«በሱዳንና በግብፅ መሀከል ነቆራው ከሯል» ወንዴ ብርሃኑ

አልጀዚራ ሁለት እንግዶችን አቅርቧል።እኔም ገና ከሦስት ቀን በፊት ማስታወቂያውን አይቸው ለማዳመጥ ስጠባበቅ ነበር
ቀኑ ደረሰ። ዛሬ ልክ ከምሽቱ 3 ሰአት ላይ እንግዶቹ ቀረቡ
.
ከሱዳን የተጋበዘው ዶክተር ዲሊ አልከባሽ ይባላል።የሱዳን
መንግስት አማካሪና በካርቱም ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ
መምህር ነው።
.
ጋዜጠኛዋ የመጀመሪያ ቃለ.መጠየቅ ያደረገችው ለሱዳናዊ እንግዳ ነበር።ጋዘጠኛዋ ዶክተር ዲሊ የኢትዮጵያ መንግስት የአረብ ሊግ ያወጣውን መግለጫ ከምንም አልቆጠረውም
የአረብን ሊግ መግለጫ እንደሰማ ወዲያውኑ ነው ንቄት የተሞላበት መልስ የሰጠው «ይሄንን ከምን አንፃር ያዩታል»?

ዶክተር ዲሊ፦ኢትዮጵያ ምንግዜም በራሷ የምትተማን
ሃገር ናት።ለማንም ተንበርክካ የማንንም እግር አጥባ አታውቅም። እውነት ነው የአረብ ሊግ ያወጣው መግለጫ በጣም አሳፋሪና በኢትዮጵያ ላይ መድሎን የሰራ ለግብፅ ያዳላ ነው ይህ የአረብን ሊግ የሚያስንቅ ውሳኔ ነው።ምንም እንኳን ኢትዩጽያ የአረብ ሊግ አባል ሀገር ባትሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ግማሹ ሙስሊሞች ናቸው።ኢትዮጵያ ለእስልምና ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ የነ ቢላል ኢብኑ ረባህ የነ አሕመደ_ነጃሽ ሃገር ናት «የአረብ ሊግ ግን ይሄንን ረስቶታል» ኢትዮጵያ ለአረቦች ከጎረቤትም በላይ በጣም ቅርብ ሃገር ናት።

ጋዜጠኛዋ ጥያቄዋን ቀጠለች፦ዶክተር ዲሊ,,ሱዳን በአረብ ሊግ ውሳኔ”የራሷን አቋም መያዟን እንዴት ያዩታል ?
ርሰወም ቢሆኑ የገዥው መንግስት አማካሪ ናቸው እስኪ ይሄንን አብራሩልኝ?.

