በአማራ ተማሪዎች እገታ ላይ መንግሥታዊ ትዕይንተ ድራማው ቀጥሏል – አቻምየለህ ታምሩ

አሁን እየተደረገ ያለው ነገር እንዲህ ነው። ሁለት አማራ ወጣት ሴቶች ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ከተማ ፣ ቀበሌ 18 ተነስተው ወደ ባሕር ዳር አካባቢ ለፀበል ይሄዳሉ። ከፀበል ቦታ ተመልሰው ባሕር ዳር ከተማ እንዳረፉ በአንድ የደኅንነት ሰው እይታ ውስጥ ገቡ። ይህ ሰው ነጋዴ እንደሆነ በመግለፅም ይተዋወቃቸዋል። ይህ ሰውም ሴቶቹን በቅንንነት በመቅረብና በማግባባት ለተለያዬ ቀናት በማግኘት ሲጋብዛቸውና ሲያዝናናቸው ቆይቷል። በመቀጠልም እነዚህን ሴቶች በገንዘብ አታሎ በፍቅር ለመጣል አንዷን ይህ ነጋዴ ተብዬ የደህንነት ሰው፤ ጓደኛዋን ደግሞ ለአንድ በእድሜ ሽማግሌ ለሆነ ሰው ለፆታዊ ግንኙነት ቢጠይቋቸውም፤ ሴቶቹ ግን አሻፈረኝ ይላሉ።

ከዚያም የልጆቹን የኢኮኖሚ አቅም እንደመጫዎቻ ካርድ አጥብቆ የያዘው የደኅንነቱ ሰው አንድ ስራ ሊያሰራቸው እንደሚፈልግና ለስራውም እስከ ቤተሰቦቻቸው ድረስ ሕይወታቸውን የሚቀይር ጠቀም ያለ ገንዘብ ሊከፍላቸው እንደሚችል ይነግራቸዋል። ሴቶቹም በጉጉት ስራው ምን እንደሆነ ሲጠይቁት ከታጋች ተማሪዎች መካከል እንደነበሩና በውሸት “ታግተናል” እንዳሉ ለሚዲያ እንዲገልፁ ይጠይቃቸዋል። ይህ ሰው የተለያዬ ሀገራት ገንዘቦችን ከመያዝና ከማግባባት ክህሎቱ በተጨማሪ ሽጉጡን በማሳየት የስነ ልቦና ጫና በሴቶቹ ላይ በማሳደር ሀሳቡን እንዲቀበሉ ያደርግ ነበር።

በመቀጠልም «ከታጋች ተማሪዎች መካከል የመጣን ነን በማለት አማራነታችንን ተጠቅመን የአማራ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እንዲነሳሳ በፖለቲካ ድርጅቶችና በግለሰቦች ምክርና ድጋፍ ተደርጎልን ታግተናል ብለን ተናግረናል። እኛም መንግሥትንና ሕዝብን አሳስተናል። ስለዚህ መንግሥትንና ሕዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን።» ብለው እንዲናገሩ ለ10 ተከታታይ ቀናት በባሕር ዳር ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይቷል። ከስልጠናው በኋላም መንግሥት ወደ አዲስ አበባ በመውሰድ ለደኅንነት ሲባል ለጊዜው ስሙ የማይጠቀስ ትልቅ ሆቴል እንዳያርፉና ለሁለት ቀናት እንዲቆዬ አድርጓል። በሁለት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው ውስጥ ለደኅንነት፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለሴቶች ጉዳይና ለሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በስልጠና እንዲያጠኑት የተደረገውን የድርሰት ቃል እንዲሰሰጡና ቃላቸው እንዲቀረፅ ተደርጓል።

እነዚህ አማራ ወጣት ሴቶች ስማቸውና ግላዊ ማንነታቸው የሚከተለው ነው።

1. ሸዋዬ ገነት ተዘራ፡ ሸዋዬ ማለት በተለቀቀው ፎቶ ላይ ጥቁር ሰማያዊ የስፖርት ጃኬት የለበሰችው ልጅ ናት። ሸዋዬ ሁለት ልጆች ያሏት ስትሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪም አይደለችም።

አድራሻ፦ማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ፣ከተማ ፣ቀበሌ 18 ዕድሜ 18 የትምህርት ደረጃ 8ኛ ክፍል

