የሃበሻ ወንድ አታግቡ? – ፋሲል የኔአለም

አንዲት የኦሮሞ ወጣት ዶ/ር መረራና አቶ በቀለ ገርባ በተገኙበት መድረክ ላይ የኦሮሞ ሴቶች ሃበሻ እንዳያገቡ፣ ያገቡም እንዲፈቱ መናገሯን ከሁነኛ አስተርጓሚ ሰማሁ። አልፈርድባትም፤ ያልተማረ ወይም እንደ ሚሻሚሾ እንጨት ተለብልቦ የወጣ ሰው ከዚህ የበለጠ ሊያስብ ወይም ሊናገር አይችልም።

እኔን የገረሙኝ ይህን ያስተላለፈው ሚዲያና በንግግሯ እንደማዘን ሲስቁ የነበሩት “ፖለቲከኞች” ናቸው። ኢትዮጵያ የማይፈጸሙ ህጎች ያለባት አገር በመሆኗ የኢትዮጵያን ህግ ጥቅሼ በመወንጀል ጊዜየን ማጥፋት አልፈልግም። እንዲህ አይነት የጥላቻ ንግግሮች ዛሬ በኢትዮጵያ ህግ ባያስቀጡ ነገ ከነገ ወዲያ በአለማቀፍ ህግ የሚያስቀጡ መሆኑን ግን መናገር እፈልጋለሁ።

ዛሬ ማንም ምንም አይመጣም ብለው ጥላቻን የፖለቲካቸው ማዕከል ያደረጉት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ባለቤቶችና እንዲህ አይነት ሰዎችን የሚያበረታቱት የኦፌኮ መሪዎች ነገ በአለም አደባባይ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀርም። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ የጥላቻ ንግግርን መግታት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ማፈን ሳይሆን ዜጎችን በዚህ ንግግር የተነሳ ከሚመጣ ጥቃት መከላከል መሆኑን ይገልጻሉ፦ “Addressing hate speech does not mean limiting or prohibiting freedom of speech. It means keeping hate speech from escalating into something more dangerous, particularly incitement to discrimination, hostility and violence, which is prohibited under international law.”

የኢትዮጵያ መንግስት በአደባባይ የሚታዩ ግጭቶችን ብቻ ሳይሆን ነገ ግጭቶችንና አጠቃላይ ማህበረሰባዊ መናጋትን የሚፈጥሩ ንግግሮችን በፍጥነት ማስቆም አለበት። እንዲህ አይነት የጥላቻ ንግግሮችን በሚያሰራጩ ሚዲያዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ፈጥኖ እርምጃ ካልወሰደ፣ ነገ “ወጪት ጥዶ” ማልቀሱ አይቀርም።

ማንኛውም ሚዲያ፣ እኔ የምሰራበትን ኢሳት ጨምሮ በእንዲህ አይነቱ ኢ ሰውኛና ኢ ተፈጥሮኛ በሆነ ሁዋላ ቀር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ከሆነ ያለ ርህራሄ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል። ዛሬ “ኦሮሞ ያልሆኑ ባሎቻችሁን ፍቱ” ያለች ሴት፣ ነገ አንፋታም የሚሉትን በሜንጫ አንገታቸውን በሏቸው ማለቷ አይቀርም።

እንዲህ ስትል ደግሞ ፖለቲከኞች ያጨበጭባሉ። ሚዲያውም ደስ ብሎት ያስተላልፈዋል። ትችት ሲመጣባቸው “የኦሮሞ ጥላቻ ያለባቸው ናቸው ንግግሩን የሚያጣምሙት” እያሉ፣ ጣላቻቸውን የብሄር ፖለቲካ ቀለም ይሰጡትና የተችዎቻቸውን አፍ ለማዘጋት ይሞክራሉ። በእንዲህ አይነቱ ስትራቴጂ ሰዎችን አንዴ ልታታልል ትችል ይሆናል፤ እድሜ ልክህን ማታለል የምትችል ከመሰልህ ግን በጨዋ ቋንቋ ጅል ነህ።

