ሳተናው የድሬዳዋ ወጣቶች ማህበር ከአለም አቀፍ የግጭት አጥኚ ቡድን /ICG/ ጋር ውይይት ማድረጉን አስታወቀ

አማራ ሚዲያ ማዕከል /አሚማ
ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

የአለም አቀፉ የግጭት አጥኚ ቡድን / International Crisis Group /ICG ተወካዮች በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በመገኘት በከተማዋ ውስጥ ስለሚነሱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች መነሻቸውን ለማጥናት ከሳተናው የድሬዳዋ ወጣቶች ማህበር አመራር እና አባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

የሳተናው የድሬዳዋ ወጣቶች ማህበር አባል የሆነው አቶ ወንድወሰን ኪዳኔ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል እንዳስረዳው ከአለም አቀፍ የግጭት አጥኝ ቡድን ተወካዮች ጋር ሳተናው ስለተሰመሰረት ዓላም ለተወካዮች ያብራሩ ሲሆን ፤ ስለ ድሬዳዋ ከተማ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዳደረጉም አስታውቀዋል።

በድሬዳዋ ከተማና አካባቢዋ ስለሚነሱ ዘር ተኮር ግጭት መነሻቸው እና ዓላማቸው ምን እንደሆነ በዝርዝር እንደተወያዩ ተናግረዋል።

በድሬዳዋ ከተማ ስላለው የ 40 40 20 አፋኝ ስርዐት እና እያደረሰ ስላለው ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ እንዲሁም ሳተናው የድሬዳዋ ወጣቶች ማህበር ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ለምን መቀየር እንዳስፈለገውም ለተወካዮቹ እንዳስረዱ አቶ ወንድወሰን ኪዳኔ ገልፀዋል።

ባለፉት አንድ አመት ሳተናው የድሬዳዋ ወጣቶች ማህበር ነፃ እና ገለልተኛ የሆነ የሲቪክ ማህበር በመሆን የተለያዮ እንቅስቃሴዎችን ያደረገ ሲሆን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የድሬዳዋን ህዝብ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እንዲሁም ትግሉን ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ለመቀየር ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኘ አስታውቋል።

ለወትሮው የፍቅር እና የመቻቻል ከተማ ተደርጋ የምትነሳው ድሬዳዋ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ማንነትን መሰረት ባደረጉ ፀረ ሰላም ሐይሎች ሰላም እየራቃት እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.