2. ቅድስት ጋሻው አበበ፡ ቅድስት በተለቀቀው ፎቶ ላይ በአግድም ነጭ ሰንበር ያለበት ቀይ ቲሸርት የለበሰችው ናት።

አድራሻ-:ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ዕድሜ 17 ብትልም የተመዘገበ ግን 18 ተብሎ ሲሆን የትምህርት ደረጃ፦ 8ኛ ክፍል

ልጆቹ ድርሰታዊ ቃላቸው በተለያዬ የመንግሥት መስሪያ ቤት እንዲቀረፅ ከተደረገ በኋላ መንግሥት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚመልሳቸው ቢጠብቁም «ማጭበርበር» የሚል የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸው፤ ማለትም «ሳይታገቱ ታግተናል ብለው እንዳጭበረበሩ እንዲሁም መንግሥትና ሕዝብን እንዳሳሳቱ» ተደርጎ እያለቀሱ ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ድራማ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በአዲስ አበባ በፖሊስ ተይዘው ወደ እስር ቤት ገብተዋል። እነዚህም፡-

1 ፍቅርተ ቸኮል ተገኝ ስትሆን አድራሻዋ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሲሆን ክስ፦ ከአጋች ጋር መመሳጠር ይ የሚል ነው። ይህቺ ሴት የታጋች እኅት ነች።

2 ወንድሜነህ ዋሴ ልመንህ አድራሻ ፦አዲስ አበባ ከተማ ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ ሰፈር ስራ፣ የሞሐ ለስላሳ መጠጦች የጥበቃ ሰራተኛ፤ ክስ፦ ሰው እገታ ይህ ሰው ከስራ ቦታው በፖሊስ ተይዞ ወደ ስር ቤት የተወሰደ ነው። ቃሉን ሲሰጥም ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልፆል።

ማስታወሻ፦ ወደ ወለጋ ማለትም ተማሪዎቹ ወደ ታገቱበት ቦታ የተጠናከረ ኃይል ከመላክ ይልቅ ይህን ድራማ ”የተዋጣለት” ለማድረግና የአማራን ሕዝብ ለቅሶ ለመቀማት ከደኅንነትና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጡ አባላትን የያዘ የልዑክ ቡድን ወደ አማራ ክልል የዘመተ ሲሆን የታጋች ቤተሰቦችንም በዛቻና ማስፈራሪያ ድምጻቸውን እያፈነ ይገኛል። ወደ ጎንደር የተሰማራው የምርመራ ቡድን ቀደም ብሎ የቀረበውን ድራማ እውነት አድርጎ በማቅረብ ባለፈው ሰሞን ስለ ታጋችቾች እውነተኛ ማስረጃ የሰጠችውን ከታገተችበት ያመለጠችውን ልጅ « ባልደካሄደ እውነተኛ ጠለፋ በመንግሥትና ሕዝብን በመዋሸት» ክስ ለመያዝ የፍርድ ቤት ትዛዝ ይዞ ሂዷል።