ኦፌኮና ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ በፍጥነት ይቅርታ ጠይቀው ራሳቸውን ከንግግሩ ማራቅ ካልቻሉና እንዲህ አይነት ነገር ቢደገም የመጨረሻ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ካልፈረሙ፤ በወጣቷ ንግግር እንደተስማሙበት ተቆጥሮ መንግስት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እጠይቃለሁ።

Fasil Yenealem

7 COMMENTS

 1. ይህች ወጣት አይፈረድባትም:: ለማስደሰትና ተቀባይነትን ለማግኘት የፈለገችው ከጥላቻ መምህሩ ከበቀለ ገርባ ነው:: ከዚህን በፊት ኦሮምኛ ከማይናገሩ ጋር አትገበያዩ ያለውን ጥሪ ተከትላ ነው::የጥላቻ ፖለቲካ ዬትም አያሻግርም:: መረራ ጉዲናም አሁኑኑ ተሸናፊነቱን ስለተቀበለ ከእነዚህ ዘረኞች ካምፕ ተደምሯል::

 2. ወንድሜ ሁላችንም ተሸማቀን አድምጠነዋል። ፈጣሪ ለሆነ አስቀምጦን በኢትዮጵያ ምድር ይህ ሲሆን አየን፣ ሰማንም። ምን ታርግ ልጅቱ? ለ ሀያ ስምንት አመት ያጠናችውን እኮ ነው መምህራኗ ፊት የተነፈሰችው። ሌሎች በሷ እድሜ ክልል ያሉትም ሁሉ አጨበጨቡላት። አስተማሪዎቹም በማድነቅ አንገት ነቀነቁላት። ይህው ነው። በቀለስ አስቀድሞ አደባባይ ቀድሟታል።፣ የአቶ መረራ ጭብጨባና ፈገግታ እስከመቼም አይረሳም። አሁን ይህ ፖለቲካ መሆኑ ነው? ይቅርታ ብቻ ሳይሆን በዚህ ጥላቻ ባናፈሰው ጣብያ ቀርበው እራስ ማራቅ ብቻ ሳይሆን ወንጀልነቱን መማማርያ አርገው ካላቀረቡ፣ ነገ ለሚመጣው የከፋ ሁኔታ ተጠያቂ ናቸው። ይህ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መወገዝ ያለበት ነው። ከሰላሳ አመት ወዲህ ለተፈጠሩ ህጻናት ከልብ አዝናለሁ። ፈጣሪ ይታረቀንም ዘንድ ከልብ እጸልያለሁ በበኩሌ። ለዶር አቢይም ከልብ አዝናለሁ። ይህን ወገን ተይዞ እንደምን ብልጽግናስ ይታሰባል? አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ዘመን።ይቺ የመጨረሻዋ የነሸኔና ኦፍኮ ካርድ መሆኗ ነው። ብልጽግናዎችና ሌሎች አገር ወዳድ በሙሉ በህብረት አውግዙ። ይህ አደገኛ ቀይ መስመር ነው በኔ አተያይ።

