ከጣሊያን አገር ለኢትዮጵያውያን የተላከ መልዕክት

ሰላም ለሁላችሁ:-

እኛ በጣሊያን አገር ሚላን ነው የምንኖረው፡፡ አሁን ላይ በሚላን ህይወት ምን እንደሚመስል ልገልጽላችሁና በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ሆኜ እናንተ እኛ ከሰራነው ስህተትና በውጤቱም ከገባንበት አጣብቂኝ ህይወት የምትማሩት ቁም ነገር አለ ብዬ ነው ይህንን የምጽፍላችሁ፡፡

አሁን ላይ ሁላችንም በማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ፖሊሶች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ሲሆን ማንኛውንም ከቤት ውጪ ሲዘዋወር ያገኙትን ሁሉ በቁጥጥር ስር ያውላሉ፡፡ ሁሉም ነገር ዝግ ነው:- የንግድ ሱቆች፣ ሞሎች፣ የሽያጭ እቃ ማዕከሎች ሁሉም ነገር ዝግ ነው፡፡ የአለም ፍጻሜ ነው የሚመስለው! ለኑሮ ተስማሚና ጤና ማህይወት ታስተናግድ የነበረችው ጣልያን ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሰዓታትና ቅጽበት ከጨለማ ውጪ ምንም የሌለባት የተወረረች ከተማ መስላ ነው የምትታየው፡፡ እኔ ራሴ ተመልሼ በዚህች መሬት ላይ እንደ ቀድሞው በህይወት እኖራለሁ የሚለው ተስፋዬ ጨልሟል፡፡

እዚህ አገር ህዝቡ ግራ ገብቶታል፣ በመከፋት አንገቱን አቀርቅሯል፤ ተስፋ በመቁረጥም ይህ ሁሉ መዓት እንዴት እንደታዘዘበትና ይህም በቅዠት እንጂ በእውን የማይመስል የጭንቅ ወቅት መቼ እንደሚያበቃ ግራ ገብቶት በየቤቱ ተዘግቷል፡፡

ይህ ክፉ ቀን ግን የጀመረው ዝም ብሎ አልነበረም! አንድ ትልቅ ስህተት ነበር! ገና የኮሮና ቫይረስ (COVID – 19) አገራችን ጣሊያን እንደገባ በይፋ በተነገረባቸው የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ህዝቡ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ አኗኗሩን እንደተለመደው ቀጠለ፣ ህዝቡ ወደ ስራ መሄዱን አልተወም፣ ወደ መዝናኛ ቦታዎች እንደ ተለመደው በጋራ ይሄዳል እንደእረፍት ጊዜ ከጓደኞቹ ከሌሎቹም ጋር እንደተለመደው በብዙ ቁጥር መንጎዱን አላቆመም፡፡ ሁሉም መጨረሻውን ሳያስብ ትክክል ያልሆነ የኑሮ ዘይቤውን ቀጠለ፤ እናንተም እንደዚህ እየሆናችሁ ነው !

ልለምናችሁ ! እየቀለድኩ አይደለም፤ እባካችሁ ተጠንቀቁ ! የምትወዷቸውን ሁሉ፣ ቤተሰቦቻችሁን፣ ወላጆቻችሁን፤ አያቶቻችሁን ከዚህ መቅሰፍት ጠብቁ ! ይህ በሽታ በተለይ ለእነርሱ እጅግ አደገኛ ነው፡፡

እዚህ በቫይረሱ ምክንያት በየእለቱ የ200 ሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ሚላን ውስጥ ያለ መድሃኒት ስለማይረባ አይደለም፤ ከመድሃኒት ጋር ባለ ብቃት ሚላን ከዓለም ከፊት ተርታ ከሚሰለፉት አንዷ ነች፡፡

