ልጅና ሚስት ስለሌለኝ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ ይላል አቶ ልደቱ አያሌው

ከምርጫ 97 በሗላ በእኔ ላይ ዘመቻ ተከፍቶብኝ ነበር። ልጅና ሚስት ስለሌለኝ ግን ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ። ህፃናት ልጆች ቢኖሩኝ ትምህርት ቤት ውስጥ፣ ሰፈር አካባቢ ስለ እኔ በሚባለው አሉባልታ ልባቸው እንዴት ሊሰበር እንደሚችል አስቡት። ሚስት ቢኖረኝም እንደዚያው። ስለዚህም የሀገራችን የጥላቻ ፖለቲካ እስካልተቀየረ ድረስ በህይወቴ ውስጥ ሌላ ቤተሰብ በማምጣት እንዲጎዳ አልፈልግም። እኔ እንደገባሁበት፣ እኔው እወጣዋለሁ።

ፖለቲካችን በትምህርት ያልገፉ፣ አለም አቀፍ ተቋማት ተወዳድረው ማሸነፍ ያልቻሉ፣ ለፈጠራ ያልታደሉ፣ መሄጃና መዋያ ያጡ፣ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በኢኮኖሚ ያላበቁ … በአስተሳሰብም፤ በኢኮኖሚም ድሃ የሆኑ ሰዎች መጠራቀሚያ አድርገነዋል።

ይሄን ያመጣብን ደግሞ ድህነትን እንደ ጀብዱ የሚያየው የኮሚኒስት ፓለቲካ ነው። በዚህ መንገድ መቀየር አንችልም። የፈጠራ ሰዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ በትምህርታቸው የበቁ ሰዎች ወደ ፖለቲካው መምጣት አለባቸው። ሀብትና ፖለቲካንም ሆድና ጀርባ እንደሆኑ ማሰብ የለብንም።

እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ድረስ ከፖለቲካ አልወጣም። የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ እታገላለሁ። በእርግጥ በፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ እቅዱ የለኝም። በፓርቲ ውስጥ ሆኜ አስተሳሰብ ላይ መስራት እንጂ!

(አቶ ልደቱ አያሌው – ከኤል ቲቪ ጋር ካደረጉት ቆይታ የተቀነጨበ)

አዲስ ሚዲያ

2 COMMENTS

  1. Lidetu should worry for his old age and start making babies, we all need children to support us in case we live a long life since the government’s retirement payment is too low.
    The yearly Ethiopian governments retirement payment budget is only Six billion birrs divided by the 750 thousands retirement recipients it comes equal to eight thousand birrs for each person per year, eight thousand birrs divided by twelve months is six hundred sixty six birrs per month for each of the seven hundred fifty thousand retirees assuming they all get paid the same amount monthly.
    Also the Ethio-Eritrean Badme war disabled volunteer Wedo Zemach fighters are not getting any retirement payments if it wasn’t for the children helping them.

    https://www.zehabesha.com/amharic/archives/100090

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.