2 COMMENTS

 1. ስማ አቻምየለህ – መቸውንም ቢሆን የተነበበና የታየ ነገር ሁሉ በአለንበት ዓለም እንዳለ እንደማይዋጥ ከእኔ ይልቅ አንተ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ይሁን እንጂ አንድን መረጃ ሰው አይቶም ሆነ አንቦ ለመረዳት ማገናዘቢያ ሃሳብ ማለትም ያለፈ ታሪክ ወሳኝ ነው። አሁን አንተ የምትለው ሴራ ያለፉ መንግስታትን የአሰራር ስልት የተከተለ በመሆኑ አይደረግም በማለት ጨልጦ መካድ አይቻልም። ምሳሌዎች ልስጥ
  አስመራ – ደርግ ስብስቦ ያሰራቸው እናትና አባቶች አንድ እስርቤት በራፍ ላይ ተከማችተዋል። ግማሹ ምግብ ለማቀበል፤ ሌላው ደግሞ ታሳሪው ጸሃይ ወጥቶ ሲሞቅ በጨረፍታም አይቶ ለመመለስ ነው። በዚህ መካከል ለረጅም ጊዜ እስረኞች የነበሩ ሰዎች ያለወትሮአቸው ለጸሃይ ሳይወጡ ይቀራሉ። እናትም አባትም ይላቀሳሉ። አታልቅሱ ለትምህርት ልከናቸው ነው አለ የደርጉ ካድሬ። እነርሱ ግን አፈረ ተመልሶባቸዋል።
  ጎንደር – እናት ልጇን ልትጠይቅ እስር ቤት ትገኛለች። ልጆ ሊጠይቃት በሰው ተደግፎ እያቃሰተ ሲመጣ እናት ተደናግጠው ይወድቃሉ። እንደ ወደቁም በዚያ ጸጥ ይላሉ። በአዲስ አበባ ወያኔ ወደ ሃያ የሚሆኑ ሰዎችን እግርና እጅ አስሮ በከተማው ጉድጓድ አስቆፍሮ ይረሽናቸዋል። በደላቸው አማራ ሆኖ መገኘታቸው ነው። ከአጭር ጊዜ በህዋላ ስፍራው ለመንገድ ሲቆፈር ይገኛሉ (በጊዜው የወጡ ዜናዎችን እይ) ወዲያው የወያኔ ደህንነቶች ስራውን አስቁመው ቀሪ አስከሬናቸው ተለቃቅሞ ሌላ ቦታ ይጣላል። በአይኑ ያየ የመንገድ ሰራተኛ ያኔ እንደተናገረ የደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ለብሰዋል እጅና እግራቸው ታስሯ።
  ደርግ ለሃገሪቱ በመቆም የሃገሪቱን ዳር ድንበርና አንድነት ሊያስከብሩ የሚችሉትን ነው ተራ በተራ የመነጠራቸው። ወያኔ የሰራውና የሚሰራው ለመላው ሃገሪቱ ገሃድ በመሆኑ መድገም አያስፈልግም። ሃገሪቱ የመከራ ዶፍ የማያባራባት ሁልጊዜ በእንባና በሰቆቃ የምትታመስ ሃገር ናት።
  መንግስት ነኝ ባዮች በሄዱና በመጡ ቁጥር ቀንደኛ ጠላት አድርገው የሚፋለሙት አማራን ነው። ይህ ለምን ሆነ ብለን ከጠየቅን 70 ዓመት ያህል ወደ ኋላ ተጉዘን የሴራውን መዘዝ ማወቅ ይኖርብናል። ይሁን እንጂ የአማራን ጥላቻ ጣራ ላይ ያወጡት ሻቢያና ወያኔ ናቸው። አሁን ደግሞ ጅሎቹ የኦሮሞ ፓለቲከኞች ጭራሽ ነገሩን ሁሉ አኞ አረጉት። በአማራ ህዝብ ላይ የተሰራውና የሚሰራውን ግፍ ዘግቦ የያዘ አንድ የሚስጢር መረጃ እንዲህ ይላል። እጠቅሳለሁ።
  “አማራንና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ካላጠፋን በጤና መኖር አንችልም” ይላል። ከዚያም አስቀጥሎ በሁሉም መንገድ ኢትዮጵያዊነትን ማዳከም ካለ በህዋላ ለዚህም እንዲረዳ የአማራን ህዝብ ቁጥር ማሳነስ፤ ከተለያዪ ክልሎች ማስወጣት፤ በንግድና በትምህርት ተቋማት ያሉትን አማራዎች ማበራየትና ማዳከም በማለት ሌሎች እዚህ ላይ ልጠቅሳቸው የማልችላቸው ነገሮች በማከል አማራን በሴራና በተንኮል ከነ ቋንቋቸው ማጥፋት ይላል።
  በመሰረቱ ታፈኑ የተባሉት ተማሪዎች በህይወት ያሉ አይመስለኝም። መንግስት ነይ ባዪ ሲዘባርቅ፤ የኦነግ ተወካይ ደግሞ በስፍራው ሄጄ ባደረኩት ጥናት ግራ ገብቶኛል በማለት ይወሻክታል። አንተ በጽሁፍ ላይ ያሰፈርከው አይደረግም አይታሰብም ማለት ጭራሽ አይቻልም። ሲሰራ የነበረ፤ የተሰራ ነው። የአማራን መሪዎችና ተቆርቋሪዎች በስመ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ የጠራረገው ሴራ ጄ/ል ጻረ በአማራ ጠባቂያቸው እንደ ተገደሉ አድርጎ ማቅረቡ አማራንና የትግራይን ተወላጆች ለማላትም ሆን ተብሎ የተሰራ የፓለቲካ ሴራ ነው። ግድያው የተፈጸመው በሌላ ወገን ነው። የጠ/ሚሩ ጠባቂ በሆቴሉ አዳማ ላይ ማን ገደለው? ዛሬ አማራ በመሆናቸው ብቻ የአዲስ አበባንና የከባቢውን እስር ቤቶች የሞሉት ወንጀል ሰርተው ነውን? በየጊዜው የዚያ ሰው ሱቅ ተቃጠለ፤ የዚህ ሰው መኪና ተገለበጠ፤ በዚህ ክልል እሳት ተነስቶ ይህን ያህል ሃብት ነደደ የሚባለው መብረቅ ስለመታው ነው? አይደለም። ከሴራቸው አንድ የኢኮኖሚ አውታሩን ማዳከም ነው። እነዚህ አሁን ተታለው በመሳሪያና በገንዘብ ተታለው በውሸት የታገቱት የአማራ ሴት ልጆች የመጀመሪያ አይደሉም። ከባህርዳር፤ ከደብረ ማርቆስ፤ ከደሴ ተለቃቅመው በተመሳሳይ ሁኔታ ለአረቦች የተሸጡ፤ በሃገር ውስጥ ተወስደው ሚስትና ሰራተኛ የሆኑ ሰዎች መረጃ አለ። ታዲያ አማራ አማራ ለአማራ የሚለው የጊዜው የፓለቲካ ጡሩንባ በሆነው ባልሆነው ከመጨፈር ይልቅ ሰውን በማደራጀት ጥቃትና ማታለል ሲደርስባቸው ሰዎች ለድረሱልኝ እርዳታ የሚደውሉበት የግልጽና የህቡዕ መስመር በማዘጋጀት እነዚህን የፓለቲካ አተላዎች ማድረግ በተቻለ ነበር። ይህ ግን አይደለም እናቱን ገቢያ አውጥቶ የሚሸጥ ትውልድ ለሌላው እህቱ አይገደውም። መኖር ለብዙዎች ዛሬ ብቻ እና ለእኔ ነውና! የአማራ ህዝብ ራሱን አስተባብሮ አጥቂዎችን መከላከል እስካልቻለ ድረስ ወያኔ ካጠፋቸው 2 ሚሊዪን አማሮች የበለጠ የኦሮሞ ብሄርተኞችና አጋሮቻቸው የሚያደርሱት ጥፋት ትውልድ አምካኝ ይሆናል። ሙያ በልብ ነው። ያልጠረጠረ ተመነጠረ ነው። የእነዚህን ልጆች ሁኔታ ለዓለም የማስታወቅ የሁሉም ወገን ሃላፊነት ነው። በቃኝ!