 3. እኮ በለ ፋሲል የዚህች ሴት ሃበሻ አታግቡ ማለቷ ከበቀለ ገርባ ቋንቋህን ካልተናገረ እቃ አትሽጥለት ከሚለው ሃሳብ ጋር በምን ይለያል። ጨምሮስ ዶ/ር መራራ የሚኒልክን ቤተመንግሥት አፍርሰን የራሳችንን እንተክላለን አላለምን? አንድ በአሜሪካ በምትገኝ ትንሽ ከተማ የስደተኞችን ጉዳይ የሚያጠና ሰው ይህን አካፈለኝ። ከዲትሪይት ብዙም ባራቀች አንዲት ከተማ ውስጥ ከ 30 ሃገሮች የመጡ ኗሪዎች ይኖራሉ አለና በትምህርት በቱም ውስጥ በ 21 የተለያዪ ቋንቋዎች ይማራሉ። በማለት ካወራኝ በህዋላ ጀርመኖች፤ ኖርዌጃኖችና ሌሎች እየፈለሰሱ ወደ አሜሪካ ሲመጡ ጅማሬው በሃገራቸው ቋንቋ ነበር። ያ የሚቀጥለው ትውልድ ግን እንግሊዝኛን ተምሮ ኗሪ ሆኗል። የእናንተ ሃገር ፓለቲካ አይገባኝም። በተለይ የዘር ፓለቲካቹሁ በማለት ትንሽ ወረፍ አርጎ አለፈኝ። እውነት ነው። በሻቢያና በወያኔ የፓለቲካ ስልት ጭንቅላቱ የታጠበ ሰው ምንም ቢባልና ቢደረግ ወደ እውነት መቅረብ አይችልም። ለእነርሱ አለም ሁሉ የሚሽከረከረው በመገንጠልና በዘር ሰልፍ ብቻ ነው። የኦሮሞ ፓለቲከኞችም ከሰከሩ ቆየ። የሚያሳዝነው ሻል ያለ እይታ አላቸው የተባሉትም በእሳት መጫወታቸው መማር መደንቆር መሆኑ ያሳያል። የኦሮሞን ሴቶች ሃበሻ ካላገባቸው ነጭ እማ እድሜ ላባቶቻችን አባረዋቸዋል። ባል ከየት ሊመጣ ነው? አታድርስ። አይ የሌብነት ፓለቲካ። ትላንት በመጤ ፍልስፍና የእልፍ ሰው ህይወት ያጠፋው ያው ወልጋዳ ፓለቲካ መልኩን ቀይሮ በዘርና በጎሳ ያናኩረናል። ፍትህ ለተነፈገ ህዝብ፤ ሰላም ላጣ ህዝብ፤ የሚበላው ለጎደለበት ህዝብ የኦሮሞ ፓለቲከኞች የሚለፉት ሸፋፋ ፓለቲካ ሁላችንንም ይዞ ይጠፋል።
  የኦሮሞ ህዝብ የሚፈልገው ምንድን ነው? ሀ. በቋንቋው መናገር ለ. በመረጠው እና ራሱ በወከለው ሰው መተዳደር ሐ. በከባቢ ሃብቶቹ ተጠቃሚ መሆን ነው። ከዚህ ውጭ ሌላው ሁሉ የፓለቲካ አተካራ ነው። ይሁን እንጂ በግድ ቋንቋዬን ካልተናገርክ በማለት ሌላውን ማሳደድ የእብድ ፓለቲካ ነው። የሌላውን ቋንቋ ጥቁር እየቀቡ የእኔን ውደድልኝ ማለትም አይችልም። የቋንቋውን ፊደል በላቲን የለወጠው ይህ የሙታን የፓለቲከኞች ስብስብ ሆን ብሎ ሃገርን ለማመስ የሚሰራ ለመሆኑ ተግባራቸው ያሳያል። ኦፌኮና የኦሮሞ ሚዲያ ይቅርታን አያውቁም። ዝም ብሎ መልፈፍ ነው። እስቲ ይታያችሁ ሰው 50 ዓመት ሙሉ በአንድ እይታና የፓለቲካ መስመር ሲራመድ አያሳዝንም። ቆም ብሎ የቱ ጋ ብናሻሽል ሰው ይሰማናል፤ ህዝባችንስ ትርፍ ያገኝበታል አይባልም? የአፍሪቃ ፓለቲካ በነጮችና በአረቦች የተጠለፈ በሃገር ውስጥ ጠባብ ብሄርተኞችና ቅጥረኛ ቡድኖች የሚተገበር ነው። ዛሬ ራሱ የሱዳኑን መሪ ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ሳነብ ይህ ምድር ከመከራ ሌላ ሰላምን ሊያገኝ እንዳልቻለ ያሳያል። መግደል መገዳደል፤ መከፈል መከፋፈል የትርምስ ፓለቲካ። በሌላው አለም ከብዙ ዘርና ወገን ጋር ኖሮ ተምሮ ሃገር ቤት ሲመለስ የሚሰብከው መከፋፈልንና መገንጠልን ብቻ። የአፍሪቃ በሽታ አያሌ ነው። ከዚህም የባሰብን የዘርና የቋንቋው እንዲሁም የወያኔ አፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ነው። እንዲህም በመሆኑ ነው ወይዘሮዋ/ወይዘሪቷ ሃበሻን አታግቡ ያለቸው። አንድ ነገር ልጨምር በኖርዌ ጎዳናዎች እየተጫወትን ስናልፍ አንድ እኛኑ የሚመስል ሰው አገኘንና ጎኔ ያለችው ሴት ሃበሻ ነህ አለችው። አይደለሁም አለ። ታዲያ ምንድን ነህ ስትለው ኤርትራዊ አላት። እሷም በረሃ ቀመስ ነበረችና አይ ሻቢያ ራሱ እኛ ሃበሾች ናችሁ ብሎ ያስተምረን ነበር አንተ ምን ለማለት ፈልገን ነው ስትለው አይ እኔ ኤርትራዊ እንጂ ሃበሻ አይደለሁም አለና ትቷን ሄደ። እሷም በትግርኛ ቋንቋ ” አስመራ ላይ ሆነህ እንዲህ ብትኩራራ ደስ ባለኝ። በሰው ሃገር ተጠልሎ መቀባረሩ ጥቅም የለውም” አለቸው። ለዚህ ነው ዋሽንግተን ላይ ተቀምጠው “ኤርትራን ለኤርትራዊያን” የሚሉን። የበድኖች ፓለቲካ!

