በገዛ ህዝቡ ላይ ከሌላ ሀይል የሚዶልት መንግስት የትግራይ መንግስት ሊሆን አይችልም፤ የኔ መንግስት ሊሆን አይችልም – አቶ ስየ አብርሃ

“ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉዳይ ዝምብለን አናይም፤ ያገባናል ምናምን ያለው ጉዳይ ሁለቱንም መንግስታት ከተገናኙ በኃላ የተባለ ነገር በመሆኑ ምንድነው አንድምታው? የሚለው፣ ያሳስበኛል። አቶ ስየ አብርሃ

እኛ ትጥቅ ትግል ጀምረን፣ ከዜሮ ከትንሽ ተነስተን በ17 ዓመት ጦርነት፣ ሰራዊት ፈጥረናል። ትልቅ ሰራዊት። አሸናፊ፣ ውጤታማ የሆነ ሰራዊት። ኮሮች ደምስሰን ኮሮች ፈጥረናል። መከናይዝዶች ደምስሰን መከናይዝድ ፈጥረናል። ሙሉ የተደራጀ ከነ መድፉ፣ ከነ ታንኩ ትልቅ ሰራዊት ይዘን ነው አዲስ አበባ የገባነው።

ሰራዊት መገንባት እናውቃለን፤ ግን ጦርነት አንፈልግም። እናውቀዋለን ጦርነት ምን ማለት እንደሆነ። የሚያስከትለው ጣጣ የሚያስከፍለው ዋጋ እውቀዋለን። እኛ ያላወቅነው ማን ያውቃል? ታቅፈነው እኮ ነው እየኖርን ያለነው።

የዛ ሁለት ጦርነቶች ቁስል ታቅፈነው ነው እየኖርን ያለነው። ጦርነት የሚያውቅ ጦርነት ይፈራል። ጦርነትን አያቀልም። ስለሆነም አናቀለውም፤ አንፈልገውም፤ አንመኘውም።

 ጦርነት ከመጣብን ግን እንዴት መመከት እንደምንችል፣ ጉራ አይደለም፤ እናውቀዋለን፤ እናውቀዋለን!

እኛ ይሄ ሁሉ ሀይል ይዘን፣ ትጥቅ ይዘን የሽግግር መንግስት 1983 ዓ/ም ስንመሰርት፣ እኔ በዛ ዘመን የመከላከያ ሚኒስትር ነበርኩ፤ የዛን ጊዜ ምክር ቤት የመከላከያና የደህንነት ኮሚቴ ሊቀ መንበርም ነበርኩ። የአገሪቱ ፀጥታ እንዴት እናስጠብቅ? በሚል ያ ኮሚቴ ተመካክረዋል። ያ ኮሚቴ ውስጥ ኦነግም ነበረ። አቶ ሌንጮ ለታ ነበረ። የአገሪቱን የመከላከል፣ ዳር ድንበር የማስከበር ሀላፊነት የኢህአዴግ ሰራዊት ይውሰድ፤ በሚል ተስማምተን ከዛኔ ጀምሮ የህወሓት ሰራዊት ከነ ሙሉ ችለታውና ከነሙሉ ትጥቁ ለመንግስት አስረክበናል። የሀገር ድንበር፣ የሃገር ልዓላዊነት መጠበቅ የማዕከላይ መንግስት እንጂ የአንድ ፓርቲ የአንድ ክልል አይደለም፤ ፓርቲ ከእንግዲህ በኃላ የታጠቀ ሀይል አያስፈልገውም፤ በሚል። ይህንን መረሳት የለበትም።

አሁንም የሀገርን ዳር ድንበር የማስጠበቅ ሀላፊነት የማዕከላይ መንግስት ነው። ይህንን የማያደርግ የማዕከላይ መንግስት፣ በገዛ ህዝቡ ላይ ከሌላ ሀይል የሚዶልት መንግስት የትግራይ መንግስት ሊሆን አይችልም፤ የኔ መንግስት ሊሆን አይችልም። እንደዚህ አይነት መንግስት የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሶማሊ መንግስትም ሊሆን አይችልም።”

ነባር የህወሓት ታጋይና አመራር ስየ አብርሃ
ሰሙኑ ከ TMH ጋዚጤኛ መድህን ገብረስላሴ ጋር ከነበረው ቆይታ የተወሰደ

6 COMMENTS

 1. Woyane and Shabiya donot like peace , they biitch all their life about Famine , about derg , about each other , about somebody …. all throughout their biitching existence because they can not live in peace.
  . COMPLAIN COMPLAIN …Complain ,THAT’S ALL THEY DO.

  Ethiopia got more serious problems now than once again get caught up in the middle of the Woyane Shabiya marriage divorce shootout drama . Their drama costed us too much in the last four decades , it got the country in the unmanageable state we are in now. It is time for this anti peace Woyane Shabiyas politics get neglected . Let them work it out on their own. We won’t give you our ear just so you complain complain and complain forever , nobody wants to hear that year after year decade after decade , biitch towards each other’s ear if you want to, see if you like it, because the rest of Ethiopians are tired of it. Abiy was raised by Woyane too that’s why he is interested in this biitching talk with Isayas , he doesn’t know any better.

