ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ – ነዓምን ዘለቀ

ነዓምን ዘለቀ

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከህወሓት ወያኔ የእዝ ሰፈር እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ የህዝብ ሉአላዊነት የተከበረበት እውነተኛ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ከማስፈን ይልቅ ፥ በፌደራሊዝም ሽፋን ኢትዮጵያን ለመግዛት ባደፈጡ ባለተራ የአክራሪ የብሄር ልሂቃን መንደር መደናገጥ ፈጥሯል።

1) ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውን ፅንፍ የረገጠ የአክራሪ የጎሳ ብሄርተኞች ትርክት በኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን አደጋ ለሀገሪቱ ህልውና መርዘኛ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ወደማትወጣው አዘቅት እየከታት ነው ማለታቸው መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያጤነ ምልከታ ነው። እነዚ ፅንፈኛ ሀይሎች ከኢትዮጵያ አልፎ ተርፎ ለኤርትራ እና ለምስራቅ አፍሪካ ከባድ ስጋት እና አደጋ መደቀናቸው የማይስተባበል ነው።

2) በኢትዮጵያ ውስጥ በጭራሽ ስላልነበሰ በህብረ-ብሄራዊ ፌደራሊዝም መናገር ትልቅ ፌዝ ነው። ፌደራሊዝም እያሉ ሲጠሩት የነበረው ማደናገሪያ ፥ በተግባር በህወሓት ወያኔ የእዝ ሰንሰለት ስር የሚዘወር የብሄር ጭምብል ያጠለቁ በየክልሉ ያደፈጡ የህዝብ ውክልና የሌላቸው ልሂቃን በስሙ ቁማር እና ጨረታ የሚጣጣሉበት አገዛዝ ነበር።

3) ዲሞክራሲ በሌለበት እውነተኛ ፌደራሊዝም የሚታሰብ አይደለም። ብሄር እንወክላለን የሚሉ የብሄር ፌደራሊስቶች በህዝብ ሳይወከሉ ህዝብን አስገድዶ ለመግዛት ሽፋን ተስጥቷቸው ቆይቷል።

4) ፌደራሊዝም የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ አይደለም። ፌደራሊዝም በየክልሉ ያሉ በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን መብት መጣስ እና መርገጥ አይደለም። ፌደራሊዝም በኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎች ያሉ ኢትዮጵያውያንን ማቆሚያ በሌለው የጥላቻ እና የቂም በቀል ትርክት እና ዛቻ በስጋት እና በጭንቀት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ አይደለም።

5) ፌደራሊዝም ለጋራ ህግ ለገዢ መሆን እና የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ማድረግ ማለት ነው። ህዝብ የራሱን ጉዳዮች ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ የሚሰጥበት ፤ የሌሎች አብረውት የሚኖሩ በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች መብት የሚከበርበት ፤ በየትኛውም የሀገሪቱ የሚኖሩ ዜጎች ደህንነታቸው የሚጠበቅበት እና መብታቸው በህግ የሚከበርበት ስርአት ነው። ኢትዮጵያም ሊኖራት የሚነባው ፌደራላዊ ስርአት ይኸው ነው። ሆኖም በአምባገነኑ ህወሀት-ኢህአዴግ አገዛዝ ይሄ ከነጭራሹ አልነበረም።

6) በመሆኑም ዳግም ወደ መንበረ ስልጣን ለመምጣት በቅዥት ውስጥ ያለው ህወሀት እንዲሁም በብሄር ፌደራሊዝም ጭምብል ኢትዮጵያን ተቀራምተው ለመግዛት ባሰፈሰፉ ሀይሎች ዙሪያ እንዲሁም የፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት አስመልክቶ የያዙት አቋም ምክንያታዊ እና አሁን ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ እና በቀጣይ በቀጠናው ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ ያገናዘበ ነው።

