ትግራኛ ቋንቋ እያለህ የትግራይ ጉዳይ በተለይ የለካቲት11የተግራይ ህዝብ ትጥቅ ትግል የተጀመረበት ቀን በአማርኛ እየጻፍክህ የትግራይ ጉዳይ ሚስጢር አሳልፈህ ትሰጣለህ ?

አስገደ ገብረሰላሴ

ስለ በአማርኛ ቋንቋ መጻፍ በሚመለከት እጅግ ቡዙ ወገኖች በአንድ አንድ ጽንፈኛ የአማርኛ ኢሊቶች ተናጋሪዎች አማርኛ ቋንቋ በእግዚአቢሄር ለብቻቸው የተሰጣቸው ይመስል በኢትዮጱያ ህዝብ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ በትግርኛ ተናጋሪዎች ባሳደረው ተጽእኖ ተገፋፍታችሁ አማርኛ በጠባብ አመለካከት እየተመለከታችሁ ቋንቋ የኛ መሆኑ ባለመገንዘባችሁ ጭምር በፌስቡክ ፣በጋዜጣ በአማርኛ ስለምጽፍ በተደጋጋሚ ስደብ አዘል ወቀሳ ታወርዱብኝ አላችሁ ።እኔም ለአስተያየታችሁ ክብር በመስጠት ለምን አላማ በአማርኛ እንደምጽፍ በግልጽ ጊዜ ሰጥቼ አብራርቸላችሁ ነበር ።

አስገደ ገብረሰላሴ

ከአስተያየታችሁ በመንደርደር አንድ ነገር እንድናገር ፍቀዱሉኝ ፤በመሰረቱ የታሪክ ሙሁራን እንደሚነግሩን ከሆነ አመርኛ ቋንቋ መፈጠሪያው የተወለደበት ከክርስትና ህማኖት ተያይዞ ከግእዝ ሆኖ በአክስማውያን ነገስታት ከክርስቲያን ሀይማኖት የተወለደ መሆኑ አመርኛ ቋንቋም በመላው ሀገራችን የሀይማኖት ማግባብያ መስበኪያ አድርገው ይሰብኩበት እንደነበሩ ሀቀኛ የታሪክ ጸሀፊዎች ይናገራሉ ።

በተጨማሪ አማርኛ ቋንቋ የቋንቋዎች ገዥ ሆኖ ጨቋኝ ሊሆን ያደረጉት ( ገናና ሊሆን ያደረጉት ) አክሱማውያን የግእዝ ፈላስፎች መሆናቸው ይነገራል ። አመርኛ ቋንቋ ቀስ በቀስ ከመንግስታዊ ስልጣን አሰጣጥ ከአክስማውን የተያዘዘ ስለነበር የመንግስታት የቤተ መንግስት ገዥ ቋንቋ ስላደረጉት እየተወራረሱ ከሀጸይ የውሀንስ ጀምረው ፣አጼ ምንሊክ ፣ጃንሆይ ፣ደርግ ፣መለስ ዜናዊ ፣ሀይለማርያም ደሳለይ ፣አሁን ያለም መንግስት ነው የምንለው ፓርት አላውቅም አመርኛ የሁሉም በሀገራችን ያሉ ቋንቋዎች እንዲጨቁን እና ሀገራዊ ገናና ቋንቋ እንዲሆን አድርገውታል ።

