የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመትን አጽድቋል

በዚህም መሰረት አቶ አወሉ አብዲ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

እስካሁን በሥራ ላይ በቆየው በድርጅቱ የቦርድ ሥራ አመራር ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ወ/ሮ አበበች ሸከታ በአዲሱ የሥራ አመራር ቦርድም የሚቀጥሉ ሲሆን፤ በተቀሩት አባላት ምትክ አዳዲስ አባላት ተሹመዋል።

ለመሆኑ አዳዲሶቹ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እነማን ናቸው

1. አቶ አወሉ አብዲ አብዶ – ሰብሳቢ

የትምህርት ዝግጅት

ኤም ኤ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በሊደርሽፕ/ፕላኒንግ ማኔጅመንት
ኤም ኤ ከኢንድራ ጋንዲ ዩንቨርስቲ በኢኮኒሚክስ፣ የማጠቃለያ ወረቀት የሚቀራቸው
ቢ ኤስ ሲ ከሃሮማያ ዩንቨርስቲ በሂሳብ ትምህርት
አድቫንስድ ዲፕሎማ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቱ በፕሪንሲፓል ሺፕ
ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲቲዩት በሚኒተሪንግ እና ኢቫሉዌሽን

የስራ ልምድ

የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አባል ሆነው እያገለገሉ ያሉ
በሚኒስትር ማእረግ በዴሞክራሲ ስርዓት ማእከል የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የፕሬዘዳንቱ ከፍተኛ አማካሪ
የብረታብረትና ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን ም/ዋና ዳይሬክተር
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የካቢኔ አባልና የክልሉ ስራ አድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ
በተለያዩ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ላይ በቦርድ ሰብሳቢነትና በአባልነት ያገለገሉና የሚሰሩ

2. ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ መሃመድ – አባል

የትምህርት ዝግጅት

በረ/ፕሮፌሰር ማእረግ፣ በግሎባል ፐብሊክ ሄልዝ ስፔሻሊስት ናቸው፡፡ በኢፕዲሞሎጅ ስፔሻላይዝ አድርገዋል፡
የስራ ልምድ
በስዊድን ሃገር ሉንድ ዩንቨርስቲ የግሎባል ሄልዝ ኮሌጅ ዲን ሆነው ሰርተዋል፡፡ ባጠቃላይ በሉንድ የንቨርስቲ ከ30 ዓመት በላይ አገልግለዋል
ደቡብ ሱዳን እንደ ሃገር ስትመሰረት በአለም ባንክ ውስጥ የጠየና አማካሪ ሆነው ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል
የአፋር ህዝብ ፓርቲን መስርተዋል፤ በሊቀመንበርነት እያገለገሉም ነው፡፡

3. ኦባንግ ሜቶ – አባል

የትምህርት ዝግጅት

በካናዳ፣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳስካቺዋን በፖለቲካል ሳይንስ ተመርቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ የሚታወቁት በሰብአዊ መብት ተከራካሪነታቸው እና ለግፉዓን ጥብቅና በመቆም ነው፡፡ አሁን ላይ የSMNE የተባለው ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ከየትኛውም የፖለቲካ ውግንናና ከግጭት በራቀ መልኩ ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ ይሰራሉ፡፡ ነጻነት፣ ፍትህ፣ መልካም አስተዳደር እና ሁሉ አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚሰሩ ናቸው፡፡

ለዚህ ስራቸው መቃናት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርፉት አቶ ኦባንግ የተባበሩት መንግስታት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ፣ የስቴት ዲፓርትመንት፣ ሴኔት፣ የአለም ባንክ እና መሰል አለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎችን በተለያዬ ጊዜ አግኝተዋል፡፡

4. ዶክተር ወዳጀነህ መሃረነ – አባል

የትምህርት ዝግጅት

ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በህክምና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተመርቀዋል
ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በካውንስሊንግ ሳይኮሎጅ በኤም ኤ ተመርቀዋል
ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በትሮፒካል እና ተላላፊ በሽታዎች የሳይንስ ማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል
ፖስት ግራጅዌት ዲፕሎማ ከኢትዮጵያ ግራጅዌት ስኩል ኦፍ ቴክኖሎጂ
ፒጂዲ በመጽሀፍ ቅዱስና ቲዎሎጂ ጥናት

የስራ ልምድ

በፐብሊክ ሄልዝ ስፔሻሊስትነታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅና አላቸው፣ የህክምና ዶክተር እና የስነ ልቦና አማካሪ፣ ሞቲቨየሽናል ስፒከር እና ፐብሊክ ዲፕሎማት ናቸው፡፡
ዶክተር መሃረነ የተለያዬ መጽሃፍን እና ጥናታዊ ጽሁፎችን ለንባብ ያበቁም ናቸው፡፡

5. አቶ ማንያዘዋል እንደሻው አባል

የትምርት ዝግጅት

በጀርመን ዩኒቨርስቲ በአርት ማስተርስ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርት ቢ. ኤ.

የስራ ልምድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴያትር ጀ/ዳይሬክተር
በአዲስ አበባዩነቨርስቲ የአርት ዲፓርትመንት ሊቀመንበርና መምህር
ሀምራዊ የማስታወቂያ አገልግሎት
በጊዜያዊነት የጻሀፊያን ዳሬክተር
በኢትዮጰያ ብሔራዊ ቴያትር ዋና ሥራ አስኪያጅ

6. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ – አባል

• የትምርትዝግጅት

ፒኤችዲ ሶሺዎሎጂ፣ ካልቸር እና ሶሻል ፓወር ከዩኒቨርሲቲ ፈ ትሮምሶ ኖርዌይ
ኤምኤ በሊትሬቸር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ቢኤ በኢትዮጵያን ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍ

የስራ ልምድ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲ፡ ቋንቋዎች ጥናት የጋዜጠኝነት እና ኮምንኬሽም ኮሌጅ ተባባሪ ዲን
በረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የህትመትና ዌብ ጋዜጠኝነት የፕሮግራም ዩኒት አስተባባሪ ናቸው፣
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ጆርናሊዝን ኤንድ ኮምንኬሽን ጄንደር ስተዲ መምህርነት
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጋዜጠኝነትና በህዝብ ግንኙነት ትምህርት ቤት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፅነ-ጽሁፍና በቋንቋ ክፍል፣ በጋዜጠኞች ማሰልጠኛ ኢንስቲዮት መምህርና ረዳት መምህር
በእለታዊው እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሚያሳትመው አዲስ ዘመን በባህል ገጽ እና የሴቶች ገጽ ላይ በአዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡

7. አቶ ጌትነት ታደሰ – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የቦርዱ ፀሃፊ እና አባል

የትምህርት ዝግጅት

ኤም ኤ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን
ቢ ኤ ከባህርዳር ዩንቨርስቲ በጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን
ዲፕሎማ ከባህርዳር ዩንቨርስቲ በታሪክ

የስራ ልምድ

የኢትዩጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ያሉ
በዋልታ ቴሌቪዥን የቴሌቪዥን ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የሰሩ
በዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኔኬሽን ኮርፖሬት የዶኩመንተሪ ክፍል ዳይሬክተር ዋና አዘጋጅ እና አዘጋጅ ሀፐነው የሰሩ
በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የሰሩ
ባጠቃላይ ላለፉት 16 ዓመታት በሚዲያና ኮሙዩኔኬሽን ዘርፉ ላይ ከባለሙያ እስከ አመራርነት ያገለገሉ እና በትምህርት ዝግጅታቸውም በዚሁ በሚዲያና ኮሙዩኑኬሽን ላይ ያተኮረ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.