የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጀምሯል


ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አባበ በሚገኘው የኀብረቱ ዋና መስሪያ ቤት በርካታ መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

መሪዎቹ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ጉባዔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ”የጦር መሳሪያ ድምጽን ማጥፋት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ሲጀመር ህብረቱን ለአንድ አመት በሊቀመንበርነት ያገለገሉት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ሃላፊነቱን ለሚቀጥለው አንድ አመት ለሚይዙት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሳይሪል ራማፎሳ ያስረክባሉ።

የመክፈቻ ንግግሮች ከቀረቡና የጉባኤው መሪ ሃሳብ ይፋ ከተደረገ መሪዎቹ በዝግ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መሪዎቹ በዝግ ይመክሩባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ለውጥ እና በአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን የተመለከተ ሪፖርት ማዳመጥና ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚገኙበት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሰላምና ጸጥታን በተመለከተም የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት እና አህጉራዊ የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ ላይ ምክክር ይደረጋል።

በተጨማሪም እ.አ.አ በ2020 በአህጉሩ ጸጥታ ለማስፈን የተዘጋጀው የተግባር ፍኖተ ካርታ አፈጻጸም ላይ መሪዎቹ እንደሚመክሩ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢ.ፕ.ድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.