ሳምንቱን አራት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

ሳምንቱን አራት ሚሊየን (4000 000)ብር የሚጠጋ ዋጋ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

– በቀን 21/04/2012 ዓ/ም በጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-48735/22729 ኢት የሆነ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ህጋዊ ዕቃ ጭኖ በመግባት ላይ ሳለ በስካኒንግ ማሽን በተደረገለት ፍተሻ ግምታዊ ዋጋው ብር 461,600 የሆነ ህገ-ወጥ የሞባይል ባትሪዎችን በተሽከርካሪው የተለያዩ ክፍሎች ላይ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ተጠርጣሪ ሹፌሩም ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተላልፏል፡፡

– በቀን 21/04/2012 ደግሞ የሠሌዳ ቁጥሩ 3-03616 ድሬ የሆነ አይሱዙ ግምታዊ ዋጋው 709,250 ብር ከሦማሌ ላንድ ተነሥቶ ወደ ሐገር ሀገር ሢገባ በጉምሩክ ሠራተኞች እና በፌደራል ፖሊሥ አባላት በተደረገ ክትትል ቢዮበሀይ በረሃ ላይ ተይዞ እቃ ድሬዳዋ ጉምሩክ መጋዘን ገቢ ተደርጓል ።

– በቡሌ ሆራ ኬላ የሞያሌ መቅረጫ ጣቢያ በቀን 16/4/2012ዓ.ም 20.75ኪ.ግ የሚመዝን እና ግማታዊ ዋጋዉ1,304,875 ብር የሆነ ጌጣጌጥ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ተይዟል፡፡

– በቀን 14/04/2012 አዋሽና አልበረከቴ ጉ/መቆ/ኬላ ግምታዊ ዋጋቸው 557,500 የሆ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በጉምሩክ ሰራተኞች እና ፌዴራል ፖሊስ ተይዟል ።

– በባህር ዳር ጉ/ቅ/ ሰራባ ጉ/መቆጣጠሪያ ጣቢያ በ19/04/2012 ዓ/ም በመከላከያ ፡ በፌ/ሊስና በጉምሩክ በቅንጅት በሸክም ሲያልፍ በመጣ ጥቆማና በበረራ ልዩ ልዩ አልባሳት ፡ ጫማ አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋ 95,175 ብር የሚያወጣ እቃ ተይዘዋል።

– በቀን 19/04/2012 በጅማ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ጌዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ከመሀል ሀገር ወደ ነቀምት ሲጓዝ የነበረ የተለያየ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ እና እስቲም መጠጦች ግምታዊ ዋጋ 220,000 ብር የሁነ ዕቃ ተይዞ ገቢ ተደርጓል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ የመቅረጫ ጣቢያዎች ሳምንቱን ሌሎች የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችም መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢ.ፕ.ድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.