የጎጃም መሬት ከሚለማ የሲናይ በረሃ ቢለማ እመርጣለሁኝ ብየ አስባለሁ።

የእነ እንዘጭ እምቦጭ የሁለት የህወሃት ትውልድ ወግ
1) «.. አማርኛ ለመማር ያጠፋሁት ጊዜ ይቆጨኛል»
(ሜ/ጀነራል ተ/ብርሃን ተ/ሃይማኖት)
.
2) «…በዚህ ግዜ፣ ለዘለቄታውም ቢሆን የአባይ ግድብን ጠሚ ዓብይ እና ም/ጠሚ ደመቀ ከሚያስተዳድሩት አል ሲሲ ቢያስተዳዳረው እመርጣለሁኝ። የጎጃም መሬት ከሚለማ የሲናይ በረሃ ቢለማ እመርጣለሁኝ።»
ዶ/ር ጎይቶም ገብረ አናንያ (Ztseat Save Adna)

«…በዚህ ግዜ፣ ለዘለቄታውም ቢሆን የአባይ ግድብን ጠሚ ዓብይ እና ም/ጠሚ ደመቀ ከሚያስተዳድሩት አል ሲሲ ቢያስተዳዳረው እመርጣለሁኝ። የጎጃም መሬት ከሚለማ የሲናይ በረሃ ቢለማ እመርጣለሁኝ።»

ይኼን ንግግር የተናገረው ጥላቻና ዘረኝነት እንደ ጋንግሪን እየገዘገዘው ያለው በምስሉ የምታዩት ሀኪም ዶር ጎይቶም ገብረ አናንያ (Ztseat Save Adna) ነው። የጥላቻውና የዘረኝነቱ ብዛት ማሰቢያውን ሁሉ ተቆጣጥሮታል፤ የሚጠላውን ሰው ወደ እሱ ለህክምና ቢሄድበት መርዝ ወግቶ ለመግደል ወደ ኋላ የማይል ቆሻሻ ሰው ነው

ይመዝገብ!!

Brook Abegaz

 

 

3 COMMENTS

 1. ይሄ ቆሻሻ ፐሮፌሺናል ኤቲክ የሌለዉ ጠላቴ ብሎ የሚገምተዉን ሁሉ ወግቶ ለመግደል ወደ ሗላ የማይል በመሆኑ ሀገር ቤት ከሆነ ጉዳዩ ለፕሮፌሺናል ቦዲ ቀርቦ ፍቃዱን መነጠቅ ይኖርበታል። የስራ ቦታዉ መቀሌ ከሆነ ወደዛ የሄዱ ኢትዮጵያዉያን እሱ እጂ እንዳይወድቁ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።፡ሌላዉ በትምህርት ሳይሆን ትግሬ ጄነራል ብሎ የሰጠዉ ተክለ ብርሀን ዶ/ር አብይ ተከታትሎ አዲስ አበባ የዘረፈዉን መሬትና ንብረት ባስቸኳይ በቁጥጥር ስር እንዲያደርግ እንጠይቃለን ሜጀር ጀነራል አበበ/ተክለ ብርሀነ፤ጻድቃን …. ሰየ አብረሃ እንኳን ለጄነራል ለ 10 አለቅነት ብቃት የሌላቸዉ ማፈሪያዎች ናቸዉ።፡ደም መጣጭ ዘረኛ ሁሉ።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 2. በእውነተኛ ሚዛን ላይ ቢመዘን ይህ ሰው እንኳን ሜ/ጄ የአስር አለቅነት እይታና ብቃት የሌለው አብሮ ሲያስር፤ ሲገልና ሲዘርፍ የኖረ ዛሬም ትላንትም በትግራይ ህዝብ ስም ከነገድ የፓለቲካ ተኩላዎች አንድ ነው። እነዚህ አጥፊ ሃይሎች ተለቅመው እሥር ቤት መሆን ነበረባቸው። ግን የዶ/ር አብይ አመራር ያዝ ለቀቅ በመሆኑ ዛሬም የሃገሪቱን ሃብት እየመዘበሩ ለግብጽ መቆማቸው አስገራሚ አይሆንም። ይህ ሰው ከሃገሪቱ የመከላከያ በጀት የሚከፈለው ነገር ካለ መቆም አለበት። አማርኛ ለመማር ያጠፋሁት ጊዜ ይቆጨኛል። ታዲያ ጣሊያንኛ ተማርና አማርኛው ይረሳህ! እንዴት ዶ/ር ነኝ ባዬ ወያኔ ከጎጃም መሬት ይልቅ የሲናይ በረሃ ቢለማ እመርጣለሁ ይላል። የወያኔ ድርቡሽነት ሥራና አፋቸው የሚመስክረው መሆኑ ዛሬም በፊትም እየታየ ነው። ሲናይ ሲለማ ጥጥ ለቃሚ ለመሆን ይሆናል ለግብጽ የሚታገለው። በዶክተርነቱ እንደማይሰራ በግልጽ እናውቃለን። እንዲህ አይነት አሳፋሪ ንግግር የሚያደርጉ ወስላቶችን እንዴት ዶ/ር ደብረጽዪን ዝም ብሎ እንደሚመለከታቸው ይገርመኛል። በምንም ሚዛን ለማንም አይጠቅሙም።
  በእውነት በዚህ ዶ/ር ታክሞ የዳነ ህመምተኛ ይኖር ይሆን? አይመስለኝም። እንዲህ አይነት መራራ ነገር ከውስጡ የሚመነጭ ሲመረቅ የገባሁን ቃል ኪዳን (Hippocratic Oath) ጠብቆ ሁሉን በሽተኛ ባለው ችሎታ ይረዳል ብሎ ማመን አይቻልም። ዘረኞች ለዘራቸውም ሆነ ለሌላው አይጠቅሙም። ለራሳቸው ብቻ የቆሙ የቀን ጅቦች ናቸው። ይህ ዶ/ር ካዳናቸው የገደላቸው እንደሚበዙ ከወዲሁ መገመት ይቻላል። ዶ/ር ካላላችሁኝ ሞቼ እገኛለሁ በማለት ለድላ የሚጋበዙ እቡዮች ያሉበት ሃገር ነው። ከሩቅና ከቅርብ እየተሸመተ ዶ/ር የተባለው ሁሉ ተግባረ ቢስና በወሬ ብቻ የተሞላ ባዶ ወናፍ ነው። እስቲ ተምሬአለሁ ያለ ሰው እንዲህ አይነት አሳዛኝ ነገር በሚዲያ ላይ ይናገራል? ትላንት 2 ሚሊዪን አማሮች የት እንደገቡ አላውቅም ያለው ወያኔ ከፍራቻው የተነሳ የጀግና እና የአርበኛ ልጆችንና የልጅ ልጆችን ጭምር ነው እያፈነ አፈር የመለሰባቸው? ዛሬም ከግብጽ ጎን ተሰልፎ ኑ እንደግፋችሁሃለን ቢል ራሱን ቂል ያረጋል እንጂ የዓለም የፓለቲካ ንፋስ ራሳቸውን ጉድጓድ ውስጥ እንደሚከታቸው የታወቀ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ያለ መዥገርና መሰሪ ጭራሽ ተፈጥሮ አያውቅም። አብረው በልተው ገድለውህ ሃዘን አብረው የሚቀመጡ ውሾች ናቸው። ምናቸውም አይታመን። ታሪካቸውን ከወደኋላ ጀምሮ ለመረመረ ስራቸው ሁሉ ማፊያ ነው። ጄኔራል ነኝ ባዪና ድክትርናውን ትራስ ያረገው የወያኔ ጀግኖች የሚያፍሩበት ቀን ሩቅ አይሆንም። አይ መማር ድንቄም ትማር። የተማረ ይግደለኝ ብሎ ነበር የሃገሬ ሰው። ይኸው ቆቡን እየደፋ እየገደለሽ ነው። እልል በይ። ባይማር ይሻል ነበር። ወይ ጄኔራል ወንድሙን ገድሎ ጄኔራል – የትኛውን የሃገር ድንበር አስጠብቆ ነው ጄኔራልነት? ሃገር መሸጥ፤ መርከብ መሽጥ፤ ሰው መግደል፤ ጫት መነገድ አዎን ጄኔራል ያስብላል በወያኔ መስፈርት። ድርቦሾች!