Neamin Zeleke

3 COMMENTS

  1. እኔ የማይገባኝ የኤርትራው መሪ ስለ ኢትዮጵያ አያገባቸውም የሚሉ ፓለቲከኞች ናቸው፡፡ የጎረቤት ቤት በእሳት ሲጋይ ሌላው ቢቀር ጭሱ እንኳን በሌላው ጎረቤት ላይ ጉዳት አያደርስም ብሎ መገመት የጅሎች ፓለቲካ ነው፡፡ የኢትዮጵያ በዘር ፓለቲካና በክልል ክፍፍል መታመስ የአፍሪቃን ቀንድ ያለቅጥ ያናጋዋል፡፡ ስለሆነም አቶ ኢሳይያስ ለመቶ ኣመት የሰጡንን የቤት ስራ አንስተው አሁን ለኢትዮጵያ መቆርቆራቸው የፓለቲካ ስሌት እንጂ ከልብ የመነጨ ሃሳብ አይደለም፡፡ ወያኔ መቀሌ ላይ ሆኖ የፕረዝዳንቱን እጅ እንቆርጣለን ሲሉ እንዴ ቡና ሰርቀው ይሆን ወያኔ በፕረዝደንቱ ላይ እንዲህ ያለ ዛቻ የሚነፋው? መቸም ፓለቲከኞች ቀናቸውን አያውቁትም፡፡ ለ 30 ኣመት ግብጽን በጉልበት የገዛው ሆስኒ ሞባረክን ሞት አስመልክቶ ዜናው የግርጌ ማስታወሻ ሆኖ ማለፉ ያስገርማል። አሁን አጋዥ ሃገራት ናቸው የሚባሉት ቻይናም ሆነ አሜሪካ ለጥቁር ህዝብ የማይገዳቸው የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች ናቸው። በኬኒያ ናይሮቢ የቻይና ባለሃብቶች የሃገሬውን ተወላጅ ሲደበድቡ መረጃ የቀረበለት የኬኒያ ፍርድ ቤት በነጻ ለቋቸዋል። የአፍሪቃ ፍትህ እንዲህ ነው። በትግራይ፤ በአማራና በሌሎችም ክልሎች የቻይና ሰዎች ወንጀል ሲሰሩ አስሮ ወደ ሃገራቸው እንደመመለስ አለባብሶ ማለፉ የተለመደ ሆኗል። ከዚህ የበለጠ ባርነት የለም። በሃገሩ ላይ ተወላጆ በቻይናዎች መደብደብ። አሁን ደግሞ በሃገራችን ክሳቸው ተቋርጦ የተለቀቁ ሰዎችን ስም ዝርዝር ስመለከት እግዚኦ ያሰብላል። በወያኔ የጨለማ ዘመን ስንት ሰዎችን ያረዱና የሃገር ሃብት የዘረፉ ሰዎች ስም ዝርዝር ስመለከት እውነትም ሃገሪቱ በጭፍን እንደምትራመድ ያሳያል። በባህርዳር አቶ በረከት የጤና መቃወስ ደርሶባቸው ከሞት አፋፍ ላይ ናቸው ስንባል ለምን ተፈትተው ፍርዳቸውን በውጭ ህክምና እየተከታተሉ አይከታተሉም ያስብላል። አሁን ማን ይሙት አቶ በረከት መቀሌ ላይ በሲቪልና በወታደራዊ መኮንንነት የከተሙት የወያኔ ደም አፍሳሾች ከፈጸሙት በደል የተለየ አቶ በረከት የፈጸመው ወንጀል አለ? ወንጀል አልሰራም አይደለም የምለው። ግን የኢህአደግ የቁልቁለት ጉዞ ጸሃፊ እንደሚነግረን አቶ በረከት ላቅ ያለ እይታ እንደነበራቸው ያሳያል። ይብቃኝ ለአቶ በረከት ጥብቅና መቆሙ። ግን ክሳቸው ተቋርጦ የሚባለው ጉዳይ ያዘው ልቀቀው አይነት የማደናገሪያ ብልሃት ይመስላል።
    ወያኔ ተደራጅቶና ሌሎችንም የሃሳቡ ተካፋይ የሆኑ ድርጅቶችን አቅፎ እንደገና ለምርጫ ቀርቦ ካሸነፈ መንግሥት የማይሆንበትም መንገድ የለም። ዝም ብሎ እንገነጠላለን ገለ መሌ ከማለት የበፊቱን እማኝ ሳያረጉ አሁን ተሻሽለና ለሃገር የሚጠቅም ሃሳብ በመያዝ ሰልፋቸው ያማረውን በብዙ የሚቆጠሩ እኔን ምረጡኝ የሚሉትን የፓለቲካ ፓርቲዎች በሃሳብ ተፋልመው ከተመረጡ መንግስት የማይሆኑበት ነገር አይታየኝም። ይሁን እንጂ በሃሳብ ከመሟገት ይልቅ ዛሬም ባሩድ የሚሸታቸው ከሆነ ከተማውን ትተው ከጫካ ቢጀምሩ ይሻላል። ለነገሩ ጫካው ሁሉ ተመንጥሯል የት ይሄዳሉ እና! ኤርትራንም እንደጠላት ከመቁጠር ይልቅ ለሰላም መስራቱና ህዝባችን እፎይ እንዲል ከአቶ ኢሳያስ ጋር እርቅ ማውረድ ማለፊያ ይሆናል። ሌላው ሁሉ የልጆች እቃ እቃ ጫወታ ነው። አለም በብዙ ጉዳዮች እየተናወጠች ነው። ቱርክ በሱዳን፤ በሱማሊያ፤ በሶሪያ ወዘተ ምን እያረገች ነው? የአለም ኢኮኖሚስ መተራመስ በሃገር ላይ የሚያስከትለው ጉዳይ መገመት ይቸግራል። ከፓኪስታን እስከ ሱማሊያ የአንበጣ መንጋ እህልና አጽዋትን ሲሟጥጥ የእኛ በዘርና በቋንቋ ፓለቲካ መተራመስ ተንጋሎ መትፋት ነው። በእኔ እምነት የኤርትራዊያን ችግር የምስራቅ አፍሪቃ ችግር ነው። የኢትዮጵያም መናጋት ኤርትራንም ይጎዳል። ይህ የማይታየው በጫትና በአልኮል አልፎ ተርፎ በዘር ፓለቲካ ጢቢራቸው የዞሩ ብቻ ናቸው።