አመርኛ በሀገር ደረጃ የሁሉም በሀገራችን ያሉ ቢሄር ቢሄረሰቦች በግድ የስራ ፣የትምህርት ቤት ቋንቋ ፣ የሁሉም ሀይማኖት ተከታዮች የቃለ ቡራኬ ቋንቋ ሆኖ ስለቀየ እጅግ የቡዙ ህዝቦች የራሳቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋ እያሉዋቸው ተገደው ሌሎች ቋንቋዏች በንጉሶች ጨቋኝ ትእዛዝ መሰረት በገዥው የአማርኛ ቋንቋ ታፍነው ተጉዘዋል ።በመሆኑ አማርኛ በውድም በግድም አመርኛ በመላው ሀገራችን ያሉ ቢሄሮች የአፍ መፍቻ የራሳቸው እያላቸው ተገዶውም ቢሆኑ ከ80 ( 90) % በላይ ህዝባችን አማርኛ ይጽፋል ያነባል ይናገራል ፣ይሰማል ።ሌላ አክስሟውያን አማርኛ ቋንቋ የማግባብያ ቋንቋ አድርገው ሲመድቡ ሀይማኖታቸው መስበካ ብለው የመደቡትም የህዝብ ብዛት ግምት አስገብተው ነበርወይ የሚለው ለታሪክ ፈላስፎች ልተወው ።በህዝብ ብዛት ቢሆን ንሮ እኮ የህዝብ ቆጠራ ቢደረግ አማራ ቢሄር ነው አይደለም ለታሪክ ባለሙያዎች ልተወውና የኦሮሞ ቢሄር ህዝብ በዘልማድ አማራ ከሚባል ቢሄር በሁለት እጥፍ ወይ ከዛ በላይ ይበዛል ። በገዥዎች ተገዶ ግን በአመርኛ እተማረ ፣እተናገረ ፣በአማርኛ እተፈረደ ኖሮዋል ።ፍርድ ቤት ቀርቦ አማርኛ ቋንቋ ባለመቻሉ ተሳስቶ ትርፊ ቃል ከተናገረ ይቀጣ ነበር ።ይህ ይሆን የነበረ አሮሞ ብቻ አይደለም ።በደቡብ ህዝቦች ፣በሱማል፣በአፋር ፣በትግራይ ፣ጋንበላ ፣በቤልሻንጎልም በተመሳሳይ በአማርኛ ቋንቋ ይገዙ ስለነበረ ቋንቋው ተገደው ስለተማሩ አማርኛ ሀገራዊ ጨቋኝ ገዥ የስራ ቋንቋ ሆኖ ቆይቷል ።አሁንም በሀገራችን ያሉ የቢሄር ቢሄረሰቦች ቋንቋዎች በስርአተ ትምህርት (ካሪከለም ገብተው ሀገራዊ ሆነው እስከሚስፋፉ አማርኛ የበላይ የስራ ቋንቋ ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው ።

የተከበራቹሁ ወገኖቼ እኔም በአማርኛ የምጽፈው አማርኛ በመጻፌ የትግራይ ሚስጢር እያወጣ ለጠላቶቻችን አሳልፎ ይሰጣል ከጅ እያቹ ግብረገብነት የገደለው ስድባችሁ ትሰነዝሩብኝ አላችሁ ፤ በወገኔ ስደብ መሳደብ ሰብአዊ መብት ጥሰት ሆኖ ጸረ ዲሞክራሲም ነው ስድቡ ቢቀርባቹና በሀሳብ ብትማጎቱ ይመረጣል ።

አሁን ልድገመላችሁ ተግርኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ነው እዳውም እኮራበትም ።በምርጥ ቃላት እጽፍ አለሁ ።እናገር አለሁ አነባለሁ ። ሌላም 17 አመት ከታገልኩላሏቸው አላማዎች አንዱ በሀቅቱ 5ሚሊዬን ለነበረ ህዝብ አሁን እንካኳን ቢቆጠር ከ8 ሚሊዬን ለሚሆን በቋንቋመው ሊማር ፣ሊሰራ ፣ሊናገር ወ ዘ ተ ነው ታድያ በትግርኛ ለምን አትጽፍም የትግሪያኖች ሚስጢር ለአማራ ለሌሎችም አሳልፈህ ትሰጣለህ? ነው ጥያቂያቹሁ ። እንግዳውስ ሀቁ ልንገኛቹሁ ፤
1ኛ መጀመሪያ ኢትዮጱያ መሀኔን እመኑ ሁለተኛ ትግራዋይ ነኝ።ለወደፊትም የማይቀዬር ፤
2ኛ ትግሪያኖች ከሞቶ ሚሊዬን በላይ ብዛት ያለው የኢትዮጱያ ህዝብ የሚደበቅ ሚስጢር የለንም ።ይህ ስሜት እየፈጠሩ የሚያራሩቁን ያሉ ፤የትግራይ ፣የአማራ ፣የኦሮሞ የሌሎችም ገዥዎች እና የነሱ ተላላኪ ጽንፎኞች ኢሊቶች ፣ ደካማ አስተሳሰብ ያላቸው ሴራ ነው ።
3ኛ እኔ እምጽፈው በአማርኛ ሆኖ የትግራይም የመላው ሀገራችን ህዝቦች በህዋሓት ኢህአደግ አባል ፓርቲዎችና አጋር ፓርቲያቸው በየግዛታቸው የሚያደርሱት ኢኮኖሚያዊ ፣ማሕበራዊ ፣ፓለቲካዊ ፣የሰብአዊ መብት ጥሰት መኖር የዜጎች ነጻነት ስለተነቁ ፣ፍትህና መልካም አሰተዳደር መንሳት ፣ግድያ ማሰር ፣መፈናቀል ፣መሰደድ ፣ጉቦ ፣አይኑ ያፈጠጠ የህዝብ ሀፍት ሰርቅ ፣ምዝበራ ስላለ ።ይህ ግፍ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ስላለ ።በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ የሚደረስ በደቡብ ህዝቦች ኦሮሞ አፋር አማራ ህዝብ ሌሎችም ወ ዘ ተ በሚረዱት አማርኛ ቢነገራቸው ምን ምን ችግር አለበት? በማራ ህዝብ በሌሎቹም ህዝቦች ያለው ሽግር ትግራዋይ ቢያውቀው ምን ይጎዳሉ ።ይልቁን ሁሉም በገዥዎች የሚሰቃዩ መሆናቸው የመረጃ ልውውጥ ካደረጉ አብረው ታግለው ለመፈነገል ።ያስችላቸዋል ። ስለዚህ እኔ በአማርኛ እምጽፈው ያለሁ ትግርኛ ቋንቋ ስለምጠላ ፣ስለማልችል ፣ሆን ብዪ የሌሎች አካላት ተላላኪ (ወይ እደ ድጅታሎች ቅጥረኛ ሆኜ የትግሪያኖች ሚስጢር ለማንም መስጠት ሳይሆን በትግራይ ያለው ችግር የመላወ የኢትዮጱያ ሽግር ነው የሌሎች ቸግርም ቸግራችን ።ስለሆነ ለወደፊት የሀገር ጉዳይ ሽግሮች ካሉ በአማርኛ ለማስተጋባት እሞከራሁ ።ይህ ስል ግን ትግርኛ አልጽፍም ማለት አይደለም ሀሳቤ ሊያሳራጭልኝ ግን እየመረጥኩ እጽፋለሁ ።ምነው የተወሰኑ
አስገደ ገብረሰላሴ
መቐለ፤
17 / 06 / 20 12

