ፍትህ ተገፋች: ለታገቱት እና ለሚገደሉት እንጩህ የኔ የአንተ እህትና ወንድሞች ናቸው= ደርበው ወልዴ

አሰቃቂ ድርጊት ህዝባችን ላይ ተፈጽሟል

1….ቡራዮ ላይ 400 የጋሞና የሌሎች ብሔር ተወላጆች
ተጨፈጨፉ
2….በዶዶላ የሰው ልጅ አካል ተቆራረጠ
3..በአርባ ጉጉና በብኖ በደሌ የሰው ሬሳ ተጎተተ
4…በሶማሌ ክልል ክርስቲያኖች ታረዱ
5..በሲዳማ ዞን የሀይማኖት አባቶች ቤንዚን ተርከፍክፎ ተቃጠሉ
6…በለገጣፎ በሰበታና በሰንዳፋ የንጹሃን ቤት በላያቸው ላይ
ፈረሰ
7…41 ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ
8..34 መስጂድ ተቃጠለ
9…ወለጋ ላይ 22 ባንክ ተዘረፈ
10…ኦነግ በአጣዬ በካራ ቆሬና በኬሚሴ ንጹሃንን ጨፈጨፈ
11..የአፋር አርሶ አደሮች በኡጋንዳ ታጣቂዎች ተረሸኑ
12… 1 ሚሊዮን የጌድዮ ህዝብ ተፈናቀለ
13…የአማራና የትግራይ ተወላጆች ከመስረያ ቤት እየተለቀሙ
ተባረሩ።
14…የአብን, የአማራ ወጣት እና የአማራ ተማሪ ማህበር
አባላትና አመራሮች በግፍ በጅምላ ታሰሩ
15…ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ተገደለ
16…በቤንሻንጉል ክልል ንጹሃን በቀስት ተገደሉ
17…ጎንደር ላይ ህጻናት ታግተው ተረሸኑ
18..45 ሺህ የአማራ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ተባረሩ
19…አሳምነው ጽጌና ሰዓረ መኮንን ጨምሮ በርካታ የአማራና
የትግራይ መሪዎች በኦነጉ አብይ ተረሸኑ
20…በሀረርጌ የ2 ወር አራስ ታረደች
21…ወለጋ ላይ 5 ንጹሃን ተገድለው ሬሳቸው ተቃጠለ
22…86 ንጹሃን በአንድ ቀን ተጨፈጨፉ
23…17 የአማራ ተማሪዎች ታግቱ
24….ሻሸመኔ ላይ ሰው ተዘቅዝቆ ተሰቀለ አብዛኛው ወንጀልም የተፈፀመው በአማራው ላይ ነው።
ልብ በሉ ይህ ሁሉ ግፍና መከራ ተፈጽሞ አንድም ወንጀለኛ
አልተያዘም።
ጎበዝ ብንችል አገር እንታደግ ባንችል ግን ለታገቱት እና ለሚገደሉት እንጩህ የኔ የአንተ እህትና ወንድሞች ናቸው::

