የፈንታ ደጀን የዘረፋ መጋረጃ ሲገለጥ – ዳግላስ (ከባህር ዳር)

ይድረስ ለአማራ ሕዝብና ለአማራ ክልል ካብኔ

ይድረስ ሰኢድ ኑሩ ዓሊ (ዶ/ር)

መቼም ሰይጣንና ፈንታ ደጀን ምን አገናኛቸው ብላችሁ እንደማትጠይቁኝ ባምንም ፈንታ ደጀን ሰይጣን ከመፈጠሩ በፊት የተፈጠረና ሰይጣን ምግባሩን ከፈንታ ደጀን እንደወሰደ ብዙ ማሳያዎችን ማመላከት ይቻላል፡፡ ይህ ግለሰብ በሊቦ ከምከም ወረዳ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ ሲሰራ የነበረው የዝርፊያ ተግባርና ግለሰቦች በኔት ወርክ መጠላለፍ ልዩ ተሰጥኦ እንደነበረው ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ ያጋለጠበት መረጃ ዋቢያችን ነው፡፡

ፈንታ ደጀን የእነበረከት ስምኦን ጋሻ ጃግሬ እንደነበረና ዛሬም የእስር ቤት የዘወትር የድብቅ ጠያቂያቸው እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ፈንታ ደጀን ማለት ምንም ዓይነት የአመራር ብቃት የሌለውና የተመደበበት ሕዝብን የማገልገል ሥልጣን የሀብት ማካበቻና የዘመድ አዝማድ መጠቀሚያ እያደረገ እንዳለ በአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በኃላፊነት ተመድቦ ሲሰራ ነበረው እኩይ ተግባር ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

ፈንታ ደጀን እልምና ጭልጥ ያለ ዘረኛ ነው፡፡ ትልቁ የባህርይው መገለጫ ከርሱ ጋር ቀሬቤታ ያላቸውን ግለሰቦች ማሾምና ወደእርሱ ማስጠጋት የተካነበት ሙያው ነው፡፡ ዛሬም በፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሆኖ ቢሾምም እንደንስር አሞራ የ27 ዓመቱ የኪራይ መሰብሰቢያ ጥርሱ እንደገና በሁለት እጥፍ በአዲስ መልክ አስሎ ተነስቷል፡፡ ምንጊዜም ከበድል ያልተላቀቅከዉና ከድህነትህ ፈቀቅ ያላልከው  የአማራ ህዝብ አንድም ዉሸት ሳልጨመር አንዲትም የብቀላና የስም ማጥፋት ቃል ሳላክል ይህንን እዉነተኛ ማስረጃ ላካፍልህ ወደድኩ፡፡

በስምህ መነገዱ ይብቃ፡፡ ፈንታ ደጀን ቀደም ሲል ተላብሶት የነበረው እኩይ መንፈስ አለቀው ብሎ የክልሉን ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮውን ሲያምስ መክረሙ ይታወቃል፡፡ በተለይ በቢሮው የመሠረተ ልማትና ቤቶች ዘርፍ እንዲመራ የተመደበውን ምስራቅ ተፈራና የከተማ ልማት የመሬት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ትልቅ የዘረፋና ሙስና ምንጭ የሥራ ክፍል መሆኑን በማወቅ ቀደም ሲል የሥራ ክፍሉን ሲመራ ነበረውን ግለሰብ ከዳይሬክተርነት አንስቶ የሟቹን እዘዝ ዋሴ የክርስትና ልጅ ወንድምነው ክንዱ የተባለውን ግለሰብ ከደቡብ ጎንደር ዞን አስመጥቶ እንዲሾም ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