ለበርካቶች በየእለቱ ሞት ምክንያት እየሆነ ያለው ደግሞ ለእያንዳንዱ ለቅርብ ክትትል የሚበቃ በቂ ቦታ ባለመኖሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብታምኑም ባታምኑም ሀኪሞች ማንን እናትርፍ ሳይሆን ማን ቢሞት ብዙዎችን መታደግ ይቻላል የሚል አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው ቫይረሱ ወደዚህ ቦታ መግባቱ በተነገረበት የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት በህዝቡ ዘንድ የነበረው ሞኝነትና ችግሩን ተገንዝቦ ፈጥኖ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ህይወት በነበረው ሁኔታ እንዲቀጥል በማድረጉ ነው፡፡

እባካችሁ ከእኛ ስህተት ተማሩ! የእኛ አገር ትንሽ የህዝብ ቁጥር ያለበት ነው፤ እናም በአገር ደረጃ እጅግ የከፋ ፍጻሜ እንዳይኖረን ያሰጋል፡፡ እባካችሁ በደንብ አዳምጡኝ፡-

• ህዝብ በብዛት ባለባቸው ስፍራዎች አትሂዱ፤
• ብዙ ህዝብ በሚጋራቸው ቦታዎች ላይ ላለመመገብ ሞክሩ፤
• በዚህ ወቅት ብዙ ጊዜ በቤታችሁ ተቀመጡ፤
• ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሰጡ መመሪያዎችን አዳምጡ፤ አዳምጣችሁም ተግብሩ (እንደቀልድ አትዩአቸው !)
• ከማንኛውም ሰው ጋር ስታወሩ ከአንድ ሜትር በላይ በሆነ ርቀት ላይ ሆናችሁ አውሩ፣ አትጠጋጉ፣ አትተቃቀፉ፣ አትጨባበጡ፤
• ማድረግ ያለባችሁን የመከላከያ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ከሌሎች ስህተትም ተማሩ፤
• በሽታ የመከላከል አቅማችሁ እንዳይዳከም ‘ቫይታሚን “ሲ” ተጠቀሙ
• የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱን ለመከላከልና ስርጪቱን ለመቆጣጠር ለሚያደርጉት ጥረት አጋዥ ሁኑ

ጣሊያን ውስጥ መላ አገሪቱ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ እንዳለች ቁጠሩት፤ 60 ሚሊዮን ህዝቧ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው እንደማለት! ታዲያ ህዝቡ በመጀመሪያ ላይ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን አዳምጦ ተግባር ላይ ቢያውል ኖሮ ይህ ሁሉ መጥፎ ቀን እንዳይመጣ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡

እናም እባካችሁ ሳይመሽ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችሁንና የምትወዷቸውን ሁሉ ጠብቁ !!!

መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ
ከአንድ ጣሊያናዊ/ት ወዳጅ (Jsca) የተጻፈ።

ይህ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንቂያ ደወል ነውና እንጠቀምበት!

