ከሃያ ከተምች በላይ ሕዝብ ድምጹን አሰማ -ግርማ ካሳ

ከ20 ከተሞች በላይ ሕዝብ ድምጹን ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሰምቷል። ያ ሁሉ ሕዝብ ወጥቶ በንብረት ላይ የደረሰ አንድም ጥፋት የለም። ምንም አይነት ረብሻም ሆነ ቀዉስ አልተፈጠረም። የተጎዳ ማንም ሰው የለም። የተወረወረች አንድት ጠጠር የለችም።

ሕዝቡ ሰልማዊ በሆነ መንገድ ለመንግስት አካላት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። በተለይም የአዴፓ አመራሮች ላይ ያለው ከፍተኛ ተቃዉሞ ገልጿል። መንግስት እባስቸኳይ የታገሩ እስረኞችን በተመለከተ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቋል።

ከጎጃም
——
አዲስ ቅዳም፣
ሉማሜ፣
ዳንግላ፣
ዱርቤቴ፣
ቡሬ፣
ፍኖተ ሰላም፣
ደብረ ማርቆስ፣
ቢቸና፣
ባህር ዳር፣
ሞጣ፣
ይልማና ዴንሳ ወይም አዴት እ
መራዊ፣
አቸፈር

ከወሎ
——
ቆቦ፣
ራያ፣
ወልዲያ፣

ከሸዋ
——
ሸዋ ሮቢትና
ደብረ ብርሃን

ከጎንደር
——–
ወሮታና አምባጊዮርጊስት ሰላማዊ ስልፎች እየተደረጉ ነው።

20 ከተሞች – ከጎጃም ፣ መንቆረር፣ አዲስ ቅዳም፣ ሉማሜ፣ ዳንግላ፣ ዱርቤቴ፣ ቡሬ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረ ማርቆስ፣ ቢቸና፣ ባህር ዳር፣ ሞጣ፣ ይልማና ዴንሳ ወይም አዴት እና መራዊ፣ አቸፈር ከወሎ ቆቦ፣ ራያ፣ ወልዲያ፣ ከሸዋ ሸዋ ሮቢትና ደብረ ብርሃን ከጎንደር ወሮታ ሰላማዊ ስልፎች እየተደረጉ ነው።

በሌሎች በበርካታ የጎንደር ከተሞች ጥር 24 ቀን ሰልፍ እንደሚደረገ እየተገለጸ ነው።

ከአማራ ክልል ውጭ በአዲስ አበባና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ የነበረ ቢሆንም፣ አዲስ አበባን የሚገዝው ኦህዴድ ሕግ መንግስቱን በመጣስ የዜጎችን ድምጻቸው በሰላማዊ ሰለፍ የማሰማት መብታቸው እየገደበ ነው።የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላማዊ ስልፍ ለማድረግ የቀረበለትን የ እወቁልኝ ደብዳቤ አልቀበልም ያለ ሲሆን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በማሰር የማወክ ተግባር ላይ እየተሰማራ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.