ከሰኔ 15ቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በትናንትናው እለት ፍርድቤት ቀርቦ ተለዋጭ የግዜ ቀጠሮ ተሰቶታል

አማራ ሚዲያ ማዕከል/ አሚማ
የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ሰኔ 15 2011 ዓ.ም በጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ተጠርጥሮ በእስር ቤት የሚገኘው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ እኔ አልገደልኳቸውም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰቷል።

አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ለፍርድ ቤቱ ቃሉን ሲሰጥ “እኔ ሰኔ 15 በቤቴ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት ያልታወቁ አካላት ድንገት ቤት ገብተው በጥይት መተውኝ ሞቷል ብለው ሲሄዱ ሌሎች ፖሊሶች ናቸው መጥተው ያሳከሙኝ ብሏል።”

እንዲሁም በውሸት ግድያውን ፈጽሚያለው እንድል ጫና እየተደረገብኝ ነው እኔ የማውቀው ነገር የለም ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የግለሰቡ ጠበቆች በበኩላቸው በተጠርጣሪው ላይ አቃቤ ህግ የጠቀሳቸው ምስክሮች በአካል ባለመቅረባቸው መሳፍንት ጥጋቡ በነጻ ሊወጣ ይገባል ብለው ተከራክረዋል።

ፍርድ ቤቱም ግራና ቀኙን አይቶ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 26 ቀጠሮ ሰጥቷል።

አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ሰኔ 15 መጀመሪያ ራሱን አጠፋ እንደገና በፖሊስ ተመቶ ተገደለ በመጨረሻም ግለሰቡ በህይወት መኖሩን በመግለፅ በመንግስት ሚድያ የተምታታ መረጃ ሲሰጥበተ እንደነበር ይታወቃል።

2 COMMENTS

  1. This is a very simple case to verify and close. This soldier blatantly lying. He is claiming that he was at home – Really ? Why unknown people attacked a chief of staff guard on that date at his home ..Ha..Ha..Ha.. the kid should be given clemency so that he can spit out the truth nothing but the truth.

  2. Abiy Ahmed forcefully stole the house Asaminew Tsige resided in that was located at the Bisrate Gebriel Orthodox Church ( International Community School ICS ) area or commonly known as the Russia military Camp neighborhood area in Addis Ababa SHEWA Ethiopia when both individuals were serving in the TPLF military.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.