ሰበር ዜና … መከላከያ ላሊበላ በሚኖሩ የፋኖ አባላት ላይ ግደያ ፈፀመ

አምስት መቶ አባላት ያሉት የሀገር መከላያ ሰራዊት ወሎ ላሊበላ ገብቷል፡፡ ከላሊበላ ከተማ በሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የገጠር ቀበሌ ብልባላ እና አካባቢዋ የሚገኙ የፋኖ አባላት ላይ ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ድንገተኛ ተኩስ እንደከፈቱባቸውም ያነጋገርናቸው የፋኖ አባላት አስታውቀዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ ቦታው ያቀኑት በኮሮና ተህዋሲ ምክንያት ማህበረሰቡ ከገጠር ወደ ከተማ እንዳይገባ ለመከልከል እንደሆም ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በአካባቢው ንፁሃን አርሶ አአደሮች ላይም ተኩስ ከፍተዋል፡፡ የቆሰሉና የተገደሉ የፋኖ አባላትና አርሶ አደሮች መኖራቸውንም በስልክ ያነጋገርናቸው የፋኖ አባል አስታውቀዋል፡፡

መንግሥት እና ፋኖ ሰሞኑን በሽምግልና ሲደራደሩ ሰንብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተስማሙባቸው ኃሳች ይፋ አልተደረጉም፡፡

መረጃው የኢትዮጲስ ነው፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.