 4. የነ በቀለ ገርባ ምልምሎች፣ ቪጂላንቴዎች /vigilante / ህግ ፣ ማህበራዊ ስርኣት / Public Order / ባለበት በኣደባባይ ወጥተው በድንቁርና የተለወሰ የጥላቻ መርዛቸውን ያለ ማንም ከልካይ ሲያስተጋቡ እየተስተዋለ ነው። ይልቁንም የጥላቻ ንግግርን የሚያግድ ህግ በጸደቀበት ማግስት OMN ያለ ምንም ፍራቻ ሲያሰራጭ ተስተውሎኣል።
  ይህ OMN ድርጊት ህጉ በተግባር ለመፈጸሙ መታያ/ litmus test / ሊሆን ይገባዋል። ኣለበለዚያ ነገም ፣ከነገወዲያ እነ በቀለ ፣ መራራ ህዝቡ ላይ በኣፋቸው ቢጸዳዱ ሊደንቀን ኣይገባም።
  ለመሆኑ የኦሮሞ ኤሊት ፖለቲካ ዝቅጠቱ ጥልቀት ምን ያህል ነው ?
  እንወክለዋለን የሚሉት ህዝብ ላይ ያላቸው ንቀትስ ልኩ ምን ያህል ነው ?
  Are they worthy of democracy or autocracy or psychological therapy?
  ትናንት ተናቅን፣ ተገለልን …..etc ስትሉ ይሰማል፣ ዛሬ የምት ሰሩት የሚያስከብራችሁ ይመስላች ሁዋል ??
  BOTTOM LINE : ሰፊው የዋሁ ህዝብ የማያውቀው ነገር፣ እንደ ሽንኩርት ስትላጡ ላስተዋለ ውስጣችሁ ማን እንዳለ ከምንጊዜውም በላይ ግልጽ እየሆነ መጥቶኣል ።በኣዲሲቱ የኢትዮጵያ ግንባታችን ውስጥ ጥቁር ነጥብ ኣስመዝግቦ ለማለፍ እየፈጠናችሁ ነው ። History will judge you .
  የጊዜ ጉዳይ ነው የእጃችሁን ታገኛላች ሁ።
  LONG LIVE ETHIOPIA !!