1 COMMENT

  1. አቶ አሰግድ ይገባኛል ህወአት የቀበረዉ መርዝ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ያሰቡ እንደርሶ ያሉ ወገኖችንን ምን ያህል እንዳሸማቀቀ ይገባኛል እርሶ በህወአት አገዛዝ አማራ ሁነዉ ቢያዩት ነገሩን ይበልጥ ይገነዘቡት ነበር። የትግሬ ባለስልጣኖች ኢትዮጵያ ላይ ሂትለር ካደረገዉ ይብስ እንደሆን እንጂ አያንስም ይህን በተመለከተ ወደፊት በስፋት ይጻፋል አሁን ያልተጻፈዉ አብይ አህመድ ለትግሬዎች ስስ ልብ ስላለዉ ነዉ። እንደሚያዉቁት አንድመ ትግሬ በፍተሀብሄር እና በወንጀል ሳይከሰስ የዘረፈዉን ገንዘብ ስምና ባንክ እየለዋወጠ አሁንም መስፍናዊ ኑሮ ይኖራል።
    አንድን ቤተሰብ ትዉልዱ እንዳይቀጥል በኡራል ገጭቶ የሚገደል የተረፈዉን ወጣት ልጅ የሚያንኮላሺ ክፉ ድርጅት ከትገሬ ተንስቶብን ያደረሰዉን በአይኖ አይተዋል ያ እግሩ ሲነቅጠቀጥ የነበረ ልጅ ከርሶ ልጂ በእድሜ ያንሳል በዛ እድሜዉ ትግሬን የሚያስቀይም ምን ነገር አድርጎ ነዉ አማራ ከመሆኑ በስተቀር? አማራነት ወይም ትግሬነት ጉራጌነት ኦሮሞነት… ተፈልጎ የሚሰጥ ሳይሆን እግዚአብሄር እንዲሆን የወሰነዉ ክስተት ነዉ። አረጋዊ በርሄ፤መለስ ሰራዊ፤አባይ ጸሀዬ፤ ስብሀት ነጋ አረ ምኑ ተቆጥሮ ያልቃል የትግሬ ግፈኞች።፡ሰዉን ማኮላሸት በግብረ ሰዶም ሰዉን ማበላሸት ሴትን ልጅ ማራከስ መስደብ መቀማት ምኑ ተቆጥሮ ያልቃል። የዚህ ሁሉ ዉጤት ንዉ እንደእርሶ ኢትዮጵያዊ መሆን የፈለጉትን ወገኖቺን ማመን ይከብደዋል እርሶን ማዋረዳቸዉ ስህተት ቢሆንም ምክንያቱን መገንዘብ አስፈላጊ ነዉ እላለሁ።
    ቋንቋዉን አስመልክቶ የተናገሩት ቋንቋዉ የትግሬም የአማራም የኦሮሞም ሳይሆን የተናጋሪዉ ነዉ እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ስቦ አሁንም የትግሬ ነዉ ወደሚለዉ ወሰዶት።፡ቋንቋዉ ኢትዮጵያዊ ሁኗል እርሶም ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ቋንቋዉ የርሶ ነዉ።ለማንኛዉም ከዚህ አስተሳስብ የጸዳን ሰዎች ባለፈዉ በችግሮ ጊዜ ሌላዉን እዚህ ሳንጠቅስ ማዘናችንን እንዲያዉቁትም ይገባል።
    ሰላም ሁኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.