ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ቻይና ሁለት ክትባቶችን በሰዎች ላይ ሞከረች

መነሻውን ቻይና አድርጎ ዓለምን ስጋት ላይ ለጣለው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ቻይና ሁለት ክትባቶችን በሰዎች ላይ “በክሊኒካል ሙከራ ደረጃ” መሞከሯንና ተስፋ ሰጭ መሆኑን ዥንዋ ዘገበ።ክትባቶቹን እየሠሩ የሚገኙት የቤጂንጉ ሲኖቫች ባዮቴክ እና የውሃን ሥነ ሕይወታዊ ምርቶች ተቋም ከቻይና ብሔራዊ የመድኃኒት ድርጅት ጋር ነው።
ባለፈው ወር በቻይና ወታደራዊ ሕክምና ሳይንስና ካን ሲኖ ባዮ በተሰኘ ተቋም በጋራ እየተደረገ ያለ የክትባት ምርምርም በሰዎች ላይ እንዲሞከር ፈቅዳ ነበር፤ ይህም ከአሜሪካው በሰው ላይ ሙከራ ላይ ከሚገኘው ክትባት ቀጥሎ ተስፋ የተጣለበት ሂደት ሆኗል።
የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን አደገኛ ወረርሽኝ ለመግታት ክትባት ወሳኝ መሆኑን አስታውቋል። ወረርሽኙ በዓለማቀፍ ደረጃ እስከ ዛሬ ከ114 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድሏል። “የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም “አብሮነታችንን እየፈተነ ያለውን ወረርሽኝ ለመግታት ፍቱን የሆነ ክትባት አስፈላጊ ነው” ማለታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.