ፖሊስ አላሰርኩትም › ያለውን አስራት አብርሃምን ፍርድ ቤት አቀረበ

ጋዜጠኛ ዳዊት ስሎሞን

በቡራዩ ፖሊስ ታስረው የነበሩ የመድረክ አመራር አባላት አሁን ተለቀቁ። ክስ አልተመሰረተባቸውም። ያለ ምንም ጥፋት ለአራት ቀናት ታስረዋል። አሥራት አብርሃም ለብቻው ታስሮ ተገኝቷል። ዛሬ ፍርድቤት 

የመድረክን ሰላማዊ ሰልፍ በመቀስቀስ ላይ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጣብያ በመታሰራቸው ትናንት ከአንድ የአረና ፓርቲ አመራር ጋር ለጥየቃ ያመራው ፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃም በጣብያው መታሰሩን ቤተሰቦቹና የአንድነት አመራሮች ሊጠይቁት እንደሄዱ የከተማይቱ ፖሊስ ‹‹አስራት አብርሃም›. የሚባል ሰው አለማሰሩን በመግለጽ አስራትን መሰወሩን ት መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት አስራትን አላሰርኩም ያለው ፖሊስ ፖለቲከኛውን ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡በፍርድ ቤት የቀረበው የአንድነት ፓርቲ አባል ‹‹ምሽቱን በፖሊሶች መደብደቡንና ፖሊሶቹም ለሌት ላይ ህክምና እንዲያገኝ ክሊኒክ እንደወሰዱት አጋልጧል፡፡
አንድ ፖሊስ ‹‹ሰድቦኛል››በማለት ክስ የመሰረተበትን አስራትን በ500 ብር ዋስ እንዲፈታ ክብርት ዳኛዋ ቢወስኑም ፖሊስ አልፈታም ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.