2 COMMENTS

 1. በህልም አለም ውስጥ ሆኖ ሌላ ህልም በሚታየው የፓለቲካ ድርጅቶች ጥርቅም ሃገሪቱ እየታመሰች ነው፡፡ በኑና እንደመር ሂሳብ ሃገር ቤት የገቡት የኦሮሞ ከአንድ ደርዘን ያለፉ የፓለቲካ ድርጅቶች አሁን ወረፋው የእኛ ነው በሚል ዘይቤ ህዝብን ያተራምሳሉ፡፡ የሚያሳዝነው በውጭ ሃገር የኖሩ የኦሮሞ ሙሁራን ተብየዎች መጤ ናችሁ ከሃገራችን ውጡልን እያሉ ሰውን ሲገድሉ ሲዘርፉ ማየት ምንኛ ይዘገንናል፡፡ አዎን አውቃለሁ እኛ ይህን አላደረግነም ይሉናል፡፡ ወጥተው የተለየ መግለጫ ሲሰጡ፤ ወይም ይህ ተግባር ትክክል አይደለም ሲሉ ግን ሰምተንም አይተንም አናውቅም፡፡ ይባስ ብለው ሰው እየጠለፉ፤ ባንክ እየዘረፉ፤ የከባቢ የመንግስት ባለስልጣናትን እየገደሉ ያሉት የኦሮሞ ነጻ አውጪ ታጣቂዎች በወለጋና በአካባቢው የሚያደርሱትን ግፍ መንግሥት ለመግታት የጀመረውን ወታደራዊ ዘመቻ በመቃወምና መግለጫ በማውጣት ግን የመጀመሪያ ሆነዋል። የሚያዋጉን ከተማ ውስጥ ተቀምጠው በተለያየ የሴራ ስልት ለመሆኑ ይታወቃል። ባንጻሩ ሥልጣን ተቀማሁ የሚለው ሃይል ደግሞ በትራፊዎቹ ባልደረቦቹ ወታደሩን ከማመስ አንስቶ እስከ ኢኮኖሚ አሻጥር እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል። ግን ሁሉም እንደ ቁራ ጭኽት አሰሚ በሆነበት ሃገር ተበደልኩ እንጂ ለተበደለ ልቁም የሚል የለም። በትግራይ ዛሬም ያው ጦር ሰበቃው ተጧጡፏል። የትግራይ ህዝብና መንግሥት ለሆነው ነገር ሁሉ ተዘጋጅቷል ይሉናል። እኔ የሚያሳዝነኝ እነርሱ እየበሉና እያበሉ ልጆችና ዘመዶቻቸውን ውጭ ሃገር ልከው የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነጥለው ያለፈው አልበቃ ብሎ ዛሬም መነገጃ ማድረጋቸው ነው። የትግራይን ህዝብ የሚወረው የለም። ራሱንም መከላከል ይችላል። ደግሞ ትግራይ ተወራ ሌላው የሃገሪቱ ክፍል ዝም ብሎ እንደማያይ ወያኔ በውል ያውቃል። ግን የውሸት ፓለቲካ ሁልጊዜ ልንጠቃ ነው በማለት የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ከበሮና ክራር ማስመታት የቀደመ የፓለቲካ ስልታቸው ነው።
  በአማራ ክልል መሪ ናቸው የተባሉት ደብተራ እንደ ደገመበት ሰው አይናቸው ፈጦ፤ ጆሮአቸው ደንቁሮ በደንበር ገተር ሲራመድ አታድርስ ያስብላል። እንወክለዋለን የሚሉት ህዝብ በኦሮሞ ጽንፈኞች ተራ በተራ እየተገደለ፤ እየተፈናቀለ፤ እየታፈነና ለአረብ መንጋ እየተሸጠ የቆምነው ለአማራ ህዝብ ደህንነት ነው ይሉናል ካሜራ ፊት ሲቆሙ። ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎችን እጅ ጠፍረውና ከሥራ አባረው ሙያ አልባዎችን ባለሙያ አርገው በመሾም በቃላት ድርደራ ብቻ ህዝቡን ያታልሉታል። ለነገሩ ያው ከወያኔ ጉያ የወጡ ስለሆነ ስልታቸው በ 27 ዓመቱ ከተካኑበት ከመለስ መጽሃፍ ነው እኮ። የላቀ እይታ የት አለና። ክልልህና ክልሌ! አቶ ደርበው ከላይ ከ 1-24 የዘረዘሩት የመከራ ዶፍ በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም ፓሊስ ቆሞ እያየ ነው። በአዲስ አበባ የባንክ ዘረፋውን ያጧጧፉት፤ የመኪና ስርቆትን የቀን ተቀን ወሬ ያደረጉት፤ ሴቶችን አፍነው በመውሰድ የግዳጅ ሴተኛ አዳሪ የሚያደርጉት በዘራቸው ዙሪያ የተደራጅ በውስጥ አዋቂዎች (በሰራተኞችና በዘበኞች) እየተመሩ ነው። የንግድ ቤቶች ዘረፋ እና በእሳት መለኮስ ሆን ተብሎ ከዚሁ የሴራ ፓለቲካ ጋር የተያያዘ ነው።
  የአብይ መንግሥት ሊታሰሩ የሚገባቸውን ለማሰር አቅም ያጣ፤ ወንጀለኛው በክልሉ የሚደበቅበት፤ ፍትህ አጣን የሚሉ ዘራቸው የሚጠየቅበት መንግሥት እየመሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም ቢሉ መሬት ላይ ከምናየው ጋር ስለማይገናዘብ እምነታችን አመንምኖታል። ወያኔ የጦር ከበሮ መደለቁም የመሃል መንግሥትን ለማስፈራራት ሆን ተብሎ የተፈጸመ ይመስላል። ከሻቢያ ጋር መላተም ግን እንደማይፈልግ ደጋግሞ ተናግሯል። ለዚያም ነው ጌታቸው አሰፋን በጊዜው ለማገት የሄድትን ወታደሮች አግተው መጨረሻ ላይ የፈቷቸው። አማራ ጠላትህ ነው በሚል የፈጠራ ትርክ እልፎችን ከምድረ ገጽ ያጠፋው ወያኔ ዛሬ የወያኔ ገጽታ ግልባጭ በሆነው የኦሮሞ ልክፍተኞች በዚህ ህዝብ ላይ የሚፈጸምበትን መከራ ለተመለከተና ለሰማ እንቅልፍ ይነሳል። ሃገርን መታደግ የሚቻለው ከክልልና ከቋንቋ ፓለቲካ ሲወጣ ብቻ ነው። ሁሉ በየጎጡ መንግስት በሆነበት የሃበሻ መሬት ላይ ኑ ሃገር እንዳትፈርስ አብረን እንስራ ማለት ተጨፈኑና ገደሉን ዝለሉ እንደማለት ነው። ገብቶ መሰባበር ብቻ ነው ውጤቱ። ፓለቲካው ተሳክሯል። በሃገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የድርቡሾች ሥራ እየተሰራ ነው። መስጊድ ማቃጠል፤ የመቃብር ቦታ አንሰጥም ማለት፤ ቤ/ክርስቲያን ማቃጠልና ማፍረስ ከዚሁ የድብቅ የፓለቲካ ሴራ አንድ ንዳድ እሳት ነው። የዶ/ር አብይ መንግስት በመረጃ የትላንትንም ሆነ የዛሬ የፓለቲካ አጫፋሪዎችን መንጥሮ በማሰር ሃገሪቱን እፎይ ማድረግ እስካልቻለ ድረስ ሴራው ራሱንም የሚያቃጥለው ለመሆኑ ከአሁኑ መገመት ይቻላል። የዘርና የጎጥ ፓለቲካ ለማንም አይበጅም። መደመርም በሃሳብና በተግባር ካልሆነ ዝም ብሎ ለሰላም ነው የገባሁት በማለት እሳት እየጫሩና ከውጭ ሃይሎች ጋር እየተሻረኩ ህዝባችን ሰላም መንሳት ለማንም አይጠቅምም። ዘረኝነት የሙታኖች የፓለቲካ ዘይቤ ነው! ቋንቋም መግባቢያ እንጂ በቋንቋህ ስለተማርክና ሰለ ጻፍክ በሂሳቡና በሳይንሱ ትልቃለህ ማለት አይደለም። ማንኛውም ቋንቋ ሙሉዕነት የለውማና! ባህርም አያሻግርም። ዝም ብሎ መዳከር ነው። በማጥ ውስጥ እንደተያዘ የመኪና ጎማ። አይ ፓለቲካ በአፍንጫዬ ይውጣ!

