በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ኦነግ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቢሮውን መዝጋቱን አስታወቀ

በኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ኦነግ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቢሮውን መዝጋቱን አስታውቋል።

አዲስ አበባ ብዙ እንቅስቃሴዎች የሚከናወኑባት እና ከውጪ አገራት መንገደኞች የሚመጡባት ከተማ እንደመሆኗ የቫይረሱ ስርጭት በከተማዋ ከፍ ያለ መሆኑ ይታወቃል ብሏል ኦነግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ።

በዚህም ምክንያት ግንባሩ በጉለሌ የሚገኘውን ቢሮውን መዝጋቱን አስታውቋል።

ህብረተሰቡም በሽታውን ለመከላከል አስፈላጊ የተባለውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪውን አቅርቧል።

BBC

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.