ዶክተር ዲሊ፦ሱዳን የወሰደችው አቋም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው።ምክኒያት ሱዳን የኢትዮጵያ ልማት ተጠቃሚ ሀገር ናት።ይሄንን ውሳኔ ባንወስን ኖሮ የሱዳን ህዝብ በመንግሥት ላይ ተቃውሞ ያደርግ ነበር
አለ።
.
ጋዜጠኛዋ ይሄንን ፍልቅልቅ ፊቷን ገምሸር አርጋ አዙራ ፊቷን
ወደ ግብፃዊ የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ሁሴን አብዱራዲ አዙራ ጥያቄዋን ቀጠለች፦
.
ጋዜጠኛዋ ዶክተር ሁሴን እርሰዎ የኢትዮጵያ መንግስት የያዘውን አቋም እንዴት ያዩታል ግብፅ እወስደዋለሁ ያለቸው እርምጃ ለግብፅ ይጠቅማል ወይ?
.
ዶክተር ሁሴን ግብፅ የአባይን ውሀ ከፈጣሪዋ ለይታ አታየውም።የአባይ ውሃ ለግብፅ ህዝብ የህልውና ጉዳይ ነው
የግብፅ መንግስት እያደረገ ያለው ግብፅ በአባይ ላይ ያላትን ታሪካዊ የመጠቀም መብትን መቶ በመቶ እውን ማድረግ ነው
ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜ ክህደት እየፈፀመች ነው።በቅርቡ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገዱ አንዳርጋቸው የተናገረው ንግግር በጣም አደገኛ ነው።መሬቱም ውሀውም
ግድቡም የኛ ነው ማለት የግብፅን የውሀ ባለቤትነት መካድ ነው።በኢትዩጽያ በኩል እንደዚህ ያሉ አቋሞችን እያየን
እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም።በዲፕሎማሲዊያ መንገድ የማይሳካ ከሆነ ሌላ አማራጭ ለመጠቀም እንገደዳለን
አለ።
.
ጋዜጠኛዋ ጥያቄዋን ቀጠለች ዶክተር ሀሰን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን እንዴት ያዩታል?
.
ዶክተር ሀሰን ግብፅ ሱዳንን የመጉዳት ፍላጎት የላትም።
ሱዳን ግን በአባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፋ የግብፅ ህዝብ በውሀ ጥም እንዲሞት እያመቻቸች ነው።በቅርቡ ዶክተር አብይ የሱዳን የተቃዋሚ ሀይሎችን አሸማግሎ መንግስት እንዲመሰርቱ ያደረጋቸው ለኢትዩጵያ ጥቅም አመች እንዲሆን እንጅ ለሱዳን ተጨንቆ አይደለም አለ።
.
በዚህ መሀከል የሱዳኑ እንግዳ ተነስቶ መናገር ጀመረ
ጋዜጠኛዋ ለማብረድ ሞከር ብታደርግ ነገሩ አልሆነም
ሱዳናዊ እንግዳ ልክ ልኩን ነገረው።ግብፅ አንድም ቀን ለሱዳን ጥሩ አስባ አታውቅም።ደቡብ ሱዳን ከሱዳን እንድትገነጠል ከአሜሪካ ጋር ወግና ስትሰራ የኖረችው ግብፅ እንጅ ኢትዮጵያ አይደለችም።በሱዳን ላይ 30 አመት ማዕቀብ ተጥሎ ሲቆይ ግብፅ አንድም ቀን ማዕቀቡ እንዲነሳ ጥያቄ አቅርባ አታቅም።ኢትዮጵያ ግን ያቅሟን አድርጋለች።በቅርቡ
ሱዳን ላይ የፖለቲካ አለመግባባት ሲፈጠር ግብፅ የሱዳንን ህዝብ እርስበርስ ለማጨፋጨፍ በሚዲያዋ ፕሮፓጋንዳ ስትረጭ ኢትዮጵያ ግን አሸማግላ ሀገራችንን ከመበታተን አድናልናለች ይሄንን መላው የሱዳን ህዝብ ያውቀዋል አለ።
.
Suleiman

