በ”ፒኮክ” (ጣዖስ) ዙሪያ የተጧጧፈው ውዝግብ – ታየ ደንድአ

ከየትኛውም አይነት ሚዲያ ተለይቼ የራሴን ህይወት የመምራት እቅዴ ላይ ፈፅሞ አልደራደርም። ሆኖም ዶክተር ዓቢይ ቤተመንግሥት አኖሩት በተባለው “የፒኮክ ቅርፅ” ዙሪያ ኃይለኛ ሙግት ዐስተዋልሁና በዝምታ ማለፍ ከበደኝ።
“An idle mind is devil’s workshop”
ለሥራ ያልታደለ አእምሮ ለተንኮል ተወዳዳሪ የለውም እንዲሉ፤ አንዱ ወገን ቀን ከሌት ጠንክሮ አገር ለማጎልበት ይታትራል፤ ሌላው ላይበስል ተወዝቶ – ከመፍትሔው ላይ ችግር በመፈለግ ይጠመዳል።
በየትኛውም መለኪያ ብንመዝን The former group ለለውጥ የቻለውን ያህል ራሱን ሰውቶ ደፋ ቀና ሲል፤ The latter ‘ቦምቦሊኖ ቀርቦለት ቀዳዳው ላይ እያፈጠጠ’ ለማሰናከል ቁልቁለት ይወርዳል።
*
በተለምዶ ፒኮክ በመባል የሚታወቀው የአእዋፍ ዝርያ ተገቢ መጠሪያው “ፒፎውል/ Peafowl” ነው። ወንዶቹ (ተባእቱ) Peacocks ሲባሉ፣ ሴቶቹ (እንስቶቹ) ፒሄንስ Peahens በመባል ይታወቃሉ።
*
ቤተመንግሥት ላይ ምን አይነት ምልክት ይቀመጥ?
1. አንበሳ፦ ከሞዓ አንበሳ ጋር ተያይዞ አሉታዊ ስሜት ሊፈጥር ከመቻሉም ሌላ የ80ውን ብሔረሰብ እሴቶች ሊያንፀባርቅ ባለመቻሉ እረፍት አልባ ንትርክ ያስነሳል።
2. ግመል፦ አርብቶ አደሩን በሚገባ ሲወክል፤ ደጋውን ወገን ያገላል። ግመልን ለማይመገቡ ወገኖች ሌላ ትርጓሜ ያሰጣል።
3. የመደመር ምልክት፦ ቢደረግ በእርግጠኝነት ክርስትናን ለማጉላት ነው የሚል የማያባራ ሙግት ይፈጥራል።
***** ለዚህ “ቡራቡሬ” ወገን የሚመጥነው ቡራቡሬ ምልክት ነው።
*
ፒፎውል (ፒኮክ/ ፒሄን)
1. ቡናማ ቀለም ያላት ፍጥረት ስትሆን ብርሀን ሲያርፍባት የተለያዩ ህብረቀለማትን ታመነጫለች (80 ብሔረሰብ + የተለያዩ እምነቶች + የፖለቲካ አመለካከቶች + ፆታዎች…)
2. ይህንን ውበት ይዘው ፍጥነታቸው በሰአት ከ10_16 ኪሎሜትር ሲሆን (በሉላዊነት ዘመን ለጊዜው በዚህ ፍጥነት ብናድግ ይበቃናል)
አደጋ ሲያጋጥማቸውም በከፍታ መብረር ይችላሉ።
3. ቤተመንግሥቱ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም ያስተናግዳል። በአንዳንድ የዓለም ሀገሮች “ፒፎውል / ፒኮክ”፦ የትህትና የደግነት የዕውቀት የጥበብ ወዘተርፈ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ሂንዱይዝም ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ነው።
4. ፒፎውል፦ 11 የተለያዩ ድምፆችን በማውጣት በርካታ አይነት ጥሪዎችን የማድረግ ብቃት አላቸው። እነዚህ ድምፆች ሲነጋና ሲመሽ እርስበርስ በመጠራራት ድንቅ መስተጋብር የሚያደርጉበት ነው። እኛም በመልካም እና በአደጋ ጊዜ በወል ቆመን ማለፍ እንዳለብን ያመለክታል። ጥሪዎቹ ፍቅርንና በአደጋ ጊዜ መጠንቀቅንም አመላካቾች ናቸው።
5. ፒኮኮች፦ በአደጋ ጊዜ ኃይለኛ ተዋጊዎች ናቸው። እባብን ሳይቀር ቀጥቅጠው የመግደል ድንቅ ብቃት አላቸው። መርዘኛ እባቦችን የማጥፋትና ወደ ግዛታቸው እንዳይገቡ መከላከል ላይም የሚደነቅ ብቃታቸውን አስመስክረዋል።
