እነ ክርስቲያን ታደለ ቤተሰቦቻችን ችሎቱን ካልታደሙ የሚል ተቃውሞ በማሰማታቸው ማረሚያ ቤት ሆነው ችሎቱ በፕላዝማ እንዲታደሙ ፍርድ ቤቱ ወሰነ

በሰኔ 15ቱ የጦር ጄነራሎች እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ በተያያዘ በእነ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

በችሎቱ ቤተሰቦቻቸው በተገቢው ሁኔታ እንዲታደሙ ባለመደረጉ ከማረሚያ ቤት ከመጡበት መኪና አንወርድም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በበኩሉ የፀረ-ሽብር እና ህገመንግስታዊ ሥርዓት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በተመለከተ ችሎቱን የሚታደሙ ቤተሰቦች እንዲቀነሱ ትእዛዝ የሰጠሁት ህግን ባለ ማክበር የችሎት ሥራ እየታወከ በመሆኑ ነው ብለሏል፡፡

ተከሳሾች ችሎቱን ለመታደም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከዚህ በኋላ በማረሚያ ቤት ሆነው በፕላዝማ እንዲከታተሉ ሲል ችሎቱ አዟል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የፕላዝማ ችሎቱን እንዲያመቻች በማዘዝ ለየካቲት 18፣ 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በአንደኛ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍት ጥጋቡ ላይ የተሻሻለው ክስ አቃቤ ህግ በማረሚያ ቤት በኩል ለተከሳሾች እንዲደርስ በችሎቱ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

የተከሳሽ ጠበቆች ተከሳሾች በሌሉበት ችሎት አንቀርብም በማለት ፍርድ ቤቱ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል፡፡

Walta

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.