ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም በሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ዙሪያ በማተኮር ውይይት አድርገዋል።

በሴቶች ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲሁም ሴቶችን ለማብቃት የሚከናወኑ ተግባራትን የካናዳ መንግስት እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የሴቶችን ሚና ከማሳዳግ እና ወጣቶችን ከማብቃት አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ እና በጋራ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች ተወያይተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም በማተኮር መወያየታቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ በኋላም ሁለቱ ሀገራት በጥምረት ለመስራት የሚያስችሏቸውን አሰራሮች እንደሚዘረጉም ተነስቷል፡፡

ኢትዮጵያና ካናዳ ለረጅም ጊዜያት በበርካታ ዘርፎች በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውም ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ እንደምትገኝ መታዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ለሴቶች የተሰጠውን የአመራር ዕድል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድንቀዋል፡፡

ከዓለም ነበራዊ ሁኔታ በመነሳት ሀገራቱ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ተናግረዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.