6. ፒፎውል፦ ከሰዎች ጋር የመቀራረብ እና የመሰናኘት ልዩ ሁኔታ አላቸው። አፍቃሪ የመሆናቸውን ያህል ከነኳቸው አፀፋዊ ምላሻቸው ጠንካራ ነው።
7. ህብረቀለማት፦ ሰማያዊ አረንጓዴ ቡናማ ወርቃማ ቀይ… ቀለማትን የተላበሱ ልዩ መስህብ ያላቸው ናቸው።
8. ስጋንም ሆነ ዕፅዋትን የሚመገቡ Omnivores መሆናቸው በራሱ ብዙ የሚናገረው ነገር አለ።
9. ማህበራዊ አኗኗራቸው ያስደምማል።
10. ከስብዕና አንፃር ልሂቃን የአንድን ሥፍራ የትኩረት ማዕከልነት ያመላክታሉ።
11. ምሁራን። ፒኮክን Bird Personality አድርገው ሲገልፁት – በውይይት ማመን፤ ዘለግ ያለ ጣፋጭ ንግግር የማድረግ ብቃትንና ከምንም በላቀ ሁኔታ በሌሎች ላይ ተፅዕኖ የማሳደርን የአሸናፊነት ስነልቡና Winning Wisdom ይገልፁበታል።
12. በር ላይ የሚቀመጡ ውበቶች ብቻ አድርገን ብንወስዳቸው እንኳ ከበቂ በላይ አሳማኝ ነው።
*
ከዚህም አልፎ አያሌ መዘርዝሮችን መተንተንና ማስተንተን ይቻላል።
መከራከሪያው ከኢትዮጵያውያን እሴት ጋር አይገናኝም ከሆነ፤ የትኛው ነው የሚገናኘው?
“ፍለጠው ቁረጠው አድቅቀው” ወይስ ፈጣሪን መፍራት ትህትና የጋራ ውበት… blah blah blah ብሎ መሰነጣጠቅና ጥላቻ ማመንጨት አይከብድም። አስቸጋሪው በጥበብ ፍቅርን መመሥረት ነው።
*
አንበሳ፦ የመስበር የማድቀቅ ምልክት ሆኖ፦
“ዘራፊ ማልአባሺ ወዲ-ሰበይቲ” ማለት ለለመደ ቁምነገርና ፍቅር አይጥመውም።
*
በዚህ ዙሪያ መፃሕፍት ማዘጋጀት ቢቻልም።
ቤተመንግሥቱ በር ላይ ብቻ ነው ያለው ማነው?!
መንግሥት የሚኖርበት ዋና ቤት አለ። ያውም ከህያው ንጉሠነገሥት ዓቢይና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር።
የእምዬ ምኒልክ ቤተመንግሥት አለ። በዚህ ውበት ላይ ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ሥፍራዎች እና ቅርሶች ከረቂቅ መልዕክት ጋር በአቢቹ “ተደምረው” እኚያውልህ!!! መሥራት ባትችል ግባና ጎብኝተህ፤ ውበትን ማድነቅ የሚችል ህሊና ካለህ ብቻ አድንቅ! (መንገድ ላይ ሱሪ ከመፍታትና ወገብ ከመፈተሽ ሳትላቀቅ – አቃቂር ለማውጣት አትውተርተር።)
*
የቤተመንግሥቱን በር አልፈህ ገብተህ ከብፌው አድንቀህ መሸመት ይከብድሀል። የትየለሌ ድንቅ ውበት!!!
ምንድነው ከአምስት ሜትር ባነሰ በር ላይ ተገትሮ፤
2ኪሎሜትር × በ1.5ኪሎሜትር የሆነ፤ የ6,000 ዘመን ታሪክ የሚንፀባረቅበት ቤተመንግሥት መተቸት?!
የአንበሳ ፍቅር እንዲወጣልህ እዚያው ቤተመንግሥቱ ፓርክ ውስጥ ህያው አንበሶች አሉ። ዋሻ ጭምር… ከሰው ስጋ እየከጀሉ፤ አሥረን የምንዝናናባቸው።
ኧረ ግመልም ከፈለግህ በቅርፅ ተውቦ አለልህ!!! (ካስፈለገ የአዲስ አበባ አየር ከተስማማው ከነነፍሱ ማስገባት ይቻላል።)
NB. ድሮ ድሮ ሰዎች በሰብአ ትካት ደረጃ በጡንቻ በሚያምኑበት ዘመን ብሔራዊ ምልክታቸው ሌሎችን መሰባበር፤ አድኖና አሳዶ መብላት፤ ለእነርሱ ከርስ ሌላውን መስዋዕት ማድረግ ላይ ያነጣጠረ ነበር። ለምሳሌ፦ አንበሳ ድብ ንሥር… በሌሎች ላይ መጫን። በዚህ ስነልቦና ያደገ የፍቅር ምልክት ባይገባው አትፍረዱበት። ለዚህ እኮ ነው ጥላቻ አጃቢዋ ብዙ፤ ፍቅር ደግሞ ጥቂት የሆነው።

