማን በነገራቸው?

ከደብተራው ምንጮች

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.