የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ወደመጡበት አከባቢ እንዲመለሱ ተወሰነ

ሙሉ መግለጫው

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሁሉም የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎችን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት ተማሪዎች ከመጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ሳምንታት ባሉበት ሆነው በመምህራኖቻቸው የሚሰጡ ንባቦችን እያካሄዱ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በውሳኔው መሰረት ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዎች ሲቆዩ የንፅህና መጠበቂያዎችን ከማሟላት ጀምሮ እንዳይተፋፈጉ ተጨማሪ ዶርሞችን የማዘገጃት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በየዶርሞቻቸው ድረስ የቤተመጻህፍት አገልግሎት ሲሰጥም ቆይቷል፡፡ ይሄንንም የሚከታተል በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክብርት ሚኒስትር በዩኒቨርስቲዎች በፕሬዚዳንቶች የሚመራ ግብረሃይልም ተቋቁሞ ክትትል ሲያደርግ ሰንብቷል፡፡

ይሁን እንጂ ይሄው ግብረ ኃይል ባደረገው የአፈፃፀም ግምገማ የሚከተሉትን ተገንዝቧል፡፡
1. የተማሪዎች የመውጣት እና ወደየአከባቢያቸው የመሄድ ፍላጎትና ጫና መኖሩን
2. በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች እስከ 50 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከግቢ መውጣታቸውን
3. አንዳንድ ተማሪዎች ለቫይረሱ አስፈላጊውን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ አለመሆናቸውን እና
4. በተለያዩ መንገዶች ወደከተማ በመውጣት ከህብረተሰቡ ጋር እየተቀላቀሉ ወደ ግቢያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ነው፡፡
ከግምገማው በኃላ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ በአካል የሚሰጥ ትምህርት ለጊዜው ካለመካሄዱ ጋር ተከትሎ እንዲሁም እንደተጠቀሰው በርካታ ተማሪዎች ቀድመው ከመውጣታው ጋር ተያይዞ ያሉትን ተማሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ወደመጡበት አከባቢ እንዲሄዱ የሚል ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

ስለሆነም ዩኒቨርስቲዎች እንደየራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ በአከባቢያቸው ካሉ የትራስፖርት አካላት እና የጤና ተቋማት ጋር በመነጋገር መኪኖቹን ከማፅዳት ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ ተማሪዎቻቸውን የመጓጓዣ እጥረት በማያስከትልና ለቫይረሱ በማያጋልጥ ሁኔታ እንዲያጓጉዙ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን አንድ ጊዜ በማስወጣት ሳይሆን መተፋፈግ በማይኖር ሁኔታ ተማሪዎቻቸውን ማጓጓዝ የሚችሉበት የማስፈፀሚያ እቅድ ነገ በሚደረግ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ቀርቦ የሚገመገም ሲሆን ከዚያ በኃላ እንደየዩኒቨርስቲዎቹ ተጨባጭ ሁኔታ በሚዘጋጁ ፕሮግራሞች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተማሪዎች አገልግሎት የሚያገኙ ይሆናል፡፡

ወደየቤተሰቦቻቸው የሚሄዱ ተማሪዎች መንግስት ሌላ ውሳኔ እስከሚያስተላፍ ድረስ በየቤታቸው የሚቆዩ ሲሆን በቆይታቸውም ቫይረሱን ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ያሳስባል፡፡

በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጉዳዩ ላይ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በተከታታይ የሚያቀርብ መሆኑን እየገለፀ አፈፃፀሞቹም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚሰጡ መመሪያዎችና መረጃዎች መሰረት እንዲሆን ያሳስባል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም

1 COMMENT

  1. The University students needed to be provided with in home wardrobes if they were expected to stay inside their parent’s homes ,now without the in home clothes the students are putting their regular clothes on and mingling outside by risking the CoronaVirus Covid-19 infection . Please donate inhome stylish clothes for the students so they can stay in home.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.