አዴፓዎች ለዶ/ር አብይ ግልጽ ቅድመ ሁኔታዎች ማስቀመጥ አለባቸው – ግርማ ካሳ

በታገቱ ተማሪዎችና በሌሎች የአገር ደህንነትና መከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ አዴፓ/ብአዴኖች ከጨዋታ ውጭ ሆነዋል። አንዱ እንዳለው በብልጽግና ስም አዴፓውፕች ከደህንነትና መከላከያ ተቋማት ተባረዋል። አስቡት አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስትር ነው። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቲር ነው። አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ፓርቲ የጽ/ቤት ሃላፊ ነው። ወ/ት ዳግማዊት ሞገስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል ናት። እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የአዴፓ አመራር አባላት አሉ። አንዳቸውም መንግስታዊ መረጃ በተማሪዎች ጉዳይ የላቸውም። አላያችሁም እንዴ ኦህዴዶች ንጉሱ ጥላሁንን የማይሆን የዉሸት መረጃ ሰጥተውት መሳሳቂያና መቀለጃ እንዳደረጉት።

ለዚህም ሳይሆን አይቀርም በአዳማ ስብሰባ በአዴፓዎችና በኦህዴዶች መካከል ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ እንደነበረ የተዘገበው። አዴፓዎች ውስጥ ውስጡን መቆጨት ሳይሆን እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ ማዳመጥ መቻል አለባቸው። የዛሬ ሰልፍ አንዱ አላማ የታገቱእነርሱ ሚወክልት ሕዝብ ጋር ተስማምተው ከብልጽግና እስከመውጣት ድረስ ዉሳኔዎች መወሰን መቻል አለባቸው። አስፈላጊም ከሆነ ከብልጽግናን በመውጣት የኦህዴድን መንግስታዊ ውንብድና በመቃወም የሕዝብን ጥያቄ ማስቀደም አለባቸው። እንደው አንድ ቀላል ምሳሌ ኦህዴድ ሌልው ቢቀር

አንድ – በአስቸኳይ የታገቱ እስረኞችን በተመለከተ ግልጽ ማብራሪያ ዶ/ር አብይ እንዲሰጥ

ሁለት – ብዙዎችን ያሳራዱ ያስገደሉ አንድ ጃዋርን ኦህዴዶች በአስቸኳይ ለሕግ እንዲያቀርቡ

ሶስተኛ – ኦህዴድ እንደ ሺመለስ አብዲሳ ያሉትን እንዲያባርር

በመጠየቅ ቁርጥ ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ፣ የዶ/ር አብይ ይሄንን የማያደርግ ከሆን ደግሞ ከብልጽግና ፓርቲ በመውጣት ከሕዝብ ጋር መሰለፍ መቻል አለባቸው። እስከ አሁን በሆነው ነበር መማር አለባቸው። ኦህዴዶች ላይ ላዩን ለስትራቲጂ እንጂ ጎጠኞች ናቸው።፡ለሁሉም ሰው ለጎጣቸው ብቻ የቆሙ፣ ሁሉንም በ እኩልነት ሳይሆን የነርሱን ጎጥ ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሰሩ፣ ተራው የኛ ነው የሚሉ ናቸው።

ደግሜ እላለሁ፣ አዴፓዎች እንደ ከብት አንገታችሁ ላይ ገመድ ታስሮ ከመጎተት፣ ራሳቸሁን ከዉርደትና መሳቂያ ከመሆን ነጻ አውጡ።

1 COMMENT

  1. እንደሁሌው ጥሩ ብለሀል ከዚህ በላይ እንኳን የሚዋረዱ አልመሰለኝም ነገር ከመሸ በሗላ ነው ነቃ የሚሉት። ክራቫት እያስተካከሉ በሉ የተባሉትን የሚያወሩት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.