 2. –Shouting for the dead is not going to bring the dead back to life .
  –Shouting for the dead doesnot protect the once that are next to be murdered .
  –Shouting is what the genocider Muktar Kedir want us to do, so he can aim target.
  -Both Abiy and Jawar are Muktar Kedir’s mercinary goons.
  -Abiy is as guilty as Jawar .

  SHOUTING FOR ABAY WATER IS WHAT WE SHOULD DO NOW ASAP ,
  EVERY SECOND MATTERS !!!!!!

  WATER IS LIFE!!!

  By the year 2050 Ethiopia’s population is expected to be close to 175,000,000 and by the year 2100 Ethiopia’s population is expected to be at least more than 300,000,000 ( three hundred millions) .

  If rights from Abay water is sold to Sudan and Egypt, then future generations of the north Westerners Orthodox Ethiopians will have to rely on water they get from further South and further Eastern part of the country, the areas where all the anti Orthodox anti Amara sentiment is brewing now.

  With relying on water from the Jihadist sentiment they will be forced to convert to Oromo Gadda since they will be unable to survive without water.

  The fathers of OPDO Muktar Kedir along with Abadulla Gemeda are preaching Gadda right now with Workneh Gebeyehu hunting down Orthodox refugees in Kenya refugee camps . While all these is done Their psychopath agent Abiy is finalizing the selling of Abay , instigating the war between Eritrea and Amara and Tigray while northern Ethiopians are too busy protesting about 21 abducted while not protesting about the future generations hundreds of millions of Orthodox Ethiopians state sponsored attack jihad that is in the making right now .

  #DoNotSellNileInMyName

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.