 3. ወያኔ ባለፉት ሁለት አመታት እንደለመደው አጀንዳ ቀርፆ በግብረበላቹ በዋናነት ራሱ በሚያዛቸው በገለጻ መልክ፣ በቃለምልልስና በዜና ይለቃል፡፡ ኮሮናን መንግስት በጥብቅ ዲሲፕሊን እየሠራበትና ውጤታማ መሆኑ አልተማቻቸውም፡፡ ቢቻል በሺ የሞቆጠር ህዝብ በበሽታው ተለክፎና ሞቶ የአብይ መንግስትን ለማሳጣት፣ ትግራይን ክልል አጥሮ ደግሞ ምንም ጉዳት አልደረሰብንም አሁንም አንደኛ ነን ለማለት አስቦ አልተሳካም፡፡ ስለዚህ የኮረና ጉዳይ አላዋጣ ሲል በማፈግፈግ ወደፖለቲካው በመመለስ የሚደረገውን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ማዳከም ለኛም አጀንዳ እያቀበለ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል ከሰሞኑ/ሳምንት ባልሞላ ቀናት
  1. ለኮረና መከላከል ትግራይ ከፌዴራል መንግስት በቂ ድጋፍ አላገኘም ተበድለናል ይላል፡፡ ማን እንደተጠቀመና ምን እንደተሠተው ግን ምንም አይነግሩንም—ደጺ
  2. አማርኛ ለመማር ያጠፋሁት ጊዜ ያሳዝነኛል–ምን እንደጎዳቸው አልነገሩንም–ካልታወቀ የሚሊታሪ አካዳሚ ጀነራል የተባሉት
  3. ምርጫው በወጣለት ካላንደር በነሃሴ መጨረሻ መካሄድ አለበት፡፡ የሰው መታመምና ሞት የናፈቃቸው፣ የህዝቡ መደጋገፍና መረዳዳት ያስደነገጣቸው፡፣ ክልሉ ያወጀው የ 3ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዘነጉ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ተብዬ ከመቀሌ፡፡
  ስለዚህ ገና በተደጋጋሚ፣ ከተለያዩ የክልሉ መሪዎችና ሚዲያዎቻቸው ገራሚ ወሬ ይነግሩናል፡፡ አላማው እኛን ከበሽታው አጀንዳ ለማስወጣትና የነሱን የረከሰ አጀንዳ ማንቆርቆሪ ሊያደርጉን፡፡
  እባካችሁ እንንቃ፡፡ በነሱ አጀንዳ በእኛ በእኛ ሜዳ አንጫወት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.