ባለፉት 4 ወራት ብቻ በኦሮሞ ክልልና በድሬዳዋ የተገደሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው – ግርማ ካሳ

አገር ሰላም ነው በሚል ነበር ወደ ትምህርት ቤቶች የሄዱት፡፡

ሰሞኑን ደግሞ እንደምንሰማው ሴት የደምቢ ደሎ ተማሪዎች በአሸባሪ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ታግተው ይገኛሉ፡፡ ቦኮ ሃራም እያደረገ እንደነበረው፡፡

ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን በኦሮሞ ብሄረተኞች የሚመራው የኦሮሞ ክልል መንግስት የተገደሉትና የታፈኑት ኦሮሞ ስላልሆኑ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም፡

1 COMMENT

  1. በሻቢያና በወያኔ ጥላቻ የተቃመሱት የኦሮሞ ህዝብ ተጠሪ ነን የሚሉት ዋና አላማቸው ኦሮሚያ የምትባል ሃገር ለመመስረት ነው። በቅርቡ በወለጋ ጫካ ውስጥ ሆኖ ሰው የሚያሸብረው ቡድን መሪ ለአሜሪካ የኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል የሰጠውን አጭር ቃለ ምልልስ ላዳመጠ የውጭ ድጋፍ እንዳለውና ለኦሮሞ ህዝብ ብቻ ለመታገል ጫካ እንደገባ ይናገራል። አዎን ነጻ እናወጣሃለን የሚሉትን ህዝብ ማሸበር የሃበሻው የፓለቲካ ዘይቤ እንደሆነ ያለፈ ታሪካችን ከአሁኑ ጋር አብሮ ያመላክተናል። ሌላው ዓለም የህዋ ምርምር ሲያረግ የእኛው የዘር ፓለቲካ በምታክል መሬትና ክልል ሲጋደል ይውላል።
    ፈራሽ ሃገሮች ተብለው በውጭ የስለላና የሃገራት ሚዛን አሰላለፍ መዝገብ ውስጥ ከተመደቡት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። አሰላለፏም ከሜክሲኮ ጎን ነው። የመመዘኛውን ነጥቦች ለተመለከተ እነዚህ ሁለት ሃገሮች በመሬት አቀማመጣቸው እጅግ የተራራቁ ቢሆኑም የሚጋሩት አንድ ዋና ነጥብ አለ። ህግና ደንብ የማይከበርባቸው ሃገሮች ናቸው። በሜክሲኮ በህገ ወጥ አደንዛዥ እጽ ሰዎች ተቧድነው ሲገዳደሉ በሃበሻው መሬት ደግሞ በዘር፤ በጎሳ፤ በቋንቋና በሃይማኖት እንፋለማለን። የተገደሉ ተማሪዎችን የዘር ሃረጋቸውን ትተን ለኮሌጅ ትምህርት ለመብቃት ያሳለፉትን መከራ ላሰብ መፈጠርን ያስጠላል። የድሃ ልጅን ገድሎ ከሚፎክር የኦሮሞ ጥርቅም ጋር እንዴት ተደርጎ ነው ሰላም የሚኖረው? ፓሊሱ በዘሩ፤ ዳኛው በቋንቋ፤ ወታደሩ በአሰላለፉ በሚያደላበት ሃገር ሰው ሆኖ መኖር ከባድ ነው። በመሰረቱ የሻቢያና የወያኔ የቀድሞና የዛሬውም እውነታ የሚነግረን ጠላትህ “አማራ” ነው። አማርኛ ቋንቋም የአማራ የመጨቆኛ ቋንቋ ነው እያሉ ውሸቱን ያጋቱት ያ ትውልድና የእነርሱ ልጆች ዛሬ ከእባብ ወደ እፉኝት ቢለወጡ አስደናቂ አይሆንም። ተማሪዎችን አግቶ ሃበሳ የሚያደርስ ወንጀለኛ የኦሮሞን ህዝብ ነጻ ያወጣል ብሎ ማሰብ ተንጋሎ መትፋት ነው። ወያኔ በመቀሌ ከሚስቱ ጋር እንደተፋታ እቃ እካፈላለሁ እያለ በጎን እሳት መለኮሱ ወያኔ ያለ ሽብር ፈጠራ መኖር እንደማይችል ያሳያል። ለወያኔ፤ ለኦሮሞ፤ ለሻቢይና አጨብጫቢዎቹ ጠላታቸው አማራ ነው። በውጭም በውስጥም እየጻፉና ከፍለው እያጻፉ በሰዎች ልብ ሰርጎ እንዲገባ ያደረጉት የውሸት ትንግርት ይህ ነው። በቅርቡ የሳውዲ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ ስለ ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም እርቅ የተናገሩት አረቡ ዓለም ከነጩ ጋር አብሮ ሃገሪቱ በማያቋርጥ የመገዳደል አዙሪት ውስጥ እንድትገባ እንደሚሰሩ ያሳያል። የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠውን ምላሽ አይቻለሁ። ማለፊያ ነው። ግን እኮ አረቦች ለሃበሻው ምድር ተኝተው አያውቁም። የአረብ ራቢጣ በአባይ ግድብ ዙሪያ ከግብጽ ጋር ማበሩም ኢትዮጵያን እስላማዊት ሃገር ለማደርግ ካላቸው የቆየ እይታ ጋር ይዛመዳል። አሁን እንዘጥ እንዘጥ የሚባልለት የምርጫ ወከባም በክልሌ ዙሪያ የእኔን ጡሩንባ ስሙ ለማለት እንጂ ሰው በነጻነት ተንቀሳቅሶ ከዳር እስከዳር ለሚኖረው ህዝባችን ሃሳቡን አካፍሎ ሃገራዊ አንድነትንና ሰላምን ለማረጋገጥ የሚችል አይመስለኝም። ታዲያማ የአሁኑ የፓለቲካ አሰላለፋችን የመሳፍንት ዘመን አይነት ይመስላል። እያደሩ መውረድ ይሉሃል ይህ ነው። ክላሽንኮፕ መሳሪያ ስለያዘ አለምን እንደገዛ ከሚመስለው የሾተላይ ስብስብ ጋር እንዴት አብሮ መኖር ይቻላል? አይቻልም። ሲገድሉ፤ ሲጋደሉ፤ ሲያለቅሱ፤ ሲያስለቅሱ ኖሩ። ዛሬም ይህ የምሾና የዋይታ እኔ ነኝ ጀግና የባዶ መሬት ፉከራ አልቆመም። የሚቆምም አይመስለኝም። የታገቱትም ሆነ በየትምህርት ተቋማቱ ከፎቅ ላይ እየተገፈተሩና እየታረድ እየተደበደቡ የሞቱትም ደም ደመ ከልብ ነው። የሚታደገው የለም። ፍትህ በዘርና በቋንቋ በሃይማኖት በተሸነሸነች ሃገር ቦታ የለውም። ሰቆቃው ይቀጥላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.