አቶ ጀዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚያሳይ ሰነድ እንድያቀርቡ ለሁለተኛ ተጠየቀ

ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአቶ ጀዋር መሀመድ የኢትዮጵያዊ ዜግነት ሰነድ እንድያቀርብ ቀነ ገደብ የተቀመጠለት ሁለተኛ ደብዳቤ ለ ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፃፈ።

ኦፌኮ በበኩሉ ጉዳዩ በህግ መሰረት እልባት እንድያገኝ እናደርጋለን ብሏል። ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ለ VOA በሰጡት መልስ ኦፌኮ አቶ ጀዋር መሀመድ በአባልነት መቀበሉንና የአሜሪካ ዜግነታቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በመናገራቸው ምክንያት ምርጫ ቦርዱ ሁለተኛ ቀነ-ገደብ ያለው ሁለተኛ ደብዳቤ ለመፃፍ መገደዳቸው ነው የተናገሩት።

ደብዳቤውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚያሳይ ሰነድ እንድያቀርቡ ነው የሚጠይቀው ብለዋል ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ።

ጀዋር መሀመድ ከፖለቲካ አክትቪስትነት ወደ ፖለቲካ ፓርቲ አባልነት እንቅስቃሲያቸው በመቀየራቸው ከቅርብ ግዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ዜግነት ጥያቄ እየቀረበባቸው ነው።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.