ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ እና ባልደረቦቹ ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ መገናኛ ቀበሌ 24 አካባቢ በፖሊሶች የተገደሉትን የሁለት ሟች ቤተሰቦችን በስፍራው ተገኝተው አፅናኑ

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ ገብርኤልና አርሴማ ቤተክርስትያንን በሌሊት ለማፍረስ የመጡ የፖሊስ አባላት ወደ ህዝቡ በመተኮስ በትንሹ ሁለት ሰዎች የገደሉ መሆናቸው መዘገቡ ይታወሳል።

በ22 ጀርባ በተለምዶ በመገናኛ ቀበሌ 24 በሚባለው ሰፈር ላይ የተሰራ ቤተክርስትያንን ለማፍረስ ከመንግስት ወገን ነን በሚሉትና በህብረተሰቡ መካከል ለቀናት ውዝግብ ነበር የተገለፀ ሲሆን ባልታሰበ ሁኔታ ያሳለፍነው ሌሊት ወደ አካባቢው ባቀኑ የፖሊስ አባላት ንፁሀንን ገድለዋል፣ አቁስለዋል፣ቤተ ክርስቲያን እንዲፈርስ ማድረጋቸውም ተዘግቧል።

ይህን ተከትሎ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር፣ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ እና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና አባላት የሟች ቤተቦችን በስፍራው ተገኝተው ያፅናኑ መሆናቸው ተገልጧል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በተፈፀመው ድርጊት ባልደራስ እጅጉን ያዘነ መሆኑን በመግለፅ በዚህ አስነዋሪና አሳፋሪ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ አካላት፣የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጭምር ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ብሎ ፓርቲው ያምናል ብለዋል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር፣ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና አባላት ወደ መገናኛ ቀበሌ 24 በማቅናት ሌሊት ላይ በፖሊስ የተገደሉ የሁለት ንፁሀን ቤተሰቦችን ማፅናናታቸውን አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል።

አቶ ስንታየሁ እንዳሉት በአካባቢው ከትናንት ምሽት ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የኦሮሚያ ክልል የልዩ ሀይል አባላት ሲያንጃብቡ እንደነበር በተኩሱም ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊሶች በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል የልዩ ሀይል አባላት እንደተሳተፉ ከነዋሪዎች መረዳት ችለናል ሲሉም አክለዋል።

ይሁን እንጅ በሌሊት ወደፈረሰው ቤተ ክርስቲያን ቀርበን ህዝቡን ለማነጋገርና ከፍተኛ ተኩስ ወደነበረበት አካባቢ ቀርበን እንዳናጣራ በፖሊሶች ክልከላ ተደርጎብናል ብለዋል።

ባልደራስ እንዲህ አይነት የለየለት መንግስታዊ ስርዓት አልበኝነትን የበለጠ ከህዝብ ጋር ሆኖ የሚታገለው መሆኑን አቶ ስንታየሁ አክለዋል።

3 COMMENTS

  1. The Acting Mayor of Addis Ababa Engineer Takele Uma asked for forgiveness because his subordinates killing people and wounding others at 22 Mazoriya neighborhood Orthodox church service participants.

    ” We will make forgiving our culture ” PM Abiy Ahmed, even Jawar is forgiven for Koyae Fechae and other crimes he committed to make forgiving our culture .

  2. አዎ!! ከ 2 ዓመት ጀምሮ አዲስ እየወረረ ያለው የታከለ ና የ አብይ ፋሽስታዊ መንግሥት አዲስ አበባን እጃቸው ውስጥ አስገብተው ሃብቷን ለመዝረፍ ፣ ኗሪ ሕዝቧን በመግደልና ጭቆና በማንሰራፋት ለትልቅ እልቂት “እየጋበዙን ” ነው። የሞት የሽረት ትግል ውስጥ እንድንገባ አስገድደውናል። በተናበበ መልኩ ከመመከት ሌላ ምርጫ የለንም ። አባ ማትያስና ሌሎቹ የኦርቶዶክስ አመራሮችም ቤተክርስቲያንን በማዳን ላይ ምንም ተሳትፎ ባለማድረጋቸው ምእመናን እንጠይቃቸዋለን። በመስከረም ላይ ብዙ ቤተክርስቲያናት በኦሮሞ ቄሮዎች ሰትቃጠል ምእመናኑ በአንድ ላይ ሆኖ ተቃውሞ ውን እንዳያሰማ አኮላሸተው ያስቀሩት የፋሽስት የውስጥ አርበኛ የቤተ ክርስቲያን አመራሮች ከሃላፊነታቸው መወገድ አለባቸው ።ገዳዮቹ ም ጊዜው ሲደርስ ቅጣታቸውን ማግኘታቸው አይቀርም ።

  3. ማንም ተነስቶ ትግልጦልኛል በሚል ባዶ ቦታ ሲያገኝ ቤተክርስትያን አይከትምም:: ትልቅ ጥፋት! ፖሊስ በሌሊት ሄዶ ማፍረስ አልነበረበትም የበለጠ ታላቅ ስህተት:: መንግስት ሟቾችን ቤተስብ ካሳ ማድረግ ይኖርበታል:: ከዚህ አሳዛኝ ድርጊት የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ድድብና ብቻ ነው:: የአዲስ አበባ ፖሊስ የህውሀት ኔትዎርክ ስለሆነ ብዙም አይገርመኝም:: እግዚአብሄር ይህን ምስኪን ህዝብ ይጠብቀው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.