የቻይና የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሆስፒታል በሁለት ቀናት ተገነባ

የቻይና የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ሆስፒታል በሁለት ቀናት ተገንብቶ ታማሚዎችን ማስተናገድ ጀመረ፡፡

በውሀን ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ይህ የቻይና የኮሮቫ ቫይረስ ሆስፒታል 1 ሺህ ታማሚዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን አሁን አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

የከተማዋ ባለሥልጣን እንዳስታወቀው ሆስፒታሉን በስድስት ቀናት ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ታቅዶ የተሰራ ቢሆንም የግንባታ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ፣ የፍጆታ ኩባንያዎች እና የፖሊስ ኃላፊ መኮንኖች በትብብር ጥረታቸው በ 48 ሰዓታት ውስጥ ግንባታውን ማጠናቀቅ ተችሏል ፡፡

አሁን ካለቀው ባለ 1ሺህ አልጋ ሆስፒታል በተጨማሪ በውሃንና ዦንግዡ ግዛቶች ተጨማሪ ሁለት ሆስፒታሎች ግንባታቸው በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን በመጪው ግንቦት ወርም ተጠናቀው ክፍት እንደሚደረጉ ዴይሊ ሜል አስነብቧል፡፡

ሶስቱም ሆስፒታሎች ወደ ስራ ሲገቡ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ 25 ሺህ ታካሚዎችን ማስተናገድ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ኢ.ፕ.ድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.