‹ከ500 በላይ ሰራተኞች ከወርልድ ቪዥን ሊለቁ ይችላሉ ተባለ – ዳኒዬል ፈይሳ

‹‹ከ500 በላይ ሰራተኞች ከወርልድ ቪዥን ሊለቁ ይችላሉ፡፡እስካሁን 170ሰራተኞች መልቀቂያ አስገብተዋል፡፡››ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ሰራተኛ።

መንግስት ባወጣው አስገዳጅ ህግ ምክንያት ከ500በላይ ሰራተኞቹን ሊያጣ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት 170ሰራተኞች መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው፡፡በ2012(2004) ዓም በወጣው የማሃበራዊ ዋስትና አዋጅ መሰረት የጡረታ ፈንድ ተቋቁሞ ሁሉም ሰራተኛ ማሃበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ሲደረግ የዕርዳታ ድርጅቶች ደግሞ ከፕሮቪደንት ፈንድ እና ከጡረታ እንዲመርጡ መደረጉ ይታወሳል፡፡በዚህም መሰረታ አንዳንድ ትላልቅ የዕርዳታ ድርጅቶች በተለይ ረዥም አመታትን በሀገሪቱ ውስጥ ያስቆጠሩቱ ፕሮቪደንት ፈንድ ይሻለናል ብለው በዚያው መሰረት ገንዘባቸውን ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡

አሁን ቀደም ሲል የወጣው ህግ በአዲስ ረቂቅ እና አስገዳጅ አንቀፆችን አካቶ ሁሉም ሰራተኛ ያለው የተጠራቀመ ገንዘብ ወደ ጡረታ ባንክ እንዲገባ ሊደረግ ነው በሚል የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች በከፍተኛ ወከባ እና ስነልቦናዊ ጫና ውስጥ መውደቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡በዚህም መሰረት አንዳንዶች የሰራተኞቻቸውን ህይወት ቅድሚያ በመስጠት አወያይተው መፍትሄ ሲፈልጉ እንደወርልድ ቪዥን ያሉቱ ደግሞ የመንግስትን ህግ ለማስፈጸም እንደሚተጉ ሰራተኞቹ ትዝብታቸውን ይገልፃሉ፡፡

ቀደም ሲል የፕሮቪደንት ፈንዳቸውን አሲዘው ከባንክ ብር መበደር እሚችሉ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህንን ማድረግ ባለመቻላቸው ሰራተኞቹ ገንዘባቸው በግል አካውንታቸው እንዲገባለቸው ሲጠይቁ እንደማይቻል እየተገለጸላቸው ነው፡፡ይህ በቻ ሳይሆን አንዳንድ የድርጅቱ ሃላፊዎች ገንዘባቸውን ቀድመው የወሰዱ ሲሆን ሌሎች እንዳይወስዱ መደረጋቸው አድሎአዊ አሰራር መሆኑን ይናገራሉ፡፡በተጨማሪም የድርጅቱ ሰው ሃይል አስተዳደር ‹‹ድርጅቱን ካለቀቃችሁ በቀር ገንዘባችሁን አታገኙም በማለት የተናገራቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በዚህም መሰረት ሰራተኞቹ ገንዘባቸው ከሚያዝባቸውና ህጉ ገና ያልጸደቀ ሆኖ ሳለ ድርጅቱ መፍትሄ ያልሰጣቸው በመሆኑ መልቀቂያቸውን በማስገባት ላይ ናቸው፡፡ወርልድ ቪዥን በመላ ሀገሪቱ በእርዳታ ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው አስተዳደር ሰራተኞቹን መብት ከማክበር ይልቅ ለመንግስት ውገና ያለው መሆኑን ሰራተኞቹ አምርረው ይናገራሉ፡፡

ረቂቅ ህጉ በፓርላማ ለውይይት ቀርቦ ለቋሚ ኮሚቴ ተላለፈ ሲሆን በቀጣዮቹ ሳምንታት ሊጸድቅ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ይህ ከሆነ ሰራተኞቹ ከገንዘባቸውም ሳይሆኑ ከስራ እንዳይባረሩ ሲሉ አንዳንድ የህግ ሰዎች ይመክራሉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.