  Woyane and Shabiya are Biitching from day one ever since Woyane and Shabiya got formed , non stop until now, it must be a record.

 2. በታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተደረገ ያለው ድርድር አሳዛኝ ነው፣ ፈፅሞ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መሄድ አልነበረበትም፣ ይህ ደግሞ የአመራር ችግር ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው – ዶክተር ደብረፅዮን

 3. The treason Siye and his TPLF fellows committed against Ethiopia can be forgiven but will never be forgotten.
  They have inflicted an irreparable damage on Ethiopia as a country and its national interests. They were the foot soldiers of president Isaias Afewerli whom they accuse of interfering in the internal affairs of Ethiopia. They have sacrificed tens of thousands of the poor from Tigray to serve the causes of the Eritrean separatists.

 4. The late TPLF supreme chief Meles Zenawi dismissed Siye Abraha from the organization and dumped him into prison. As was told then the main reason for siye`s dismissal and arrest was his disagreement with the late Tigray supreme leader over the war with Eritrea. He was blamed for heading the faction within the TPLF that rebelled against the supreme leader. But his rebellion cost him and his brothers very much. Siye is from the Southern part of Tigray and is not considered as pure Tigrayan as those hailing from Adwa, Shire and Axum. Normally those from Siye`s region are considered as second class Tigrayans or mixtures with the Amharas. .

 5. ” በገዛ ህዝቡ ላይ ከሌላ ሀይል የሚዶልት መንግስት የትግራይ መንግስት ሊሆን አይችልም፤ የኔ መንግስት ሊሆን አይችልም”
  በምን ሞራል መሰረት ነው ይሄን ልትናገር የምትችለው ??
  ሀገራችንን ለመገንጠል ካሴሩ ጋር ኣልተባበራች ሁም ?? የመቶሚሊዮን ህዝብ ወደብን ኣላስረከባች ህም ?? በኣለም ቀርቶ በኣፍሪካ የተወገዘ ሁዋላ ቀር የዘር ፖለቲካን ሀገራችን ተክላች ሁ ኣላተራመሳች ሁንም ?? ከሀግራችን ኣልፎ ለኣፍሪካ ኩራት የሆኑ በኢትዮጵያዊነታቸው ላይ ቅንጣት ጉድፍ የሌለባቸውን መሪዎቻ ችንን ሰድባችሁ ፣ ኣዋርዳችሁ ለዶንቆሮዎች እና ነውረኞች መሳለቂያ ኣላደረጋች ሁም ? ኣንድ ኣርጋ ያሰተባበራችንን ባንዲራችንን ኣላዋረዳች ሁም ??
  ሌላው ‘ሰራዊት መገንባት ፣መመከት’ ገለ መሌ የምትለው ፣ደርግን ኣሸንፈናል በሚል ትእቢት ነው ።ደርግ በራሱ ምስጥ እንደበላው እንጨት የተፍረከረከ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የተገሸገሸበት፣ሌላው ቀርቶ ምንም ያልጎደለባቸው ጄኔራሎቹ ሊያስወግዱት የሞከሩበት ቅርጽ እንጂ ይዘት የሌለው ውስጡ ባዶ የሆነ ስር ኣት ነበር። ይህ ባይሆን ኖሮ፣ የትህነግ የሶስተኛ እና ኣራተኛ ክፍል ጄኔራሎችህ ፣ ከእውቁ ሀረር ሚሊቴሪኣካዳሚ፣ ፣Royal Military Academy Sandhurst ,UK , School of Saint -Cyr , France, General Staff Academy , Moscow and others የተመረቁ የጦር ኣበጋዞችን በግል ችሎታቸው ያሸነፉ ይመስለሃል ???
  ኣሁን ጊዜው ( landscape ) ተገላቢጦሽ ሆኖኣል፣ በጅምላ ያሰራችሁት፣ ያሰቃያችሁት፣ የገደላችሁት፣ ጥፍሩን የነቀላችሁት፣ ግብረ ሰዶም የፈጸማችሁት፣ ህዝብ ከልቡ ጠልቶኣችዋል።ህዝብ ካልተባበራችሁ እመነኝ ከመቀሌም ኣታልፉ።በዚህ ኣጋጣሚ ለእውነተኛ ዲሞክራሲብለው የተሰው ትግራዊ ወገኖቼ ላይ ያለኝ ክብር እንደተጠበቀ ነው። My comments are targeted at the leadership not to the rank and file members of the party nor The Tigrean People.

 6. Aite Seye`s lies can be exposed easily. The TPLF disbanded the Ethiopian defence forces and replaced them with its own. The TPLF continued to control and command the defense forces it has established until it lost power in 2018. Then the key and sensitive positions in the army were filled with the Tigray personnel as the TPLF leaders do not have any trust in non-Tigray members. When the war with Eritrea broke out, the TPLF was forced to call back to duty the former army service men. It was known then that Seye and Meles were at odds with each other over this issue (calling back the former officers).

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.