ፈንታ ደጀን

የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በክልሉ አሁን ያለው አንጻራዊ የሰላምና መረጋጋት በመጠቀም ከብልጽግና ፓርቲ አባልነት ዉጭ የተሻሉ ግለሰቦችን በባትሪ ፈልገው ወደ ሥልጣን ማምጣትዎና ቀደም ሲል የሕዝቡ ደም ሲመጡ ነበሩ ግለሰቦችን ከአቅራቢያዎ ማራቅዎና በርካታ ሥራዎችን እዩኝ እዩኝ ሳይሉ ማከናዎነዎ  በእርግጥም የአማራን ህዝብ ስነልቦና የሚመጥን የአመራር ሚናዎትን እየተዎጡ እንዳሉ ቢሰማኝም አብዛኛው ካብኔዎ  እየተባበረዎ እንዳልሆነ ባውቅም በተጨማለቀ ቤት መግባትዎ እጅግ ቢያበቻጨኝም አንዳንድ ሸዋጅ የቀድሞ ቁማርተኛ ተላላኪ ህዝብን የበደሉና የዘረፉ እንደ ፈንታ ደጀንን ያሉ አመራሮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቀጥተኛና እዉነተኛ መረጃ ልሰጥዎ ፈለግሁ፡፡  ስለ አቶ ፈንታ ደጀን ዘራፊነት ተዘርዝሮ አያበቃም፡፡ አሁን ደግሞ አርሰዎን በመሸወድ በአንድ በኩል የዘረፈዉን ሃብት ላለማስነካት በሌላ በኩል ዘረፈውን ለማስቀጠል ሁለት ጥርስ በአዲስ ስሎ ዉስጥ ዉሰጡን አደራጅቶ እርሰዎን የሚያሳምንበትን ስልት ቀይሶ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ያሾመዉን አቶ ወንድምነዉ ከንዱን በሚመለከት ነዉ፡፡

አቶ ወንድምነዉ ምንም ልምድና እወቀት ሳይኖረዉ የተለያየ ሹመት በመስጠት ላለመወቀስ ደግሞ ምንም አይነት ለዉጥ ሳያመጣ በዉሸት ሪፖርት ሽልማት በማበርከት ከፍ ከፍ ሲያደርገው ቆይቷል፡፡ ፈንታ ደጀን የደቡብ ጎንደር ሕዝብ የዘረፈ ሥራዉ ስርቆት ብቻ የነበረ የሚሰርቅበትን ስልት ብቻ ሲቀይስ የኖረ በመሆኑ ወንድምነዉ ከንዱን የቢሮዉ የመሬት ልማትና ማኔጅመነት ዳይሬክተር አድረጎ መደበዉ፡፡ ቢሮዉ ዉስጥ ሁለት ም/ቢሮ ኃላፊዎች አያሉ ተደርጎ በማያዉቀዉ ሁኔታ 3ኛ ም/ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ውክልና ሰጠው፡፡ አሰራሩ የማይፈቅድ መሆኑ አንድ የቅርብ ወዳጁ ሲነገረዉ ለማሾም እንዲረዳኝ ብዬ ነዉ የሚል ምላሽ እንደሰጠው ሰምቻለሁ፡፡ ለካ ይህን ግለሰብ በ3ኛ ደረጃ በም/ቢሮ ኃላፊነት የሾመው ያለምክንያት እንዳልሆነ ያወቅነው በወረታ ከተማ በፈንታ ደጀን ያላግባብ መሬታቸዉን የተቀሙና የተነጠቁ ሰዎች አቤቱታ ሲጀምሩ ነው፡፡

ፈንታ ደጀን ከክልሉ እግሩን ባነሳ በማግስቱ አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ቢሮው የመጡት የወረታ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ ለማቅረብ በፈንታ ደጀን በተሸመው ወንድምነው ክንዱ ቢሮ ሲቀርቡ የተሰጣቸዉ መልስ ቀደም ሲል በቢሮው የመሬት ዘርፍ የሚከታተለውና በም/ቢሮ ኃላፊነት ተመድቦ ከጥቂት ወራት በፊት ከፈንታ ደጀን ጋር ባለመግባባት በአማራ ክልል ቤቶች ልማት ድርጅት የተመደበው ሷሊህ አቡ ልኳችሁ ነዉ አቶ ፈንታ ደጀን ፌዴራል ሳይደርስ የመጣችሁ ብሎ አቤቱታቸውን ሳይቀበል ከቢሮ እንዳስወጣቸው እናውቃለን፡፡

ፈንታ ደጀን በባህርዳር፣ በጎንደርና በኮምቦልቻ ከተሞች በሪል እስቴት ስም የአርሶ አደሮችን መሬት በማስለቀቅና ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር በመደራጀት ክፍተኛ የመሬት ዘረፋ እያካሄደ እንዳለ ቢታወቅም ይህን እኩይ ተግባሩን ለማስቀጠል ወንድምነው ክንዱ በኃላፊነት እንዳስቀመጠው በግልጽ መናገር ይቻላል፡፡

