ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግሥቴ ” በረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 -1887 ዓ/ም) (ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግሥቴ)

ፕሮፌሰር ሀብታሙ መንግሥቴ ” በረራ ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 -1887 ዓ/ም) ” የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቀተዋል።
ይህ መጽሐፍ በርካታ ታሪካዊ መረጃና ማስረጃዎችን ሊያካትት እንደሚችል የፕሮፌሰሩን የቀደሙ ስራዎቻቸውን በማየት ከወዲሁ መገመት ይቻላል።

ፕሮፌሰር ሀብታሙ ከዚህ ቀደም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሰሜን ምዕራብ የሃገራችን ክፍል በዲማ ጊዮርጊስና መርጡለ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት መካከል ተነስቶ የነበረውን አለመግባባት በተመለከተ “Dispute over precedence and protocol: Hagiography and forgery in 19th-century Ethiopia” በሚለው ጥናታዊ ጽሑፋቸው ያካተቷቸውን በርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች መመልከት ይቻላል።

ፕሮፌሰር ሀብታሙ በዚህ ጥናታዊ ጽሑፋቸው የሁለቱን ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት ውዝግብ በተመለከተ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ምንሊክ ከጎጃሙ ንጉሥ ተክለ ሐይማኖት ጋር የተላላኳቸውን ጦማሮች አያይዘው ያስነብባሉ። ለቅምሻ ያህል አንዱ የዐፄ ምንሊክ ጦማር እንደሚከተለው ይነበባል:

ሞዓ፡ አንበሳ፡ ዘእምነገደ፡ ይሁዳ፡ ዳግማዊ፡ ምኒልክ፡ ሥዩመ፡ እግዚአብሔር፡ ንጉሠ፡ ነገሥት፡ ዘኢትዮጵያ።

ይድረስ፡ ክንጉሥ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ርቱዓ፡ ሃይማኖት፡ ወልዱ፡ ለቅዱሥ፡ ማርቆስ፡ ወንጌላዊ።
ወንድሜ፡ እጅጉን፡ እንዴት፡ ነህ። እኔ፡ እግዚአብሔር፡ ይመሥገን፡ ደኅና፡ ነኝ። ዲሞችንና፡ መርጡለ፡ ማሪያሞችን፡ አጋጥሜ፡ ነገራቸውን፡ ጨረስሁላቸው፤፡ ነገሩም፡ እንዲህ፡ ነው። ዲሞች፡ መርጡለማሪያሞችን፡ በአብርሃ፡ ወአጽብሃ፡ አልተተከላችሁም፡ ይሏቸው፡ የነበረውን፡ አብርሃ፡ ወአጽብሃ፡ ተክለዋችኋል፡ ብለው፡ ተፈጸሙላችው። ነገርግን፡ ቀድሞ፡ ስለተተከላችሁ፡ ሹመትም፡ ቡራኬም፡ እቤተ፡ መንግሥትም፡ እተስካርም፡ ቀድሞ፡ መግባት፡ ለኛነው፡ ከጃችን፡ ወጥቶ፡ አያውቅም፡ አሏቸው። መርጡለማሪያሞችም፡ በአብርሃ፡ ወአጽብሃ፡ መተከላችነን፡ ካመናችሁልን፡ ቡራኬውንም፡ እቤተመንግሥት፡ መግባትም፡ ፈጽማችሁ፡ ልቀቁልን፡ አሏችው። በዚህ፡ ተፋረዱ። ፍርዱ፡ ግን፡ መርጡለ፡ ማሪያሞች፡ ቀድሞ፡ ሥለተተከሉ፡ ቡራኬም፡ እቤተ፡ መንግሥትም፡ ቀድሞ፡ መግባት፡ በዲሞች፡ እጅ፡ እስካሁን፡ ከኖረ፡ ዲሞች፡ ይርቱ፡ ተብሎ፡ በመኳንቱም፡ ቃል፡ በፍትሐ፡ ነገሥትም፡ ተፈረደ። በዚህ፡ ቃል፡ አረታተን፡ አፈጣጥመናቸዋል። አሁንም፡ መርጡለ፡ ማሪያሞች፡ በአብርሃ፡ ወአጽብሃ፡ አልተተከሉም፡ እየተባለ፡ ተጽፎብናል፡ በደብሩ፡ ብለዋልና፡ ከየደብሩ፡ የተጻፈው፡ ይፋቅላቸው።
ቡራኬና፡ እቤተ፡ መንግሥት፡ ቀድሞ፡ መግባት፡ እስከ፡ አሁን፡ በዲሞች፡ እንደሆነ፡ ይጽና። ይህን፡ አያፍርሱ።

ሰኔ፡ ብ፳፯፡ ቀን፡ በደብረ፡ ማርቆስ፡ ከተማ፡ በ፲፰፻፹፱፡ ዓመተ፡ ምሕረት፡ በንጉሥ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ፈቃድ፡ ተጻፈ፡ ታተመ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.