 5. A Mother of two from Ethiopia got shot and killed in San Francisco California USA by two males two months ago , even though the killers admitted to the killing of the 32 years old mother of two from former state of Ethiopia Eritrea while Eritrea was under Ethiopia, with no charges filed for killing her by the USA government authorities . The international communities should know that denying Ethiopians water and their chance of being self reliant with food got so many unforseen negative consequences not only to Ethiopia but to the whole world since Children who grow up malnourished witnessing starvation related disasters got less stamina throughout their lifetime .

  A former Ethiopian famine victim as a little child who witnessed the death loosing of her parents to the Ethiopian famine starvation in the state of Eritrea who is now an independent country , who later got adopted and moved to USA later ended up having two children of her own got shot and killed by two male individuals a couple of months ago in San Francisco , California USA , ingniteing one of the most controversial legal conflicts since the killers are not charged with murder but charged the admitting killers with only gun charges since these Ethiopian lady was a former famine victim in the former Ethiopian State of Eritrea who terrorized the two males that were charged with only gun charges even if they admitted to killing the 32 years Ethiopian who was born from Eritrean family , the two men claimed they feared for their life before they shot and killed Emma Hunt so no murder charge is being filed for this 32 years old Ethiopian mother of two despite the Ethiopian Eritrean Community continuous outcry to charge the killers with murder the prosecutor is inclined to not charge them with murder saying she acted threatening towards the two male individuals exhibiting her African sides of when she grew up fending for herself and her younger sister homeless in Ethiopia after her parents died of starvation famine .

  News Break › … › San Francisco
  Web results
  SF District Attorney declines to file murder charges in Tenderloin shooting of mother

  San Francisco Chronicle › article
  SF district attorney declines to file murder charges in Tenderloin shooting of …

 6. To Daniel Zeru stop saying that an outcry was made by Habeshas for this lady, because it didn’t happen, it remains to be seen if it ever will.

  Daniel Zeru

  According to the priest at the St. George Ethiopian Orthodox Church in San Francisco , CA. and the pictures at the events seen in the website links below not one Habesha showed up to voice their concerns at the Candle light vigil or the many other events held for Emma Hunt including her memorial , so please donot pretend the SF California Abesha Community fought for justice trying to pressure the District Attorney because the priest himself didn’t participate or no other Habesha participated in such activities. The San Francisco Habeshas got no unity , they are divided by ethnicity so much, the other races shit on habeshas regularly and get away with it, according to the SF priest and other individuals I spoken to.

  SFist › 2020/01/17 › no-murder-cha…
  No Murder Charges For Pair Implicated In January 5 Tenderloin Slaying – SFist

  The San Francisco Examiner › news
  Web results
  Police arrest two in fatal shooting of SF woman – The San Francisco Examiner

  San Francisco Chronicle
  Web results
  Family, friends mourn San Francisco woman slain in weekend shooting

 7. እኔ የማይገባኝ እነዚህ በከፍተኛ የአዕምሮ መታወክ የሚሰቃዩ ፖለቲከኞች ነን የሚሉ ሁሌም ታጥቦ ጭቃ የሆነ አስተሳሰባቸዉ ሰዉ ይሰማኛል ማለታቸዉ ነዉ ።ለነገሩ ሆድ ያባዉን… ሆኖባቸዉ እዉነተኛ ማንነታቸዉ ይህ ነዉ ።በዚህ በረከሰ አስተሳሰብ አለም አልተቀየረም ስለሆነም በአሁኑ ሰአት የታመሙ ፖለቲከኞች ለምርጫ ከመወዳደራቸዉ በፊት ስለአዕምሮ ደህንነታቸዉ ከሐኪም መረጃ ቢያቀርቡ የሚሻል ይመስለኛል ።ካልሆ ግን ነገ ከተመረጡ ሐገር ማበዱ የማይቀር ሐቅ ነዉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.