ይጠናቀቅና ትርጉሙም ከነሥፍራው ይገለፅ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይን የሥልጣን ዘመን ይባርክ። አትራፊ ሀገርና ህዝብ ናቸውና!

3 COMMENTS

 1. እንዴ ይኼ ሰዉዬ መልስ መስጠቱ ነዉ መሳደቡ? ዊኪፒዲያ ኮፒ ፔስት አድርጎ የጻፈዉን በትልቅ ምርምር ጊዜ ወስዶ እንዳቀረበዉ አይነት ሲያቀርብና ሲዘባነን ትንሺ አይሰቀጥጠዉም። አንዱን ጀምረን አይመለስብንም ብለን ስንሸኘዉ እንዲህ አይነት ይመጣብናል። ጎበዝ ይሄ ሰዉ ቀደም ሲል የኦሮሞ ድርጅት አሁን ደግሞ ብልጽግና ዉስጥ እርሶ የተባለ ምልምል ነዉ።
  ገና ወደ ከፍተኛዉ እርከን ሳይደርስ እብሪቱ እንዲህ ከጨመረ የምርጫዉ ኮሮጆ ተደፍቶ ስልጣን ላይ ቁጭ ካለ ዜጋዉን ምን ያህል ቁም ስቅል እንደሚያሳይ መገመት ይቻላል።፡እንዴት ያለ ደረጃዉን ያልጠበቀ መልስ ነዉ? ግለሰቡ ሀይ የሚለዉ የለም ባለፈዉ 2 ሚሊዮን በ\ጠራራ ጸሀይ ጠፋብኝ ብሎ ደግ አደረግህ እንኳን አንተ ጤና ሆንክልን የተባለ እቡይ ካድሬ ነዉ።፡መገላገያዉን ይስጠን እንጂ ያሁኑ ሳይብስ አይቀርም።

 2. በአንተ ቤት መልስሰጥተህ ሞተሀል ስራ የፈታህው አንተና ያ በግማሽ የተማረው ጠሚህ ነው
  እገሪቱ ስንት ችግር ባለባት ሰዓትቤተ መንግስቱን እንደግል መዝናኛ ግቢው በዚህ መሀል ላይ በቆመ የጥራዝ ነጠቅ ጣዕሙ የእንሰሳት ማሳያ የመዝናኛ ግቢ የስጋና የቡና መሸጫ አርጎ ቅጥ ባጣ መልኩ ሲያተራምስው ዝም ብላችሁ አጨብጭቡ ነው የምትለን? ለአንተም ለአለቃህም እውቀትና ስልጣኔና በትምህርት የሰላ ጣዕም በጉልበት እይመጡም! ለነገሩ ያጨበጨበልህ ዞር ብሎ ይስቅብሀል እንዳንተ በሆድ የሚያስብ ደፋር ካልሆነ በቀር ባንተ ቤት ሰርተህ ልብህ ውልቅ ብሉዋል! እንዳንተ ያለውን ጥራዝ ነጠቅ ስልጣን ላይ ሳይ ላገሬ ህዝብ በጣም እፈራለሁ