2 COMMENTS

  1. ግብጽ የሱዳን የተዘዋዋሪም ሆነ የቀጥታ ቅኝ ገዢ አይነት ባህሪ ያላት ሃገር ናት። ግብጻውያን አፍሪቃ ውስጥ አንኖርም እኛ መካከለኛው ምሥራቅ ነን በማለት የቆሙበትን መሬት የሚክድ በእንግሊዞች ጭንቅላት የሚያስቡ ናቸው። ምን ማለት ነው? የቆዳቸውን ፈካ ማለት ተገን በማድረግ ጥቁሩን ዓለም የሚከዱ ወስላቶች ናቸው። አሁን በሱዳን በሃገሪቱ መሪ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረጉትም እነርሱ ናቸው በየ ነው የማምነው። የዓረብ ጉራ ማለቂያ የለውም። ልጥቀስ። በፔትሮ ዶላር የሰከረቸው ሳውዲ አረቢያ ወደ የመን ግጭት መሰል የዓረብ ሃገሮችን ይዛ ስትገባ ለጥቂት ጊዜ ነው ምንም ችግር አይኖርም ወዲያውኑ ወደ ሰላም ሃገሪቱን እንመልሳለን። መሪዋንም ወደ ሥልጣኑ ይመለሳል በማለት ነበር ዜናውን ያናፈሱት። ግን አሁን በምድር ላይ የምናየው እውነታ ከዚህ የራቀ ነው። ሳውዲ የዓረብ አለም ችግር ፈጣሪዎች ናቸው።
    በመሰረቱ የአረቡ ዓለም በራቢጣው ስብሰባ ላይ አንድ አቋም ያዘ መባሉም የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ነው። ውስጥ ውስጡን የሚሻኮት አንድ በሌላው ሃገር ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚገባ የማይተማመን ስብስብ ነው። የግብጽ ኢትዮጵያን ማስፈራራት የማይሆን ነገር ነው። የአባይ ውሃ ክፍፍል ሆን ተብሎ በእንግሊዞች የተሰመረ የያኔ የፓለቲካ አሻጥር ነው። የግብጽ መደንፋት የትም አያደርሳትም። ግን ህዝቡ የዳቦ ጥያቄውን ለአፍታም ቢሆን ረስቶ በዚህ የውሃ ፓለቲካ ቀልቡ እንዲሳብ ለማድረግ እየተሞከረ ነው። ግብጽ ብዙ ችግር ያለባት ሃገር ናት። ከሙባረክ መውረድ በህዋላ የምትተራመሰው ግብጽ የሰው መብት የተነፈገባት፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በእስር የታጉሩባት ከሰው ብዛት የተነሳ ምድሩ የጠበባት ሃገር ናት። የአረብ ሃገሮች ከግብጽ ጎን መሰለፍ ልከክልህና እከክልኝ አይነት የፓለቲካ ስሌት ነው።
    ያው በቃለ ምልልሱ ላይ የሱዳኑ ምሁር እንዳስቀመጡት ግብጽ ኢትዮጵያን ማስፈራራቷ የማይመች አካሄድ ነው። ጉራና ተግባር ይለያሉ። ይኽው ከሰሞኑ ዪጋንዳ ግድብ ለመስራት እያሰበች ነው ይባላል። ጥቁርና ነጭ አባይ ሲገደብ ምን ሊያረጉ ነው? ከንጉሱ ፍንቀላ በህዋላ ያለ ወታደራዊ መሪ የማታውቀው ግብጽ ለራሷ ሰላም የሌላት 0.1% ህዝብ ተንደላቆ ሲኖር ቀሪው የእለት ዳቦ የጎደለበት ሃገር ናት። ግብጽ ለኢትዮጵያ አንድም ቀን ተኝታ አታውቅም። ከንጉሱ ዘመን ጀመሮ እስከ ዛሬ ከመተናኮል ወደ ኋላ ብላ አታውቅም። በተለያየ ስም ኢትዮጵያን ለማመስ ለተነሱ ሁሉ የመጠለያና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የሃበሻው ምድር ሰላም እንዳያገኝ እየሰሩ ለመሆኑ በፊትም አሁንም ግልጽ ነው። ቆሻሻው የሃገራችን ፓለቲካ በዘርና ወንዝ በማያሻገር ቋንቋ ሲቆራቆስ እነርሱ ያን ተገን በማድረግ ሰውርና ግልጽ ደባ በቅጥረኞቻቸው ይፈጽማሉ ያስፈጽማሉ። ግብጽ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነችበት ጊዜ የለም። በጥቅሉ ግብጾች አፍሪቃዊነታቸውን የካድ ከአፍሪቃ ሰማይ ስር ሆነው ምድሪቱን የካድ ናቸው። የፈርኦን ጦር ቀይ ባህር ገብቶ የለ ይህም በኢትዮጵያ ተራራማና ኮረብታዎች ላይ ወድቆ ለመቀረት ካለሆነ በጦርነት የአባይን ግድብ ማስቆም አይቻልም።

  2. Historical facts are all well illustrated by the Sudanese rep. Egypt must abide, by the law of the land. The blue Nile is Ethiopian natural wealth. Over 86% of the river flows within Eth. The Nile carries over 250 million tons of fresh alluvial soil from the highlands of ETh. Eth should stop this completely. This can be done by constructing several small dams. For thousands of years Egypt has enjoyed development on th Cost of Eth. It’s time for Ethiopians to develop their country.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.