የኦማንና የኩዌት መሪዎች ከግብፅ ጎን ነን አሉ

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ የተላኩ መልዕክቶችን በመያዝ ወደተለያዩ ሃገራት እየሄዱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የሚኒስትሩ ጉዞና የፕሬዝዳንቱ መልዕክትም ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባቸው ባለችው ግድብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #ሳሚ_ሽኩሪ በኩዌት ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኢራቅ፣ ኦማን፣ ዮርዳኖስና ባህሬን በመሄድ ስለግድቡ የማግባባት ስራ እየሰሩ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አህመድ ሃፊዝም ይህንኑ
አረጋግጠዋል።ለጉብኝት በሄዱባቸው ሃገራት ሁሉ የድርድሩን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መልዕክቶችን እንደሚያደርሱም ነው የተናገሩት፡፡ትናንት እሁድ ግድቡን በተመለከተ ከአል ሲሲ የተላከ መልዕክትን ለኩዌቱ ኢሚር አድርሰዋል፡፡
.
የኦማንና የኩዌት መሪዎች ከግብጽ ጎን እንቆማለን ስለማለታቸውንም ከግብጽ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የወጣውን መረጃ ዋቢ አድርጎ [ አል አይን አረብኛ ዘግቧል]
.
Suleiman Abdella

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.