#ጣሊያን
#ኢትዮጵያ
#ዓለም

3 COMMENTS

  1. የሃገራችን ሰው ጀሮ ያለው ይስማ ይላል። እንዴት ልክ ሃሳብ ነው። ከወደ ኢጣሊያን ይህን መልካም ሃሳብ ስላካፈላቹሁን እናመሰግናለን። አዎ ጊዜው የማይታለፍ ይመስላል። ግን ሁሉም ነገር ነፋስ ይመታዋል። ይቀየራል። በቀልድና በቧልት እኔን አያመኝም በማለት እንደፈለጉ መሆን ተገቢ አይደለም። ችግሩ ከባድ ነው። ግን የዓለም መጨረሻም አይሆንም። ድሮም እንዲህ ሆኗል። ዛሬም እየሆነ ነው። ወደፊትም ይሆናል። እንዴት ብትሉ በነጮች በ 1918-1919 “የስፓንሽ ኤንፍሎንዛ” በተባለ ቫይረስ 50 ሚሊዪን ህዝብ አልቋል በዓለም ዙሪያ! እናም ምጻተ ዓለም ገና መጪ እንጂ በራችን ላይ አልቆመም። ግን ክፈቱልኝ ልግባ ብሎ የቆመ ይመስላል።
    ህዝባችን ራሱን ከሰው ማራቅ፤ እጆቹን መታጠብ፤ ለወራት ሊበቃ የሚችል ጥራጥሬና ሌሎች የማይበላሹ ነገሮችን ማጠራቀምና ለመከራው ቀን መዘጋጀት ያስፈልገዋል። ዝብ ብሎ ይህ በእኔ ላይ አይደርስም ማለት በራስንና በቤተሰብ በሃገርም ላይ መቀለድ ነው። በየሚዲያው የበሽታው መድሃኒት ተገኝቷል፤ ይህ ፍቱን መድሃኒት ነው የሚባለው ሁሉ የውሸት ጋጋታ ነው። ለምሳሌ የማላሪያ በሽታ መከላከያ መድሃኒት የኮሮና ቫይረስን ያድናል መባሉ እንደ ሃገራችን የጠበል ውሃ ነው። ሳይንሳዊ ያልሆነ የፓለቲካ ቱልቱላ! በሶሻል ሚዲያና በተለያዪ አፕዎች ላይ መድሃኒት እንደተገኘ ወይም ምንም ምን ሰው ማድረግ እንዳለበት የሚሰራጩ ሁሉ ከንቱ ሃሳቦች ናቸው። ለምሳሌ በቅርቡ የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የወጣ አንድ አፕ ስልካቹሁ ላይ ካወረዳቹሁት በህዋላ ስልካቹሁን በመቆለፍ ገንዘብ ለዚያውም በቪትኮይን ካልተከፈለ ጠርቅሞ ይዘጋባችሁሃል። ሰው የሰውን መጨነቅ አይቶ የማይሰራው ክፉ ስራ የለም። በዚያው ልክ ሌላውን እየረድ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡት ወደ 17 የሚጠጉ የጣሊያን ዶክተሮች አይነትም መልካም ሰዎች አሉ። አጉል መጨነቅ ሌላ በሽታ ያመጣል እንጂ ምንም ጥቅም የለውም። ሞት መጣ ቢሉት አንድን ግባ በለው እንዳለው ሰው አይነት ነው። ቫይረሱ ከ 4-14 ባሉት ቀናቶች ይከሰታል ተብለናል። ራስን ለይቶ በእነዚህ ቀናት የህመም ምልክቱ ካልታየ ለአሁኑ ዙር ተርፈናል ማለት ነው። Spillover: Animal Infections and the Next Human Pandemic by David Quammen በማንበብ በቫይረስ ዙሪያ ያለውን አስከፊ ግብግብ መረዳት ይቻላል። ዓለማችን ከቫይረስ ነጻ ሆና አታውቅም። በጣሊያንም ሆነ በመላ ዓለም ተበትነው በቤታቸው ተዘግተው የቫይረሱን ውርጅብኝ ማለፍ ለሚጠባበቁ ኢትዮጵያውያንና የዓለም ህዝብ ምክሬ አንድ ነው። ልክ እንደ ወታደር ወገብን ጠበቅ አርጎ ቀኑን በብልሃት ለማሳለፍ መታገል ነው። እንበርታ፤ አይዞን፤ ነገም ጸሃይ አለችና!

  2. In the next eight weeks by May 2020 , fifty six percent of the California , USA population amounting to 25+ millions people California residents are expected to get infected with CoronaVirus Covid-19 according to the California State Governor Gavin Newsom in USA.

    California projects 56 percent of population will be infected with coronavirus over 8-week period | TheHill

  3. Doordash food delivery corporation is saying it can cut the transmission by half if African countries give Doordash Corporate a business permit to start operation within weeks time from now in African countries such as Ethiopia.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.