የኢንጅነር ስመኛዉ በቀለ አባት የመኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው ቃል ተገባ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኛው በቀለ አባት አቶ በቀለ አይናለም በጎንደር ከተማ አስተዳደር የፋሲል ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሸንበቂት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ናቸው፡፡

እርሳቸው አሁን የሚኖሩበት ቤት ደረጃውን የጠበቀ አይደልም። ይህንም በመረዳት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር በሪሁን ካሳው የዘንድሮዉን የፈሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የበግ ስጦታ ሲያበረክቱ ከቦታዉ በመገነት በታቸዉን መጎብኘት ችለዋል፡፡

በእለቱ ምክትል ከንቲባው ቤታቸዉን ካዩ በኃላ በአስቸኳይ ቤት እንዲሰጣቸዉ ለፋሲል ክፍለ ከተማ ትእዛዝ ሰጠዋል፡፡ ከክፍለ ከተማው ስራ አስፈፃሚ ከአቶ አበራ አደባ ጋር በመወያየት በክፍለ ከተማው የመኖሪያ ቤት ተፈላልጎ እንዲሰጣቸው ስምምነት ተደርሷል፡፡

የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.