ሌላዉ በ2011 ዓ.ም ቀድሞዉን ካቢኔ ሸዉዶ ያሾመዉ ምስራቅ ተፈራን የሚመለከት ነዉ፡፡ ይህ ግለሰብ ዘሎ ያልጠገበ እንቦሳ፣ ማፊያና ዱርዬ ነው፡፡ አብዛኛውን ዕድሜ በክልሉ ምክር ቤት በአባልነት እጁን ብቻ ሲያወጣ የኖረ እንጂ የመንግስት መስሪያ ቤት ላይ ተቀጥሮ የማያዉቅ ምንም ስራ የማይችል ከመሆኑም በላይ ያዉቃል እንዲባል የማያዉቀዉን ብዙ የሚያወራ ሰዉ ነዉ፡፡

የከተማ ልማት ሰባኪው ምስራቅ ተፈራ

ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ስለምስራቅ ተፈራ  የቀድሞዉን የክልሉ ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ዩሴፍ ረታን በመጠየቅ ብቻ ዉሳኔ ላይ ሊደርሱ ይገባል፡፡

  • በጥቃቅን ያልተደራጁትን ተደረጅተዋል በሚል በሌሎች ስም በርካታ ገንዘብ በብደር  ከመንግስት ወስዶ ሳይመል በክስ ላይ ያለ፣
  • የአርቲስቶችን የፈጠራ ዉጤት ሰርቆ ያሳተመ ሲሆን በዚህም ተከሶ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ያለ፣
  • የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ልሆን ነዉ በሚልና ከደላላና ከሀገወጥ ነጋዴ ጋር አብሮ በማበር ጉዳያችሁን አስፈጽምላችኋለሁ በሚል ከበርካታ ባለሀብት በርካታ ገንዘብ ወስዶ እያስለቀሰ ያለ ግለሰብ ነው፡፡
  • እጅግ የሚገርመው በአንድ ወቅት ገንዘብ የሚያበድረዉ ቢያጣ የድሆችን የፑል ማጫወቻ ልከራያችሁ ብሎ ባህርዳር ዩኒቨርሰቲ ፖሊ ካምፓስ በዕዳ አስይዞ በፍርድ ቤት አስፈርደዉ ንብረታቸውን ላለማስረከብ መተማ ከተማ ተደብቆ የድሆችን ጉሮሮ ዘግቶ የነበረ ሰዉ ነዉ፡፡

ተጨማሪ መረጃ ላክል- በ2007ዓ.ም በአማራ ክልል ም/ቤት አባልነት በመሰረታዊ ድርጅት ለእጩነት የቀድሞው የባህር ዳር ከንቲባ የነበሩት አቶ ያየህ አዲስ  ምስራቅ ተፈራ ሲጠቁሙ የቀድሞዉን የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዩሴፍ ረታ በጣም ተበሳጭተዉ አቶ ያየህን ሰው ጠፍቶ ነው ወይስ  የምስራቅ ተፈራ ጉድ የማታዉቅ ሆነህ ነዉ የተቆምከው በሚል የምሰራቅን ጉድ አዉጥተዉ በተቃዋዉሞ ሃሳብ ሲያቀርቡ አቶ ያየህም ይቅርታ ሃሰቤን አንስቻለሁ በማለት ከዉድደር ዉጪ ከተደረገ በኋላ በማዕከላዊ ኮሚቴ  ምርጫ ላይ  እንዴት እንዳለፈ ባይታወቅም ፈንታ ደጀን በወጣቶች ሊግ እንዲተካና ስርቆቱን እንዲያቀላጥፍለት እርሱ ከሚመራው ከተማ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አድርጎ በማሾም በአዲሰ መልክ የስርቆት ጥርሱን በመሳል ምስራቅንና  ወንድምነዉን አሹሞ እሱ ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ መሾሙ  የፈንታ ደጀን እግርና አሻራ ከክልሉ እንዳልወጣ የክልሉ መንግስትም ሆነ አሁን ቢሮው እንዲመሩ የተሾሙት ሰኢድ ኑሩ ዓሊ (ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ በዓይነ ቁራኛ እንዲከታተሏቸው ከአደራ ጭምር ይህን መልዕክት ማስተላለፍ ወደድኩ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.