  2. ነአምን አሁንመ አለህ በ ቪዢን ኢትዮጵያ ስም ሻቢያን አትንኩ ብለህ መከራችንን ስታበላነ ነበር አሁንም እዛዉ ነህ ማለት ነዉ። አርበኞች፤ጂ7፤ኢዜማ እያላችሁ ስትገለባበጡ ከረማችሁ በነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴያችሁ የሻቢያ ወዳጆች መሆናችሁን ከጽሁፋችሁ ከንግግራችሁ እናዉቃለን አሁንም አርካይቭ ዉስጥ ይገኛል።
    3/4 የኤርትራን ህዝብ ያባረረ መቅሰፍት ታላቅነቱን ለመግለጽ የሄድክበት እርቀት ከምንም በላይ ኤርትራዉያን ዘመዶችህን ስለሚጎዳ አርፈህ ብተቀመጥ ይሻልሀል አባትህ የተከበሩ ወገን ናቸዉ የእናትህን መስመር ይዘህ አገር አታዋርድ ከገባህ ይግባህ።

  3. በየሚዲያው ከሚርመሰመሱት ቃተኛ ፖለቲሻንና አክቲቪስት ተብዬዎች ያንተ አይነቱን አስታዋይ ወገን ምናለ ቢያበዛልን? እውነት ብለሀል ተስፋ። እንዴት አይመለከታቸው ኢሳያስን? እነዚህን የወያኔ መሀይማን ምናለ ፈጣሪ በቁም በጨረሳቸው? ከዚህ ቀደም ብዬ ነበር፣ ምናለ የአልትራ ከንሰርቨቲቭ ፓርቲ አቋቁመው ተራ ቢገቡና ምረጡኝ ባሉ። ህውሀትነት ትንሽ ለጆሮም ቢሆን ይቀፋል ብዬ ነው። እውቀት ይጠይቃላ ክፋቱ። ከዬት ይምጣ እንጅ ። ማ ይሙት አገሪቱን በነፍስና በስጋ ሲያተራምሱ ሰው አያውቅብንም ብለው ያስቡ ይሆን እንዴ እላለሁ። መጨረሻችን ምን ይሆን? አሳዛኝ ዘመን ነው በውነቱ። እንኳን ኩታገጠም ያሉት ኤርትራውያን ወገኖች ቀርቶ መላው ምስራቅ አፍሪካ ባገራችን አስከፊ ሁኔታ ግድ ካልሰጣቸው ወላፈኑ በዬት እንደሚያገኛቸው የማያውቁ ነፈዞች መሆን አለባቸው። ይህው ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.