 2. LET FIRST LADY ZINASH LEAD THE RESCUE MISSION!!

  Army Lt. Colonel Abiy Ahmed got awarded the army Lt. Colonel post not because he earned it, he was awarded the army Lt. Colonel post so the United Nations Peace Keeping Mission pays him a colonel salary in dollars , he talked his Tigrigna way to get the Army Lt. Colonel post through corruption salary division. Abiy didn’t fire a single bullet at the Eritrean soldiers at the Ethio-Eritrean badme war since he wasn’t near enough to see the Eritrean soldiers , he run back to the command center when the war started and he stayed there talking his tigrigna way as coffee errand boy at the command centers the whole time the war was being fought.

  Abiy’s skill is all about spying politics detective , he contributed so much to Meles Zenawi spy agency with no care abput what consequences his spying actions brings to Ethiopia, as long as he gets admiration from Meles Zenawi and his wife Zinash is happy with him that’s all he cared for. Nowadays it is rumored Abiy’s wife Zinash is not willing to speak to Abiy in private anymore because the Amhara students abduction case is getting her angry at him, she even offered to lead a rescue mission herself . He wanted to solve it through his spy comrades to avoid other options but there was nothing to be spied so they resorted to create fake story .

  Abiy has no conscious of his own, that’s why he says tedemer tedemer, Many of those that worked as spies to Meles Zenawi did have some degree of conscious Abiy had none he still donot, many refrained from the immoral spying for Meles Zenawi but Abiy didn’t until Meles died. Abiy got hundreds of unsuspecting Amharanized looking peacefull pedestrians of Addis Ababa gunned down by claiming they were participating in the election protest of 2005 . To avoid confrontation with the mass that were protesting Abiy decided to gun down honest law abiding pedestrians that were not even near where the protest was going on , he has no conscious that regrets it.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.