 3. የዘረኛ አእምሮ መላ ሲጠፋው ወፍ ይስላል!!
  አዬ አቶ ታዬ ደንድአ!!
  የዘረኛ አእምሮና የነጠፈች ላም ጡት አንድ ናቸው ። ቢጨምቁት፣ ቢጨምቁት ጠብ አይልም ። ከዘረኛ አእምሮም የወጣው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ነው።ሌላ ምንም!! ኗሪውን አፈናቅሎ መንገድ ላይ በመጣል ሀብቱን ና እርስቱን መዝረፍ ነው። አቶ ታዬ ይሄንን ነው “አገር ለማጎልበት እየታተርን ነው” የሚለው። እንዲህም አድርጎ መታተር የለ!!! አፓርታይዳዊ ብልፅግና! !
  ለውዝግቡ ማብራሪያ ይሆነኝ ዘንድ የሚከተለውን ላስቀደም ፤
  እንዲያው እኔን የሚገርመኝ፣ የኦሮሞ ድርጅቶችና ምሁሮች ካለመዝረፍ፣ካለመውረር፣ካለማፍረስና የታሪክ ቆርጦ ቀጥሎች ከመሆን ሌላ የምታውቁት ነገር የለም ማለት ነው!!!?? ብቻ አይፈረድባችሁም! የ 16ኛው ክፍለ ዘመነ ወራሪ አባቶቻችሁ፣ ኗሪውን ሕዝብ ወርረው ወንዱን እየሰለቡ፣ እያፈናቀሉ እርሰቱን ዘርፈው በሞጋሳ አስገድደው ኦሮሞ እያደረጉ፣ ተገዢ ማድረግና የወረሩትን አካባቢ የኦሮሞ ስም መስጠት እንጂ ለስሙ አንድ ከተማ እንኳን አልቆረቆሩም።
  የአሁኖቹ የኦሮሞ ድርጅቶችና ምሁሮች፣ “አገር አጎለበትን” የሚሉት ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን አፈናቅለው፣ ጨለማን ተገን አድርገው፣ ቤታቸውን በማፍረስ ፣ እርስታቸውን መዘረፋቸውን ነወ።
  ፒኮክና የጥቁር አንበሳ
  የፒኮኳንም ጉዳይ በተመለከተ፣ የተነሳው ጥያቄ፣ “እነዚህ ዘረኞች የመጡት ታሪካዊ ቅርሶችን ለማውደም ነው እንዴ” የሚል በመሆኑ የአቶ ታዬ ከመዝገበ ቃላት ተገልብጦ የመጣው ትርጉም ፣የውዝግቡን አቅጣጫ ለመቀየር የታለመ የመደዴ ብልጠት ነው እንጂ ለመሰረታዊው ውዝግብ ያበረከተው ቅንጣት ያህል የለም።
  የዚህ መሠረታዊ ውዝግብ መነሻው፣ለምን ታሪካዊው የአንበሳ ቅርፅ፣ ያለምንም ውይይት በፒኮኳ ተተካ ነው። እንደሚታወቀው ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያለው የአትዮጵያ ታሪክ የኦሮሞም ታሪክ ነው። የ ኦሮሞ ደጃዝማቾችና ሌሎች የኦሮሞ የጦር መሪዎች የኢትዮጵያን ንጉሦች አንግሠዋል፣ አውርደዋል። ስለዚህም የአንበሳው ታሪካዊ ቅርስነት ለኦሮሞም መሆኑ የማይካድ ነው። ለኢትዮጵያ ንጉሣቸው እነደ አንበሳ የተዋጉ ኦሮሞ የጦር መሪዎች ፣ወታደሮችን እኛ ኦሮሞ ያልሆንን ኢትዮጵያውያን ስማቸውን ከፍ አድርገን ይዘናል። እንደ አቶ ታዬ ያሉት የታሪክ ቆርጦ ቀጣዮች፣ ሞዓ አንበሳ ኦሮሞ ሳይሳተፍበት የመጣ አድርገው በማስቀመጥ፣ ሱሪአቸውን ሳይፈቱ የውሸት ጡሩምባቸውን ይነፋሉ።
  በሚከተሉት ሁለት ነጥቦች ለአቶ ታዬ በጣም አፍሬለታለሁ፤
  1ኛ “,,,,,,, ወገብ ከመፈተሽ ሳትላቀቅ,,,,,,,,,,,,,, „ ያልከው „እኔ ተላቅቂያለሁ ለማለት ነው!!!???” አንተ ከየትኛው ማህበረሰብ መጣህና!!!!!!
  2ኛ “ድሮ ድሮ ሰዎች,,,,,,,,,, ለእነርሱ ከርስ ሌላውን መስዋዕት ማድረግ ነበር። በዚህ ስነልቦና ያደገ የፋቅር ምልክት ባይገባው አትፍረድበት” ያልከው “እኔ የፍቅር ሥነልቦና አለኝ”፣ለማለት ነው?? አቶ ታዬ!! እሱን ደሴ ካቲካላ ቡሲ!!
  የእናንተ ስነልቦና የዘረኞች፣ፍቅር ሲያልፍ እንኳን ያልነካው ስነልቦና ነው። መግደል፣ማፈናቀል፣መዝረፍ መውረር ነወ።

  ፈጣሪ ለምትገድሉትና ለምታፈናቅሉት ህዝብ ሲል ሥልጣናችሁን ጎምዶ ዘመናቸወሁን ያሳጥረው!!!! አሜን አሜን!!!!!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.